መግቢያ

        

ኢትዮጵያ እና መጽሐፍ ቅዱስበሚል ርዕስ በቀረበው በዚህ ጥናት፥ ኢትዮጵያ፥ ለዓለም፥ በቋንቋ፣ በታሪክ እና በአምልኮ ውስጥ የነበራትን ድርሻና ያበረከተችውን አስተዋጽዖ እንመረምራለን።

የጥናቱ አላማ፥ ኢትዮጵያውያ፥ ለዓለም ያበረከተቻቸውን መልካም ነገሮችን፥ ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ውስጥ በመፈለግ፥ ለአንባቢዎች፣ ለተመራማርዎች እና ለጸሐፊዎች፥ ለመነሻ የሚሆኑ ነጥቦችን ማጋራት ነው።

በዚህ ጥናት፤ ከአብርሃም ዘመን (2000 ዓመተ ዓለም) እስከ ክርስትና (በመጀመሪያው ዓመተ ምህረት) የነበረውን፥ በኢትዮጵያ ውስጥ የነበሩ ክዋኔዎችን፥ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መርምሮ ማቅረብ ይሆናል።

በተለይም፥ ስለ አብርሃም፣ ሙሴ እና ጌታ ኢየሱስ፥ በመጽሐፍ ቅዱስ የቀረበ ቋንቋን፣ ታሪክን እና ስርዓተ አምልኮን ይመረምራል፣ ያብራራል፣ ያልተጻፋ ክፍሎችን ከተጻፋት ጋር በማገናዛብ ለመረዳት እና ለማብራራት ጥረት ይደረጋል።

ኢትዮጵያ ለዓለም ህዝቦች፥ ስልጣኔ፣ ሰላም፣ ፍትህ... ወዘተ ያበረከተችውን፥ እና አስተዋጾ ያደረገውን የሚዳስስ፣ የሚመረምርና ተጨባጭ መረጃዎችን ለማሳየት የሚያስችል መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥናት ነው።

 

ጥናቱ፥ በአራት ክፍሎች የተከፈለ ነው፥

 

የመጀመሪያው ክፍል፥ ኢትዮጵያ ከታሪክ ጠባቂነት አኳያ፥ የዓለምን ታሪክ፥ በቃልና በጽሑፍ፥ ከማንም በፊት ያቆየችና፥ ለመጣው ትውልድ ያስተላለፈች፥ ስለመሆኗ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃዎች ቀርበውብታል።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተመዘገቡ፥ ሆኖም ግን ተያያዥነት ያላቸው ታሪኮች፥ የተከናወኑት በብዛት ኢትዮጵያ ውስጥ መሆኑን ግንዛቤ ያስጨብጣል። በታሪክ ውስጥ ፈዘዝ፥ ደብዘዝ ብለው፥ የተገለጹት ክንውኖችን፤ ጎላ ደመቅ ብሎ እንዲታይና እንዲታወቅ፥ ማድረግ አንዱ የጥናቱ አላማ ነው።

ምዕራባውያን፥ የኢትዮጵያን ታሪክ በጥቁር ወረቀት፥ በጥቁር ብዕር ሲመዘገቡ ኑረዋል። አሁን ደግሞ፥ የተሻለ ለማድረግ በመምሰል፥ ታሪካችሁን በነጭ ወረቀት ካልጽፍንላችሁ እያሉን ነው።

አንበሶች የራሳቸውን ታሪክ እስኪጽፋ፥ አዳኞች እንደ ጀግና ይቆጠራሉ።እንደሚሉት አፍሪካውያን፤ የኢትዮጵያ ታሪክ የግድ መጻፍ ያለበት በኢትዮጵያውያን መሆን እንዳለበት ያሳስባል።

 

ሁለተኛው ክፍል፥ ኢትዮጵያ ከቋንቋ አንጻር፥ ለተለያዩ የዓለም ቋንቋዎች ያበረከተቸውን፥ የእንግሊዝኛ ቋንቋን በምሳሌነት በመውሰድ፥ በንጽጽር ለማሳየት ተሞክሯል። ይህም ከዓለም ቋንቋዎች ውስጥ፥ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ቀዳሚ ስለመሆናቸው፥ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃዎች ቀርበውበታል።

ለሰዎች፥ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስሞችን የሰጠ እግዚአብሔር፥ በኢትዮጵያ ስለመሆኑ... እና እግዚአብሔር የሚጠራበትን በመጀመሪያ ያሳወቀው ለኢትዮጵያውያን መሆኑን፤ ለእግዚአብሔርም ስሞችን ያወጡ፥ ኢትዮጵያውያን ስለመሆናቸው እናያለን። እንዲሁም፥ በዓለም ላይ የሚታወቁ የመጽሐፍ ቅዱሳዊ የቦታ ስያሜዎች ሁሉ፥ አስቀድሞ በኢትዮጵያው ውስጥ የነበሩ ስሞች መሆናቸውን ለማሳየት ተሞክሯል።

 የጌታን፣ የመላእክት፣ የነብያት፣ የሐዋርያት፣ የቦታዎች እና የተለያዩ  ነገሮች ስሞችን ትርጉም ማወቅ፤ የስሞች ምንጭ (ሥርዎ ቃል) መነሻቸው እና መሰረታቸው የኢትዮጵያ ቋንቋዎች መሆናቸውን ለመረዳት እንዲያግዝ የሚያደርግ መንገዶችን ይጠቁማል።

መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስሞች፥ ከመጠሪያነት በተጨማሪ፥ ምስጢራዊ መልእክትና መንፈሳዊ ፍች ያላቸው መሆኑን ማወቅ እና ማሳየት መጽሐፍ ቅዱስን እና መንፈሳዊ መልክቱን በጥልቀት ለመረዳት እገዛ ያደርጋል።

በጽሑፍም ሆነ በቃል ያሉ መልእክታት፥ ከጊዜ ወደ ጊዜ፣ ከቋንቋ ወደ ቋንቋ በተተረጎሙ መጠን፥ ምን ያህል የመጀመሪያ ትርጉማቸውንና መልክታቸውን እየለቀቁ እንደሚሄዱ በመገንዘብ፥ ታሪክ  ጸሐፊዎች ትክክለኛውን ድርጊት መዝግበው ለማቆየት እንዲችሉ ያግዛል።

ይህን ጥናት እንደመነሻ በማድረግ፥ በሌሎች የተለያዩ  ቋንቋዎች መካከል ያለውን ውርርስ መመርመርና መረዳት፥ በዚህም ለቋንቋዎቻችን መዳበር ድጋፍ መስጠት ያስችላል።

 

በሦስተኛው ክፍል፥ አንድ እግዚአብሔርን ማምለክ፥ ከእስራኤልም ሆነ ከሌላው ዓለም ሕዝቦች በፊት፥ ከእግዚአብሔር ተቀብላ ስትፈጽም የቆየች አገር፥ ኢትዮጵያ መሆኗን፥ በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ታሪክ ተደግፎ ቀርቧል።

ከዚህ በታች የቀረቡት ነጥቦች፥ በስፋትና በጥልቀት፥ ተብራርተው ቀርበዋል።

1.     የኢትዮጵያን የቃል ኪዳን አገርነት... ሰባቱም ቃል ኪዳናት በኢትዮጵያ (ብቻ) ስለመኖራቸው።

2.     የኢትዮጵያ አገረ እግዚአብሔርነትን ማስገንዘብ... የእግዚአብሔር ቤት፣ የእግዚአብሔር መቀመጫ፣ የእግዚአብሔር ማደሪያ፤ የሚባሉ ነገሮች ጥንትም የነበሩት፥ አሁንም ያሉት፥ በኢትዮጵያ (ብቻ) ስለመሆናቸው።

3.     ጽድቅ፣ ቅድስና፣ ዘለዓለማዊ ህይወት...  እስራኤል ከመመረጡ በፊት፣ አብርሃም ገና ሳይጠራ፣ የጥፋት ውኃ ሳይወርድ፥ ኖህም መርከብ ሳይሠራ... በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያውያን ዘንድ (ብቻ) የነበሩ እሳቤዎች እና ግንዛቤዎች መሆናቸው። እግዚአብሔር፥ ለእስራኤል የተገለጠው፥ በኢትዮጵያውያን በኩል ስለመሆኑ... በሌላ አባባል፥ እግዚአብሔር በእስራኤል ከመታወቁ በፊት፥ በኢትዮጵያውያን ይታወቅ እንደነበር... ይበልጥ ግልጽ ለማድረግ፥ እስራኤላውያን አምላክን ያወቁት ኢትዮጵያ ውስጥ ስለመሆኑ... “ለኢትዮጵያውያንም ምግባቸውን ሰጠሃቸውያለው ቅዱስ ዳዊት፥ እግዚአብሔር አምላክ፥ ቃሉን (ቃል አብን፥ ቃለ እግዚአብሔርን...) ከማንም በፊት ለኢትዮጵያውያን መስጠቱን ለመግለጽ መሆኑ።

4.     የጌታ ኢየሱስ፣ የመቤታችን ማሪያም፣ የመልከጼዴቅ፣ የአቢሜሌክ ...እና የሌሎች ቅዱሳን የትውልድ ሐረግ በመጽሐፍ ቅዱስ አለመመዝገብ፥ ኢትዮጵያዊነታቸውን የሚያረጋግጥ መሆኑ።

5.     የቅዳሜ እና እሁድ ሰንበታት፥ በኢትዮጵያ (ብቻ) መከበራቸው፥ የሰንበትን አፈጣጠር፥ ከኢትዮጵያዊነት ጋር ያለውን ቁርኝት አጉልቶ ማሳየቱ።

 

በአራትኛው ክፍል፥ መሰረታቸው የኢትዮጵያ ቋንቋዎች የሆኑ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃላትን እና ስሞችን ከእንግልዝኛ ፍቻቸው ጋር በማነጽጸር፥ በማስረጃነት ቀርቧል።

No comments:

Post a Comment

ማውጫ

መግቢያ                                                                                                     ክፍል አንድ፡ ኢትዮጵያ እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ታ...