ክፍል ሦስት

 ኢትዮጵያ እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ አምልኮ (Theological studies)
በዚህ ክፍል፥ ኢትዮጵያ እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ አምልኮ፥ በሚል ርዕስ፥ ኢትዮጵያ በቀረው ዓለም የአምልኮ ሥርዓት ውስጥ ያላትን ድርሻና ያበረከተችውን፥ አስተዋጽዖ እንመረምራለን።
በተለይም የመጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል ኪዳናትን፥ አመሠራረትና አፈጻጸም፥ ለመመርመርና ለመረዳት ጥረት ይደረጋል።
ኪዳንናት (covenants/ testaments)
1.     ምዕራፍ አንድ፥ ታቦት (Tablet)
2.     ምዕራፍ ሁለት፥ ሰንበት (Sabbath)
 ምዕራፍ አንድ
 ታቦት እና ኢትዮጵያ
በዚህ ምዕራፍ ሥር፥ ታቦት ምንድን ነው? ጽላት ምንድን ነው? የቃል ኪዳኑ ታቦት መቸ ወደ ኢትዮጵያ መጣ? ለምን ወደ ኢትዮጵያ መጣ? ለምንስ አይመለስም? ለምን ይሸፈናል? ለምን ብዙ ኖረንእና የመሳሰሉትን ጥያቄዎችን እያነሳን፥ ለመመለስ እና ለማብራራት ይሞከራል።
ሰባቱም የእግዚአብሔር ዋና ዋና የቃል ኪዳን ምልክቶች፥ የኖህ ቃል ኪዳን (ቀስተዳመናው በባንዲራው) የአብርሃም ቃልኪዳን (ግርዛት) የሙሴ ቃልኪዳን (ታቦቱ) የምህረት ቃልኪዳን (መስቀሉ) የዳዊት ቃልኪዳን (ንግሥናው)... ዛሬ የሚገኙትና የሚዘከሩት በኢትዮጵያ ነው። እንዴት እና ለምን ሁሉም የቃል ኪዳን ምልክቶች በኢትዮጵያ ውስጥ ሊገኙ ቻሉ? ይህን እና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች በማንሳት፥ መልስ ለመስጠት ይሞከራል።
ከዚህ በተጨማሪ የእግዚአብሔር አገር፣ የእግዚአብሔር ቤት፣ የእግዚአብሔር መቀመጫ (ወንበር) ቤተ መድኃኒዓለም፣ ቤት ማርያም፣ ቤተ ጊዮርጊስ፣ ቤተ ገብርኤ፣ ቤተ ሩፋኤል፣ ቤተ ራጉኤል... የተባሉ ቦታዎችና ህንጻዎች የሚገኙት በኢትዮጵያ ነው። እንዴትና ለምን ሊሆን ቻለ? የሚሉትንም ጥያቄዎች እያቀረብን፥ ለመመርመርና ለመመለስ አስፈልጊውን ያህል ጥረት ይደረጋል።
ታቦት (Tablet) የምስክር ታቦት (ዘጸ 2522)  የእግዚአብሔር የኪዳኑ ታቦት ( 31: 26) የእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት (2 ዜና 6: 11) የእግዚአብሔር ታቦት (ኢያ 4: 11) የእስራኤል አምላክ ታቦት (1 ሳሙ 5: 7) የአምላክ ታቦት እና የመቅደስህ ታቦት (መዝ 132: 8) በሚሉ መጠሪያዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ተመዝግቦ ይገኛል ... በአገራችን በኢትዮጵያም ታቦተ ሕግ፣ ታቦተ ጽዮን፣ የሙሴ ጽላት፣ ... እየተባለ ይጠራል።
ታቦት፥ በእስራኤል ህዝብና በእግዚአብሔር መካከል ለተደረገ ቃል ኪዳን፥ ምልክት እንዲሆን በሙሴ በኩል ለተሰጠው ጽላት፥ ማደሪያ ነው። ጽላት፥ አሥርቱ ትእዛዛት የተጻፉበት፥  ከእግዚአብሔር፥ ለእስራኤል ሕዝብ፥ በሙሴ በኩል የተሰጡ የድንጋይ ሰሌዳ ነው።
የቃል ኪዳን እና የትእዛዛት ዋናው ልዩነት፥ትእዛዛትግዴታዎች ሲሆኑ፥ አለመፈጸም ቅጣትን ያስከትላል።ቃል ኪዳንደግሞ ስምምነት ላይ የተመሰረተ ሲሆን፤ አለመፈጸም ጥቅምን ያሳጣል። ታቦት (እና በውስጡ ያያዘው ጽላት) የቃል ኪዳንም፤ የትእዛዝም ማራጋገጫ ምልክት ነው።
ኪዳን ማለት በሁለት ወይም ከዚያ በላይ ባሉ አካላት መካከል የሚደረግ ውል ወይም ስምምነት ማለት ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ከሰባት በላይ የሚሆኑ፥ ዋና ዋና ቃል ኪዳናት፤ በእግዚአብሔር እና በተለያዩ ሰዎች መካከል ተፈጽመዋል። አብዛኞቱ የመጽሐፍ ቃል ኪዳናት የተፈጽሙት በኢትዮጵያ ውስጥ ነው። ለምሳሌ፥ የኖህ የቃል ኪዳን ምልክት የሆነው፥ ቀስተ ደመና፥ ቃል ኪዳኑ ኢትዮጵያ ውስጥ በመፈጸሙ፥ የኢትዮጵያ ባንዲራ አርንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ሆነ። ቃል ኪዳኑ የተፈጸመው በቱርክ አገር ቢሆን ኑሮ፥ የቱርክ ባንዲራ አረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ ይሆን ነበር። የአብርሃም ቃል ኪዳንም የተፈጸመው ኢትዮጵያ ውስጥ በመሆኑ፥ የአክሱም ሐውልት ኢትዮጵያ ውስጥ ተተተከለ። የቃል ኪዳን ታቦቱን ሙሴ የተቀበለው ኢትዮጵያ ውስጥ በመሆኑ፥ የእስራውያን ቃል ኪዳን ሲፈርስ፥ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰ።
ኪዳናት በሁለት ይከፈላሉ፥ የቃል ኪዳን እና የጽሑፍ ኪዳን፥ በመባል።
ቃል ኪዳን፥ ከጽሑፍ ኪዳን በፊት የነበረ ነው። የጽሑፍ ኪዳን እንደገና ብሉይ ኪዳን እና አዲስ ኪዳን በመባል፥ በሁለት ይከፈላሉ።ቃል ኪዳናትከጽሑፍ ኪዳናት፥ በእድሜ ይቀድማሉ። ቃል ከጽሑፍ ይቀድማልና። ኢትዮጵያውያን የቃል ኪዳን ልጆች ሲባሉ፥ እስራኤላውያን ደግሞ የመጽሐፍ ልጆች ይባላሉ። ከአዳም እስከ ሙሴ ድረስ የነበሩ ኪዳናት ሁሉ፥ በኢትዮጵያ ብቻ የነበሩ በጽሑፍ ያልሰፈሩ፥ ቃል ኪዳናት ነበሩ።
የእስራኤላውያን የትውልድ ሐረግ፥ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተመዝግቦ ሲገኝ፥ የኢትዮጵያውያን ግን ስማቸው እና ሥራቸው እንጅ ትውልዳቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልተመዘገበም።
እንደ ምሳሌም፥ ታላላቅ የመጽሐፍ ቅዱስ ሰዎችን ለመጥቀስ፥ የንጉሥ አቢሜሌክ፣ የንጉሱና ካህኑ መልከጼዴቅ፣ የካህኑ ዮቶር፣ የንጉሥ ዳዊት ቅድመ አያት ሩት፣ የንግሥተ ሳባ፣ የንጉሥ ዳዊት ወታደር ኦርዮን፣ የሰሎሞን እናት ቤርሳቤህ፣ የኢትዮጵያዊው ነብይ አቤሜሌክ፣ የኢትዮጵያ ንግሥት ሕንደኬ፣ የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ፣ የመቤታችን የቅድስት ማርያም... የብዙ ነብያት፣ ሐዋርያት፣ ቅዱሳን ሰማዕታት... ስማቸው እና ታሪካቸው እንጅ የትውልድ ሐረጋቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተመዝግቦ አይገኝም።
1.    ታቦት ምንድን ነው?
ከግራር እንጨትም ታቦት ይሥሩ፤ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል፥ ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል ይሁን።~ ark (ዘጸ 25: 10)
ታቦት፥ ተቤት፣ ተቤተ፣ ቤተ... አደረ፣ ማደሪያ፣ ማስቀመጫ፣ ሳጥን... ሙሴም ይህችን ሕግ ጻፈ፥ እግዚአብሔርንም የቃል ኪዳኑን ታቦት (the ark of the covenant of the Lord) ይሸከሙ ለነበሩ ለሌዊ ልጆች ለካህናቱ ለእስራኤልም ሽማግሌዎች ሁሉ ሰጣት።” (ዘዳ 31: 9)
ጽላት፥ ለአንድ ጽሌ፥ ለሁለትና ከዚያ በላይ ጽላት፥ ፍችው፥ ሰሌዳዎች፣ ጠረጴዛዎች፣ መጻፊያዎች... እግዚአብሔርና የእስራኤልን ሕዝብ፥ በሙሴ በኩል ያደረጉት ስምምነት፥ ዋና ዋና ጉዳዮች የተጻፉባቸው፥ የድንጋይ ሰሌዳዎች ናቸው።
ታቦት፥ የጽላት ማስቀመጫ ሳጥን ነው። ጽላቱ ደግሞ የእግዚአብሔር ቃል የተጻፈበት ስለሆነ፤ ታቦት የእግዚአብሔር ማደሪ፤ መቀመጫ ዙፋኑ ሆነ ማለት ነው። ለሚታየው ለታቦት ሰገድን ማለት፥ በታቦቱ ላይ የማይታየው እግዚአብሔር ተቀምጧል ብለን በማመን ነው። ስለዚህ ታቦት ባለበት እግዚአብሔር አለ።
በሳኦልም ዘመን አልፈለግነውምና የአምላካችንን ታቦት ወደ እኛ እንመልስ አላቸው።” (1ዜና 13: 3) ይህን ያለው ንጉሥ ዳዊት ነው። ሰው ምድራዊ ስልጣን ሲያገኝ፥ መፈለግ ያለበት፥ ማረጋገጥ ያለበት፥ እግዚአብሔር ከርሱ ጋር መሆኑን ነው። የቃል ኪዳኑን ታቦት አለመፈለግ ማለት እግዚአብሔርን አለመፈለግ፣ ከእግዚአብሔር ጋር የተደረጉ ቃል ኪዳናትን ማፍረስ፣ የመገንጠል አላማን ማስፋፋት ... ማለት ነው።
2.    የቃል ኪዳኑ ታቦቱ የት ነው?
ዛሬ በዓለማችን ካሉ አገራት፥ በይፋ፣ ግልጽ እና ባልተድበሰበሰ መልኩ፥የቃል ኪዳኑ ታቦት የሚገኘው እዚህ ነው።የሚል፥ ከኢትዮጵያ በስተቀር፥ አንድም አገር የለም።
ለአራት መቶ ዓመት ያህል፤ ለእስራኤል ህዝብ ብርታት፤ ለመንግሥቱም ጽናት ሁኖ የኖረው የቃል ኪዳን ታቦት፤ ድንገት፥ ከእስራኤላውያን እይታም፥ ከመጽሐፍ ቅዱስ ትረካም በቅጽበት ተሰወረ።
ከብዙ መቶ ዓመታት ዝምታ በኋላ፥ ነብዩ ኤርሚያስ እንዲህ በማለት አወሳው፥በበዛችሁም ጊዜ በምድርም ላይ በረባችሁ ጊዜ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በዚያ ዘመን፦ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት ብለው ከእንግዲህ ወዲህ አይጠሩም ልብ አያደርጉትም፥ አያስቡትምም፥ አይሹትምም፥ ከእንግዲህ ወዲህም አይደረግም።” (ኤር 316) ለመሆኑ፥ እስራኤላውያን፤ ከአምላካቸው ከእግዚአብሔር ጋር የፈጸሙበትን የውል ሰነድ የያዘ ታቦት ሲጠፋ፥ ለምን አልፈለጉትም? ‘በእንደዚህ ዓይነት ቦታ አስቀምጠነዋ!’  የሚል አገርና ህዝብ ሲገኝ፥ ለምንስ መልሱልን አላሉም? ለእነዚህና ለመሳሰሉት ጥያቄዎች መልስ ይሆናሉ ያልናቸውን፥ በዚሁ ምዕራፍ ሥር ለመቃኘት እንሞክራለን።
3.    መቸ (ጽላት/ ታቦት) ወደ ኢትዮጵያ መጣ?
ወደ ኢትዮጵጵያ የመጣው፥ የዛሬ ሦስት ሽሕ ዓመት ገደማ፥ በምኒልክ ዘመን ነው። የኢትዮጵያ የሦስት ሺሕ አምት ታሪክ እየተባለ ሁል ጊዜ የሚወሳውም በዚሁ ምክንያት ነው። ቀዳማዊ ምኒልክ ወደ እስራኤል አገር የሄደው፤ የአባቱን ዙፋን ወርሶ፥ እስራኤልን እና ኢትዮጵያን አንድ አድርጎ ለመግዛት ነበር። ነገር ግን፥ የእስራኤላውያን ተቃውሞ ስለበረታ፤ ከእስራኤል አገር እንዲወጣና ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ ተደረገ። ይህም የሆነው፥ ከአባቱ ንጉሥ ሰሎሞን ፍላጎት ውጭ ስለነበር፤ በልጁ ቢጨክኑ በልጆቻቸው ስለማይጨክኑ በሚል፤ ሃሳባቸውን ለማስቀየር እና ልጁን በማስቀረት፥ የበኩር ልጁን በዙፋኑ ለማስቀመጥ፤ የሁሉም እስራኤላውያን በኩራት፤ ከበኩር ልጁ ጋር ወደ ኢትዮጵያ እንዲሄዱ አዘዘ። እስራኤላውያንም፥ የኢትዮጵያ ሰው በነሱ ላይ ከሚነግሥ፤ የበኩር ልጆቻቸውን ለኢትዮጵያ ንጉሥ መገበርን መረጡ። ይህም፥ኢየሱስ በላያችን ከሚነግሥ፤ ይሰቀልና ደሙ በልጅ ልጆቻችን ላይ ይሁን፥ካሉት ጋር ተመሳሳይነት አለው። ለዚህም እንደማስረጃ የሚቀርበው፥ የቤተ እስራኤላውያን ወገኖች በኢትዮጵያ መኖር ነው።
እስራኤል ከእግዚአብሔር ጋር ጨርሳ ያቋረጠችው በንጉሥ ሰሎሞን ዘመንና ከርሱ በኋላ በነበሩት መንግሥታትና ዘመናት ነው።
4.    ለምን (ጽላቱ/ ታቦቱ) ወደ ኢትዮጵያ መጣ?
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እናታችሁን የፈታሁበት የፍችዋ ጽሕፈት የት አለ? ወይስ እናንተን የሸጥሁ ከአበዳሪዎች ለየትኛው ነው? እነሆ፥ ስለ ኃጢአታችሁ ተሽጣችኋል፥ ስለ በደላችሁም እናታችሁ ተፈትታለች” (ኢሳ 501)
መጽሐፍ ቅዱስ፥ የእስራኤል ሕዝብን እና የአምላክ እግዚአብሔርን ግንኙነት፤ በባል እና በሚስት መካከል በሚደረግ ስምምነት መስሎ አስቀምጦታል። የጋብቻ ውል የሚፈርስበት አንድና ዋነኛ ምክኛት፤ የሴቲቱ ማመንዘር እንደሆነ የእስራኤላውያን የህግ መጻሕፍት ይመሰክራሉ። የፈታት ባል የፍችዋን ደብዳቤ ጽፎ ሲሰጣት፤ የተፈታችው ሚስት ደግሞ፥ የጋብቻው የቃል ኪዳን ምልክት የሆነውን፥ የተሰጣትን የእጣት ቀለበት ትመልሳለች።
አንድ ሚስት ስታመነዝር፥ ባሏን ስታታልል፥ ባሏ እንዲፈታት ህጉ ይፈቅዳል። ከተፈታችም፥ የጋብቻ የቃል ኪዳን ምልክት የሆነውን ቀለበት ለባሏ ትመልሳለች። ባልዬውም የተፈታች ሚስቱ የመለሰቻለትን ቀለበት በጨርቅ ጠቅልሎ፥ በሳጥን ያስቀምጠዋል። በፍርድ በተጠየቀ ጊዜም፥ ካስቀመጠበት አውጥቶ፥ ለዳኞች ያሳያል። ሌላ ሚስት ለማግባት ማስረጃውን በጥንቃቄ ያስቀምጣል። ይህ የፍች ማስረጃ፥ የማያኮራ ነገር ስለሆነ በግልጽ፥ ሁሉም ሰው በሚያየው ቦታ አይቀመጥም። ይህም ከመስቀል ክብር በተቃራኒ ነው። መስቀል፥ የአሸናፊነት፣ የድል አድራጊነት... አርማ ስለሆነ ሁሉም ሰው ሊያየው በሚችል ቦታ ይቀመጣል። መስቀል የሚለው ቃልም፥ ልክ ፎቶን እንደመስቀል ብዙ ሰው፤ ሁልጊዜ እንዲያየው ማድረግ ነው። የታቦት አቀማመጥ ደግሞ ከዚህ ተቃራኒ ነው።  
እግዚአብሔር ከአባቶች ጋር ያደረጋቸው ቃልኪዳናት በሙሉ የሚገኙት በኢትዮጵያ፥ ለማስረጃነት፣ እስራኤላውያን ቃል ኪዳናቸውን እንዳልጠበቁ ለማሳየት... መነሻውም ከኢትዮጵያ ስለሆነ። ኮሬብ በዛሬዋ የኢትዮጵያ ግዛት ሲሆን፥ ሙሴም ጽላቱን የተቀበለው በዚሁ ተራራ ላይ ነው። ሲና ተራራ እና ኮሬብ ያንድ ቦታ ስሞች ናቸውና። ሙሴ የቃል ኪዳን ታቦቱን የተቀበልው፥ በዛሬዋ የሳውዲ ሲና ተራራ ቢሆን ኑሮ፥ ታቦቱ ከእስራኤል ተመልሶ መቀመጥ የነበረበት በሳውዲ በሆነ ነበር።
5.    ለምንስ (ጽላቱ/ ታቦቱ) ለእስራኤል አይመለስም?
የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ሚስት ባልዋን እንደምታታልል እንዲሁ አታለላችሁኝ ይላል እግዚአብሔር፦” (ኤር 320)
ሚስት ባሏን በማታለሏ ከተፈታች፤ የፍችዋን ደብዳቤ የመጠየቅ እንጅ፤ የጋብቻ ቀለበቷን የይመለስልኝ ጥያቄ የማቅረብ፤ የስነልቦናም ሆነ የህግ ድጋፍ የላትም።
የተፈታች ወይም የፈታች ሚስት፥ የፈታችው ባልዋ ያጠለቀላት ቀለበት፤ ፍችው ከጸና ምን ፋይዳ ይኖረዋል። እስራኤልም ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን የተግባቡበት የምስክር ታቦት፥ ከእግዚአብሔር ከተለያዩ፤ አይፈልጉትም፣ ጌታን እስካልተቀበሉ ድረስም አይጠቅማቸውም...
ባልና ሚስት በተለያየ ምክንያት ፍች ሲፈጸም፥ ባልየው ለእጮኛው የሰጣትን ቀለበት ትመልሳለች። ሴትዮዋ ጋር ቢቆይም ጠቀሜታ የለውም። ከተፋታችና ቀለበቱን ስጠኝ የምትልበት ምንም ዓይነት ምክንያት አይኖርም። እንደዚሁም የቃል ኪዳኑ ታቦት አገልግሎቱ ያበቃው እስራኤል ከአምላክ ጋር ያላትን አንድነት ስታቋርጥ ስለሆነ፥ አንድነቱ እስካልታደሰ ድረስ፥ ታቦቱን ለመጠየቅ ያሚያበቃ ፍላጎትም ሆነ ምክንያት የላትም። እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ፥ በበዛችሁም ጊዜ በምድርም ላይ በረባችሁ ጊዜ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በዚያ ዘመን፦ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት ብለው ከእንግዲህ ወዲህ አይጠሩም ልብ አያደርጉትም፥ አያስቡትምም፥ አይሹትምም፥ ከእንግዲህ ወዲህም አይደረግም።” (ኤር 316)
6.    ለምን (ጽላት/ ታቦት) ይሸፈናል?
እስከ ቅርብ ዓመታት፥ አስርቱ ትእዛዛት የተጻፈባቸው የድንጋይ ጽላቶች በአሜሪካን የመንግሥት መሥሪያቤቶች፣ ትምህርት ቤቶች እና የመማሪያ ክፍሎች ግድግዳ ላይ ይደረጉ ነበር። አሁንም፥ በአሜሪካ የፍርድ ቤቶች ቅጽር ግቢ በትላልቅ የእብነበረድ ጽላቶች ላይ ተጽፈው፥ ለሁሉም ሰው እንዲታዩ ሁኖ፥ እንደሐውልት ይተከላሉ። ይህም ድርጊታቸው፥ ጽላትን፥ እንደ ሰንደቅ አላማ እና የመስቀልን ምልክት ከማሳየታ ጋር ያመሳስለዋል።
ወደ ኢትዮጵያ ስናይ ደግሞ፥ መስቀል እና ሰንደቅ አላማ ጎልተው ከሚታዩበት ቦታ ሲቀመጡ፥ ጽላት ግን፥ ተሸፍኖና ተደብቆ በሳጥን፥ ከካህን በስተቀር፥ ሰው በማይደርስበት፥ በመቅደስ ውስጥ ይቀመጣል። መስቀልም፣ ሰንደቅ አላማም ሆነ ጽላት፥ ሁሉም፥ የቃል ኪዳን ምልክት ናቸው። ባንዲራና እና ሰንደቅ አላማ (ቀስተ ደመና) ለምእመናን እንዲታዩ፥ ግልጽ ቦታ ላይ ሲቀመጥ፥ ጽላት ግን ከምእመናን እይታ እንዲሰወር ይደራጋል።
ምክንያቱ እንዲህ ነው፥ ዛሬ በኢትዮጵያ ያሉ ታቦታት፥ የእስራኤልን ከእግዚአብሔር መለያየት የሚገልጹ፥ ማስረጃና ማረጋገጫ ናቸው።ከዳተኛይቱም እስራኤል ስላመነዘረች ስለዚህ ፈትቻታለሁ የፍችዋንም ወረቀት ሰጥቻታለሁ አታላይ እኅትዋ ይሁዳ ግን እንዳልፈራች እርስዋም ደግሞ ሄዳ እንደ ጋለሞተች አየሁ” (ኤር 38) በበዛችሁም ጊዜ በምድርም ላይ በረባችሁ ጊዜ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በዚያ ዘመን፦ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት፡ ብለው ከእንግዲህ ወዲህ አይጠሩም፤ ልብ አያደርጉትም፥ አያስቡትምም፥ አይሹትምም፥ ከእንግዲህ ወዲህም አይደረግም።” (ኤርምያስ 3:16)
ፍች የሚያኮራ፣ የሚያመጻድቅ፣ የሚስደስት ጉዳይ ስላልሆነ፤ የፍች ደብዳቤ በሳጥን ተከድኖ ይቀመጣል።
የጋብቻ ፎቶ፥ ወይም የወድድር አሸናፊነት ማስረጃዎች፥ ሁል ጊዜ ብዙ ሰው ሊያየው በሚችል መልኩ፥ ከፍ ብለው ይሰቀላሉ። በአንጻሩ የፍች ማስረጃ፥ ሁል ጊዜ ሰው ሊያየው በማይችልበት ሁኔታ፥ በፍርድ ቀን እንዲቀርብ እስከሚጠየቅበት ቀን ድረስ፥ ተሸፍኖ ይቀመጣል። ለኃይል እና ለክብር ተብሎ ለእስራኤላውያን የተሰጣቸው የቃል ኪዳን ታቦት፤ ውሉን ሲያፈርሱ፥ የታቦቱ ባለቤት ወደሆነው፥ ወደ እግዚአብሔር አገር ይመለስና፥ እስከ ፍርድ ቀን ተሸፍኖ ይቀመጣል።
7.    ለምን (ጽላት/ ታቦት) ብዙ ኖረን?
እንደ ኖሕ ቀስተ ደመና (ባንዲራ) የአብርሃም ግርዛት (የአክሱም ሃውልት) እንደ ጌታ የምሕረት ኪዳን (መስቀል፥ ማተብ)...
የመጀመሪያው ባንዲራ፥ ዛሬ የት እንደደረሰ  የሚያውቀው እግዚአብሔር ብቻ ነው። የመጀመሪያው ባንዲራ ቢኖርም ባይኖርም፥ እስከ ዛሬ ባንዲራ አለን። ይህ ባንዲራ የኛው፥ የራሳችን  እስከሆነ ድረስ የግድ የመጀመሪያው ካልሆነ ለማለት አይቻልም። ልክ እንደ ባንዲራው፥ በቃል ኪዳን ምልክትነቱ፥ የመጀመሪያው ቢሆንም፥ ባይሆንም ቃል ኪዳኑን ለማስጠበቅ በሌላ የቃል ኪዳን ታቦት ምልክትነት፤ ቃል ኪዳኑ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲያስተላልፍ ይኖራል። የአብርሃም የቃል ኪዳን ምልክት የሆነው፥ በአብርሃም ግርዛት ብቻ ተወስኖ የቀረ ሳይሆን፥ በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ወንድ ሁሉ ላይ የሚደረግ የቃልኪዳን ምልክት ነው። ጌታ የተሰቀለው በአንድ የእንጨት መስቀል ነው፤ ሁሉሙ ክርስቲያን ደግሞ፥ የድህነት ምልክት የሆነውን መስቀል ተሸክሞ ይሄዳል። ታቦታትም ይህንኑ አካሄድ በመከተል፥ የመጀመሪያው ታቦት ቢሆንም፥ ባይሆንም ቃል ኪዳኑን የሚያሳስቡ ታቦታት በየቤተክርስቲያናቱ ይቀመጣሉ።
 
 ምዕራፍ ሁለት
 ሰንበት እና ኢትዮጵያ
እግዚአብሔርም የሠራውን ሥራ ሰባተኛው ቀን ፈጸመ በሰባተኛውም ቀን ከሠራው ሥራ ሁሉ ዐረፈ።” (ዘፍ 2: 2)
በዚህ ምዕራፍ ሥር፥ ሰንበት፥ በሦስቱም ኪዳናት ውስጥ፥ ማለትም በቃል ኪዳን (ከመጻሕፍት በፊት) በብሉይ ኪዳን (በኦሪት) እና በአዲስ ኪዳን (በወንጌል) ውስጥ እንዴት እንደተመሰረተ፣ እንዴት እንደተገለጸ፣ እንዴት እንደተፈጸመ.... እየመረመርን እና እያብራራን እናቀርባለን።
እንዲሁም፥ ሰንበት፥ ምንድን ነው? የቃሉ ትርጉም... ሰንበት፥ መቸ ነው? ቅዳሜ፣ ዕሁድ፣ ወይስ ሌላም? ሰንበት፥ ማን ነው? ሰንበት ለሰው ተፈጠረ እንጅ፥ ሰው ለሰንበት አልተፈጠረም... የሰው ልጅ የሰንበት ጌታ ነው... እና የሰው ልጅማለት ምን ማለት ነው? የሚሉትን እና የመሳሰሉትን ሀሳቦች ለማስረዳት፣ ለማብራራትና ለማስገንዘብ ይሞከራል።
ከዚህ በተጨማሪም፥ የሰንበት ትእዛዛት፥ ጠብቁ፣  ቀድሱ፣ አክብሩ... እና የመመሳሰሉ እይታዎችን ለመዳሰስ እንሞክራለን።
እግዚአብሔር የሠራቸው እና የሠራባቸው ቀናት ሰባት ናቸው። ስድስቱ ቀናት ፍጠረታትን የፈጠረበት ቀናት በመሆናቸው፤ በሁሉም ዘንድ በግልጽ የታወቁ ናቸው። በሰባተኛው ቀን የሠራው ሥራ ግን፥ የፍጥረት ሥራ ባለመሆኑ፥ በግልጽ አልታወቀም። በሰባተኛ ቀን እንደሠራ የምናውቀው፤ ሥራውን የጨረሰው በሰባተኛው ቀን በመሆኑ ነው። እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ፥ ‘... ሥራውን፥ በሰባተኛው ቀን ፈጸመ...’ (ዘፍ 22)
እግዚአብሔር፥ ያልሠራበት እና የማይሠራበት ቀን የለም።በሰባተኛው ቀን ሰርቷል በሚለው ከተስማማን፥የሠራው ሥራ ምንድን ነው?’ ወደሚለው ጥያቄ እናመራና መልሱን እናያለን። በርግጥ እግዚአብሔር ዛሬም ይሠራል... “ኢየሱስ ግን፦ አባቴ እስከ ዛሬ ይሠራል እኔም ደግሞ እሠራለሁ ብሎ መለሰላቸው።(ዮሐ 5: 17)
እግዚአብሔር የሠራው ሰባት ቀን ከሆነ፥ በሰባተኛው ቀን የሠራው ምንድን ነው? በሰባተኛው ቀን አረፈ ሲል፥ የእግዚአብሔር እረፍት ማለትስ ምንድንና እንዴት ነው
...ዓለሙን ከፈጠረበት፥ ሰውን ያዳነበት ጥበቡ ... እንዲሉ አበው፤ ከስድስቱ ቀን ፍጥረታት ይልቅ፥ የሰባተኛው ቀን ሥራው የላቀ ነው። እሱም፥ ሰውን ለማዳን፥ አምላክ ሰው የሆነበት ሥራ ነው።
በአጭር አገላለጽ፥ ሰንበት፥ እግዚአብሔር አምላክ አዳምን ከዘላለማዊ ሞት፥ ወደ ዘላለማዊ ህይወት የመመለስ ሥራውን የሠራበት፥ ቀን (በጊዜ) ስም (መጠሪ) እና ሰው (አካል) ነው። ጊዜው ቅዳሜ (ሰባተኛው ቀን) ስሙ የሰው ልጅ (የእግዚአብሔር ልጅ...) አካሉም ጌታ ኢየሱስ ነው።
የእስራኤልም ልጆች ለልጅ ልጃቸው ለዘላለም ቃል ኪዳን በሰንበት ያርፉ ዘንድ ሰንበትን ይጠብቁ” (ዘጸ 31: 16) የዘላለም ቃል ኪዳን፥ በጌታ ኢየሱስ የተገኘ ድኅነት ነው። ይህም ድኅነት የሰንበት እራፍት የተባለው ነው። ስለዚህ፥ ጌታ ኢየሱስ፥ እስኪመጣ እንዲጠብቁት የታዘዙትሰንበት ነውማለት ነው።
የምቀድሳቸውም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቁ ዘንድ፥ በእኔና በእነርሱ መካከል ምልክት ይሆኑ ዘንድ ሰንበታቴ ሰጠኋቸው።~ a sign between me and them (ሕዝ 20: 12) [ሰንበታት የተባሉ የእግዚአብሔር ቅዱሳን፥ መሆናቸውን ሲያመለክት፥ “...ካህናትህ ደኅንነትን ይልበሱ ቅዱሳንህም በደስታ ደስ ይበላቸው።ብሏል (1ዜና 6: 41)
ሰንበት፥ ሦስቱ ባሕርያትን (መገለጫዎችን) የያዘ ነው። እነሱም፥  ሴማዊ፣ ጊዚያዊ እና ሰባዊ ናቸው።
1.    የሰንበት ሴማዊ ባሕሪ (ሰንበት፥ ምንድን ነው? የቃሉ ትርጉም...)
ሴም፥ ማለት ስም ማለት ነው። ሴማዊ ባሕሪ ስንል፥ የሰንበትን ባህሪያት የሚገልጹ መጠሪያዎች፥ ማለት ነው። ይህምሰንብት ምንድነው?’ ተብሎ ለሚጠየቅ ጥያቄ፥ መልስ ይሆናል።
ሰንበትየሚለው ቃል ፍች፥ ሰባት ማለት ነው።
ሰንበት፤ (ሰብዐ ሰብዐት ዕብ ሻባት ሱር ሻብታ ዐረ ሰብት) (ኪወክ)
በእንግሊዝኛው መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ፥ Sabbath, ይባላል። ስለዚህ፥ሰንበትወይምሰባትከሚሉት መጠሪያዎች ይልቅ፤ሰብቤትየሚለው መጠሪያ፥ ለጥንታዊው እና ለስርዎ ቃሉ የቀረበ ነው።
ሰንበት፡ ሰምበት፣ ሰብበት፣ ሰብ ቤት፣ ሳባ ቤት፣ ሰባት...
ሰንበትየሚለው ቃል ምንጭ፥ሰብእናቤትየሚሉ ሁለት ቃላት ናቸው።
ከሌሎች ተመሳሳይ ቃላት አመሠራረት ጋር ለማመሳከር ያህል፥ እነዚህን ሁለት ቃላት እናያለ፥
አቤትእናእመትየሚሉ ቃላት ሲተነተኑ፥አብ ቤት እና እማ ቤት ሁነው እናገኛቸዋለን።አብአባት ሲሆንቤትደግሞ ልጅ ማለት ነው።አቤትማለት የአብ ልጅ፣ የአብ ወገን፣ የአምላክ ወገን... ማለት መሆኑን እንረዳለን።
እማ እናት ማለት ሲሆን፤ቤት እንዲሁ ልጅ ማለት ነው።እመትማለት ደግሞእመቤትማለት ሁኖየእማ ልጅየእናት ወገን ማለት ነው።
ሰባትማለት ደግሞሳባእናቤትሁኖሰብዓ ቤትነው።
ሰብዓማለት ሰው፣ ሳባዊ፣ ኢትዮጵያዊ... ማለት ሆኖቤትደግሞ ልጅ፣ ወገን... ማለት ነው።
ስለዚህሰንበትማለት፣ ሰባት ሁኖ፣ የሰው ልጅ፣ የሳባ ልጅ ማለት ሲሆን፥ በሌላ አገላለጽ፥ ኢትዮጵያዊ፥ የሚሉ ፍችዎችን የያዘ ነው።
ሰንበትየሚለው ስም
ሰብ የሚለው ስም፥ ሦስት ፍችዎችን የያዘ ነው።
የመጀመሪያው፥ ሰው ማለት ይሆንና፤ ሁሉንም ያዳም ዘር፥ ለመግለጽ ያገለግላል።
ሁለተኛው ደግሞ፥ሳባማለት ሁኖ፥ የኩሽ ልጅን ለመግለጽ ያገለግላል። ኢትዮጵያውያን፥ በኩሽ፥ ኩሻውያን (Cushitic) እንደሚባሉት፤ በሳባም፥ ሳባውያን (Sabbian) ይባላሉ።ሰበን’ (Seven/7) የሚለው የእንግሊዝኛው የቁጥር ስምም የመጣው፤ ከዚሁ፥ (Sabbian / ሳቢያን) ከሚለው ስም ነው። ዕብራውያን የኢትዮጵያውያንተክተውታል፥አብአቭክታብ ክታቭልብልቭ’ ... [‘ላቭየሚለው ቃል፥ልቭከሚለው እብራይስጥ ሁኖ፥ልቭ/Loveየሚለው ደግሞልብከሚለው የኢትዮጵያውያን ቃል መሆኑን ልብ ልንል ይገባል።]
ሦስተኛውና ብዙም ትኩርት ያልተሰጠው ፍች፤ ሰብ ማለት ሰው፥ ወይም የሰው ማለት ሁኖ የራስ ያልሆነን ነገር ለመግለጽ ያገለግላል። ይህም የሰው አገር፣ የሰው ገንዘብ፣ የሰው ልጅ ... ጌታ ኢየሱስም፥ እራሱን የሰው ልጅ እያለ የገለጸበት ምክንያት፤ እነዚህን ሦስቱንም መልክቶች የሚያስተላልፍ መጠሪያ ሆኖ ስለተገኘ ነው። አንድም የአዳም ትውልድ የሆነ፤ እንደማንኛውም ሰው መሆኑን። አንድም፥ የትውልድ ሐረጉ፥ የኩሽ ልጅ፥ የሳባ ልጅ መሆኑን። አንድም ደግሞ፥ የእነሱ ልጅ ያልሆነ፤ የሌላ አገር ሰው፤ የሌላ አገር ልጅ፤ የሰው ልጅ መሆኑን ሲነግራቸው ነው።
ቤት የሚለው ስም፥ ቢያንስ ሁለት ፍችዎችን የያዘ ነው።
የመጀመሪያው፥ መግቢያ፣ መቀመጫ፣ ማደሪያ፣ መኖሪያ... ህንጻ ማለት ነው። የእከሌ ቤት፣ የአብርሃም ቤት፣ የእግዚአብሔር ቤት ...
ሁለተኛው ደግሞ ልጅ፣ ዘመድ፣ ወገን ... ይህም የያቆብ ቤት (ቤተ እስራኤል) የሳባ ቤት ( ቤተ ሳባ/ ቤተሰብ) ...
ሰንበትእንግዲህ ሰብ ቤት ሁኖ፤ የሳባ ወገን ወይም ቤተ ሳባ/ ቤተሰብ ማለት ነው።
የሰንበት ጌታ
የሰው ልጅ የሰንበት ጌታ ነውና።” (ማቴ 12: 8) ጌታ ማለት ባለቤት፣ አለቃ፣ ገዥ... የካህናት አለቃ፥ ካህን፤ የነገሥታት ንጉሥ...
ጌታ ኢየሱስ፥ በሳብያውያን ዘንድ ይከበራል፣ ይፈራል፣ ይወደዳል፣ ይወደሳል፣ ይነግሣል፣ ይመሰገናል...
እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት፤ ሐሤትን እናድርግ፥ በእርስዋም ደስ ይበለን።(መዝ 11824 ) እንዲል፥ ሰንበት እግዚአብሔር የሠራባት ቀን ብቻ ሳይሆን፥ እግዚአብሔር የሠራትም ቀን ናት። አንድ ሰው ለሠራው ነገር፥ ለዚያ ጌታው ነው፤ ማለትም የዚያ ነገር ባለቤት ነው። እናም ጌታ ኢየሱስ፥ ሰንበትን የሠራት ስለሆነ፤ የሰው ልጅ፥ የሰንበት ጌታ ተባለ።
ሰንበት ስለሰው
ሰንበት ስለሰው ተፈጠረ እንጅ፥ ሰው ስለሰንበት አልትፈጠረም
ሰንበት ለሰው ተፈጠ (ሰንበት- ትእዛዝ፣ ሕግ፣ ቃልኪዳን፣ ሥርዓት፣ መንግሥት... ነው።) ሰው የሚድንበት መንገድ፥ ለሰው ልጆች ሲባል ተመሰረተ... ቅዱስ ዳዊት ሰንበትን ሲገልጽ፥ እግዚአብሔር ማዳንን የሠራባት ቀን ብቻ ሳይል፤ ቀኗን ራሷን፥ የሠራት ሲል ገልጿታል፥ እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት... (መዝ 11824)እግዚአብሔር የሠራት ቀንየተባለች፤ የሰንበት ቀን ናት። ቅዱስ ጳውሎስ እንደነገረን፥ የሰንበት ቀን ደግሞ የነገር ጥላ ስለሆነ፥ አካሉ ክርስቶስ ነው። በክርስቶስ ደግሞ የተገኘው፤ የዘላለም ድኅነት ነው። የመዳን ቀን ደግሞ ዛሬ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር ለኛ የሠራት ሰንበት፤ ይች የመዳን ቀን፥ ዛሬ፤ አሁን... ትባላለች።
            የሰው ልጅ (ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ) የሕጉ ሠሪ፣ አስከባሪ እንጅ ሕጉ አይገዛውም። አንድ ንጉሥ ህዝቡን የሚገዛበት ሕግ ያወጣል፥ ሕግ ግን ንጉሡን አይገዛውም።  ግብር የሚያስወጣ መንግሥት (ንጉሥ) የግብር አወጣጥን ሕግ ያወጣል፣ ያፀድቃል፣ ያስፈጽማል፣ ያስተገብራል እንጅ፤ ሕግ ግን በገዥው ላይ ተፈጻሚነት የለውም። ምክንያቱም ግብር አስከፋይ ግብር አይከፍልምና። ለማንስ ይከፍላል። ዛሬ ዛሬ ነገራችን ግራ ስለሆነ ሕዝብ መሪውን እንዲመርጥ ይጠበቃል፥ መሪም ግብር እንዲከፍል ይጠበቃል። ቀድሞ  በመጽሐፍ ቅዱሳዊው ሥርዓት እንዲህ አልነበረም። መሪን እግዚአብሔር ይመርጣል፥ መሪም ሕዝቡን ይመርጣል። መሪውና ልጆቹም ከግብር ነጻ ናቸው፥ እነዲህ ተብሎ እንደተጻፈ፥ወደ ቅፍርናሆምም በመጡ ጊዜ ግብር የሚቀበሉ ሰዎች ወደ ጴጥሮስ ቀረቡና፦ መምህራችሁ ሁለቱን ዲናር አይገብርምን? አሉት። አዎን ይገብራል አለ። ወደ ቤትም በገባ ጊዜ ኢየሱስ አስቀድሞ፦ ስምዖን ሆይ፥ ምን ይመስልሃል? የምድር ነገሥታት ቀረጥና ግብር ከማን ይቀበላሉ? ከልጆቻቸውን ወይስ ከእንግዶች? አለው። ጴጥሮስም፦ ከእንግዶች ባለው ጊዜ ኢየሱስ፦ እንኪያስ ልጆቻቸው ነጻ ናቸው ነገር ግን እንዳናሰናክላቸው፥ ወደ ባሕር ሂድና መቃጥን ጣል፥ መጀመሪያም የሚወጣውን ዓሣ ውሰድና አፉን ስትከፍት እስታቴር ታገኛለህ፤ ያን ወስደህ ስለ እኔና ስለ አንተ ስጣቸው አለው።” (ማቴ 7125-27)
ሕገ መንግሥት፥ ህዝብ የሚተዳደርበት እንጅ ገዥ የሚፈረጅበት አይደለም፥ እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ፥ሁሉን ከእግሩ በታች አስገዝቶአልና። ነገር ግን፦ ሁሉ ተገዝቶአል ሲል፥ ሁሉን ካስገዛለት በቀር መሆኑ ግልጥ ነው።(1 ቆሮ 1527)
ሰንበትበሚለው መጠሪያ ስም፥ የመሲሁን ማንነት የሚያሳዩ ምስጢራትን እና ፍቻቸውን የሚጠቁም መልክትንም በውስጡ የያዘ ነው።
ሴምማለት ስም፣ መጠሪያ፣ መታወቂያ... ማለት ነው።
ሰንበትሴማዊ ማለት፥ ስማዊ፣ የተሰየመበት፣ የሚጠራበት፣ የሚታወቅበት፣ የሚገለጽበት፣ ስም ያለው... ማለት ነው።
ሰንበት በተለያዩ ስሞች ይጠራል፥
አንዱና የመጀመሪያው፥ ቀዳሚ ሰንበት፥ ወይም በአጭሩ፥ቅዳሜነው። ቀዳሚ ወይም ቅዳሜ የሚለው መጠሪያ የተጨመረለት ከእሁድ ሰንበት መምጣት ጀምሮ ነው። ከዚያ በፊት የነበረው ቀን መጠሪያ ሰባት (ሰንበት) ብቻ እንጅ፥ ቀዳሚ የሚል ቅጥያ አልነበረውም። ለምሳሌ፥ ዳግማዊ ምኒልክ እስኪመጡ ድረስ፤ የመጀመሪያው ምኒልክ፥ምኒልክእንጅ፥ ቀዳማዊ ምኒልክ አይባሉም ነበር። ዳግማዊ ምኒልክ ከነገሡ በኋላ፥ የመጀመሪያውን ምኒልክ፥ ከዳግማዊው ለመለየት ሲባል፥ ቀዳማዊ የሚል ቅጥያ ተጨመረለት።
ሁለተኛው ሰንበት ደግሞ እሁድሰንበት ነው። የእሁድ ሰንበት እሁድ የተባለው፤ በሳምንቱ በመጀመሪያው ቀን ስለሆነና ከሰባተኛው ቀን ሰንበት ለይቶ ለመግለጽ ነው።እሁድማለትም አሐደ ከሚለው ሁኖ፥ የመጀመሪያ ማለት ነው። ያም ሆነ ይህ፤ እሁድ የሰንበት አንዱ መጠሪያ ሁኖ ያገለግላል።
የሰባተኛው ቀን መጠሪያ መሆናቸው በግልጽ የማይታወቁ፤ ብዙ የሰንበት መጠሪያዎችን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እናገኛለን።
ከነዚህ ውስጥየመዳን ቀንየሚለው ነው።ድኅነትበሰንበት ነው። ስለዚህ፥ በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ መዳንም ቀን ረዳሁህ ይላልና፤ እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ እነሆ፥ መዳን ቀን አሁን ነው።” (2 ቆሮ 6: 2) ያለው፥ ሰንበትን እንደሆነ፥ ልንገነዘብ ይገባል። ከዚሁ ጥቅስ ሳንወጣ፥በተወደደው ሰዓት...’ ጠራሁህ ይላል። እንግዲህ ይህየተወደደ ሰዓትም ሰንበት ነው ማለት ነው። ቀጥሎም፥የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፥ይለናል። ስለዚህ ሰንበትምአሁንነው፥ ማለት ነው።  
ሌላው፥ ሰንበትን የገለጽበት ስም፥የእረፍት ቀንበሚለው ነው። እግዚአብሔር ዕረፍት ያገኘበትን ሥራ የሥራው፥ በሰባተኛው ቀን ነው። በሰባተኛው ቀን በሠራው ሥራ አረፈ፥ ይላልና፥ እግዚአብሔርም የሠራውን ሥራ በሰባተኛው ቀን ፈጸመ በሰባተኛውም ቀን ከሠራው ሥራ ሁሉ ዐረፈ” (ዘፍ 2: 2)
ይህ ጥቅስ የሚነግረን፥ እግዚአብሔር በሰባተኛው ቀን እንደሠራ፥ የሠራው ሥራም እረፍትን የሰጠው መሆኑን ነው። ይህ ሥራ፥ አምላክ ሰውን ለማዳን ያደረገው፥ ጠቅላላው ጉዞ፤ በሙሉው የመጽሐፍ ቅዱስ የተመዘገበው ስለሆነ፥ በአንድ ቃል፥ ወይም ዓረፍተ ነገር ሊገለጽ አይችልም።
ለቃለ እግዚአብሔር ልባቸውን ላልከፈቱ፤ በልባቸው ለሚስቱና፤ መንገዱን ላላወቁ፤ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት፥ ወደ እግዚአብሔር ሰንበት እንደማይገቡ፥ እንዲህ ሲል ገልጾታል፥እንዲሁ፦ ወደ ዕረፍቴ አይገቡም ብዬ በቍጣዬ ማልሁ።” (ዕብ 311)
2.   የሰንበት ጊዜያዊ ባሕሪ፥ (ሰንበት፥ መቸ ነው? ቅዳሜ፣ ዕሁድ ወይስ ሌላ()...?)
ሰንበት ጊዜያዊማለት፥ በጊዜ፣ በሰዓት፣ በቀን፣ በዓመት... የሚገለጽ ማለት ነው።  ይህም፥ ቅዳሜ፣ እሁድ፣ ሁሉም ቀን፣ ዛሬ፣ አሁን...
ሰንበት ጊዜሲገለጽ፥ ሰባተኛ ቀን ማለት ነው።ሰንበትበኦሪት ቅዳሜ ነው፤ በአዲስ ኪዳን ደግሞ እሁድም ነው። በኢትዮጵያ ደግሞ ቅዳሜም ሰንበት፥ እሁድም ሰንበት ናቸው።
ቅዳሜ (ሰባተኛው ቀን)
እግዚአብሔር አምላክ ሰውን ለማዳን ለሚሠራው ሥራ የለየው ወይም የቀደሰው ቀን ነው። ያም ቀን፥ የእግዚአብሔር እረፍት የተባለው ቀን ነው። ሰባት (ሰንበት) የተባለውም፥ የሳምንቱ የመጨረሻ ወይም ሰባተኛ ቀን በመሆኑ ነው። ቅዳሜ በመባሉ መጀመሪያ የሚል መጠሪያ ሲኖረው፥ ሰባተኛ በመሆኑም የመጨረሻው ቀን ተብሎ ይጠራል። ሁለቱንም ሰንበታት ለሚያከብሩ፥ ሰንበት፥ የሚለው መጠሪያ፥ መጀመሪያና መጨረሻ ወይም አልፋና ኦሜጋ የሚል ፍችን በውስጡ ይዞ እናገኘዋለን።
እሁድ (መጀመሪያ ቀን)
የእሁድ ሰንበት፥ እግዚአብሔር ለሰዎች ከሰጠው ቀናት፥ ሰዎች ለእግዚአብሔር የሰጡት ቀን ነው። እግዚአብሔር የማዳን ሥራውን በምድር ላይ ከተፈጸመ በኋላ፥ ሰው ለእግዚአብሔር የሰጠው ቀን በመሆኑ፥ የእሁድን ሰንበትነት የሚያስረዳ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥቅስ ወይም ማስረጃ የለም።
የሰንበት ቀን መቸ እንደሆነ ከመመለሳችን በፊት፥ የቀናትን አፈጣጠር እና ልዩነት እንመረምራለን።ጊዜከእግዚአብሔር ፍጥረታት አንዱ ነው። ይህም ማለት ጊዜ ያልንበረበት ጊዜ አለ። ማለትም፥ጊዜበአንድ ወቅት አልነበረም፤ በሌላ ወቅት ደግሞ ኖረ። ጊዜን በሁለት ከፍለን ማየት እንችላለን። ፀሃይ እና ጨረቃ ከመፈጠራቸው በፊት የነበረን ጊዜ እና ፀሃይና ጨረቃ ከተፈጠሩ ብኋላ ያለው ጊዜ።
የመጀመ ሦስት ቀናት፥
በፍጥረት መጽሐፍ፥ በምዕራፍ አንድ እንደምናገኘው፤ ፀሃይ እና ጨረቃ የተፈጠሩት በአራተኛው ቀን ነው።እግዚአብሔርም ሁለት ታላላቆች ብርሃናትን አደረገ፤ ትልቁ ብርሃን በቀን እንዲሠለጥን፥ ትንሹም ብርሃን በሌሊት እንዲሰለጥን፤ ከዋክብትንም ደግሞ አደረገ።” (ዘፍ116)
በመጀመሪያዎቹ ሦስት የፍጥረት ቀናት የነበሩት ቀናት፥ የሚለኩበት ብርሃን፥ ዛሬ ጊዜን ከምንለካበት የተለየ በመሆኑ፥ ይህን ያህል ሰዓት ነው፥ ብሎ መናገር አይቻል። ይህ ማለት ለሰው እንደ ሺህ ዓመት፥ ለእግዚአብሔር ደግሞ እንደ ሰከንድ፤ ወይም ደግሞ ለሰው እንደሰከንድ፥ ለእግዚአብሔር ደግሞ፥ እንደ ሺሕ ዓመት ሊሆን ይችላል።
የሚቀጥሉት ሦስት ቀናት፥
ከዚያ ቀጥሎ ያሉት ቀናት፥ በፀሃይ መውጣትና መጥለቅ በመለካት ማወቅ ይቻላል። ይህም እንደሰው አተያይ እንጅ እንደ እግዚአብሔር ከሆነ ቅጽበት የማይሞሉ ሊሆኑ ይችላሉ።
ሰባተኛው ቀን፥
ከሦስቱ የፀሃይ ቀናት ቀጥሎ የሚቀረው፥ ሰባተኛው ወይም የመጨረሻው ቀን ነው። ሰባተኛው ቀን እንደ እግዚአብሔር ቀኑ ሲጀምር ይታያል፥ መጨረሻ ግን የለውም። በእግዚአብሔር ዘንድ ስምንተኛ የሚባል ቀን አልተነገረንም። ስለዚህ ዛሬ የምኖረው ሰባተኛውን ቀን ነው። እግዚአብሔር በዚህ ቀን የመፍጠር ሥራ አልሠራም፤ ሆኖም ግን ሥራ አልሠራም ማለት ሳይሆን፤ የሠራው ሥራ በቀጥታው አልተገለጸም።
1.1.1.   የቅዳሜ ሰንበት፥
እግዚአብሔርም የሠራውን ሥራ ሰባተኛው ቀን ፈጸመ፤ በሰባተኛውም ቀን ከሠራው ሥራ ሁሉ ዐረፈ።” (ዘፍ 22)
ሰባተኛ ቀን፥ የእሁድ ሰንበት እስኪታወቅ ድረስ፥ ሰንበት (ሰባተኛ) ተብሎ እንጅ፥ ቀዳሚ ሰንበት (ቅዳሜ) ተብሎ አይጠራም ነበር። ይህ ቀን፥ እግዚአብሔር ሰውን የማዳን ሥራውን ሊሠራበት፥ ከሌሎች የፍጥረት ቀናት፥ ለይቶና ቀድሶ፤ ያስቀመጠው ቀን ነው። ይህም የኢየሱስ ምሳሌ ሁኖ፥ ከእግዚአብሔር ለሰው፥ የድኅነት ምክንያት ሁኖ መቅረቡን እናይበታለን።
የቅዳሜን ሰንበት፤ የኦሪት ሰንበት ልንለው እንችላለን። ኦሪታውያን፥ በተለይም አይሁድ፥ አሁንም የሚጠብቁት እና የሚያከብሩት ቀን ነው። ለክርስቲያኖች ደግሞ፤ ሰንበት የሆነው ኢየሱስ ስለመጣ የሚጠብቁት አይደለም። ሊያከብሩትና ሊቀድሱት ግን ይገባለ። ከአስርቱ ትእዛዛት ዘጠኙን፥ ጌታ ኢየሱስ፥ በተለያየ መንገድ እንዲጠበቁ ሲያዝዛቸው፥ሰንበቴን ጠብቁየሚለውን ግን፤ የትም ቦት ሳያነሳ አልፎታል። ይህም የሚያሳየን፤ ሲጠበቅ የነበረው ሰንበት፥ የእግዚአብሔርን መንግሥት ይዞ ስለመጣ ነው።
1.1.2.   የእሁድ ሰንበት፥
የመጀመሪያ፥ የቅዳሜን ሰንበት፥ ቀዳሚ ያሰኘው፥ በአዲስ ኪዳን የእሁድ ሰንበት መምጣት ነው። ይህ ቀን፤ ሰው ከእግዚአብሔር ለአገኘው የድኅነት ሥራ ማሳያ፥ ከእግዚአብሔር ከተሰጠው ሰባት ቅናት፤ የቀናትን በኩር፥ የሳምንቱን መጀመሪያ፥ ለእግዚአብሔር የሰጠው ነው። በኢየሱስ ምሳሌነቱም፥ ኢየሰስ፤ ሰውን ከእግዚአብሔር ለማስታረቅ፤ ከመቤታችን የተወለደ በኩርን፥ መሰዋእት ሆኖ መቅረቡን፥ እንዘክራለን።
አይሁድ የቅዳሜን ሰንበት ሲያከብሩ፥ ክርስትቲያኖች ደግሞ የእሁድን ሰንበት ያከብራሉ። ኦርታውያን፥ አይሁድ የእሁድን ሰንበት የማያከብሩት፥ ክርስቶስን ስላላወቁ ነው፤ ወንጌላውያን፥ ክርስቲያኖች የቅዳሜን ሰንበት የማያከብሩት፥ በኦሪት ዘመን እግዚአብሔርን ስላላወቁ ነው።
ከነዚህ፥ ከሁለቱ ለየት ባለ፥ የኢትዮጵያ ክርስትና አምልኮን ስናይ ደግሞ፤ የቅዳሜ ሰንበትንም የእሁድ ሰንበትም ታከብራለች። የቅዳሜን ሰንበት የምታከብረው፥ እግዚአብሔርን እና ትእዛዛቱን በብሉይ ኪዳን ዘመንም ስለምታውቅ ነው። የእሁድን ሰንበት የምታከብረውም፥ በአዲስ ኪዳን ዘመን፤ ጌታ ኢየሱስን እና የእግዚአብሔርን መንግሥት ስለምታውቅ ነው። ዛሬ፥ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን፥ ሰንበታትን፥ ትቀድሳለችና ታከብራለች እንጅ፥ሰንበትን ትጠብቃለችተብሎ ፈጽሞ አይገለጽም።
1.1.3.   ዕረፍትህ
አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም። (ኢሳ 40: 28) “... በሰባተኛውም ቀን ከሠራው ሥራ ሁሉ ዐረፈ።” (ዘፍ 22)
የእስራኤልም ልጆች ለልጅ ልጃቸው ለዘላለም ቃል ኪዳን በሰንበት ያርፉ ዘንድ ሰንበትን ይጠብቁ” (ዘጸ 31: 16)
ከላይ የቀረበው ጥቅስ የሚያስገነዝበን፥ ሰንበት የዘላለም እረፍትን የሚያስገኝ ጉዳይ መሆኑን ነው።
በሳባተኛ ቀን አረፈ..” ማለት ሥራ አልሠራም ማለት ሳይሆን፥ ለእኛ ዘላለማዊ እረፍትን ያስገኘልንን ሥራ የሠራባት፤ ለኛ የሞተበት... ማለት ነው። ኢየሱስ ግን፦ አባቴ እስከ ዛሬ ይሠራል እኔም ደግሞ እሠራለሁ ብሎ መለሰላቸው።” (ዮሐ 5: 17) እግዚአብሔር አብ፥ ዓለሙን እና በውስጡ የያዘውን በስድስት ቀን የፈጠረና፥ በሰባተኛው ቀን ሥራውን የፈጸመ፤ በሰባተኛው ቀን ያረፈ ከሆነ፤ እንዴት እስከዛሬ ይሠራል? የእግዚአብሔር እረፍትስ፥ ሰዎች በሥራ የዛለ አካላቸውን፥ በመቀመጥ ወይም በመተኛት እንደምናሳርፈው ነው? ካልሆነ፥ ከሰዎች እረፍት የተለየ የሚያደርገው ምንድን ነው?
የእግዚአብሔር እረፍት፥ ሥራ አለመስራት እንዳልሆነ እና እግዚአብሔር ሥራ ያልሠራባቸው ቀናት እንደሌሉ፥አባቴ እስከ ዛሬ ይሠራል እኔም ደግሞ እሠራለሁ በሚለው እንረዳለን።
ሞት እረፈት ይባላል። እግዚአብሔር ወልድ ሲሞት፥ ሰውን የማዳንን ሥራ እየሠራ ነው። እግዚአብሔር በሰባተኛው ቀን የሠራው፥ አዳምን ማዳን ነው። ትልልቅ አባቶች ሲሞቱ፥ከዚህ ዓለም ድካም አረፉይባላል።
አዳምን ማዳን እረፍትን የሚያስገኝ ሥራ ስለሆነ፥ በዚህ ሥራው እግዚአብሔር አረፈ።
ከላይ ለቀረቡት ጥያቄዋች፥ አጥጋቢ መልስ ለማግኘት፥ በቅድሚያ ቀጥለው የቀረቡ ሁለት ነጥቦችን፥ በጥልቀት መመርመር እና መረዳት ያስፈልጋል።
የመጀመሪያው፥ ‘... ሊሠራ ያሰበውን ሥራ በሰባተኛው ቀን ፈጸመ፥ የሚለው እና፤ ሁለተኛው፥ ‘... በሰባተኛው ቀን አረፈ  የሚሉትን አባባሎች፥ ትክክለኞችን መልእክቶች ልንረዳቸው ይገባል።
ፈጸመየሚለውን የመጀመሪያ ነጥብ ስናይ፥ እግዚአብሔር አምላክ ሥራውን የጨረሰው በሰባተኛ ቀን መሆኑን ነው። በሰባተኛው ቀን የሠራው ሥራ ምንድን ነው? ካልን፤ ሰውን ከዘለዓለም ሞት ወደ ዘለዓለም ሕይወት የማምጣት ሥራ ነው። ይህም ሥራ እስከዛሬ የቀጠለ እንጅ፤ የተፈጸመና ያበቃ አይደለም። ስለሆነም ይህ፥ የእግዚአብሔር ሰባተኛ ቀን፥ ቅዳሜ፥ ዛሬም የምንኖርበት የእግዚአብሔር ሰንበት ነው።
በሰባተኛው ቀን አረፈ ማለት ሥራ አልሠራም፤ ሥራ መስራትን አቆመ ማለት እንዳልሆነ አጽንዖ ሰጥተን ልንመረምረውና ልንረዳው ይገባል።
ሰባተኛው ቀን፥ እግዚአብሔር አምላክ፥ ዓለምን እና በውስጡ ያለውን፥ ይሁን ብሎ ከፈጠረበት ጥበቡ የላቀውን፤ ሰው ሁኖ ሰውን ያዳነበትን ጥበብን ያሳየበት እና እረፍት ያገኘበት ቀን ነው። በሠራው ሥራ አረፈ እንጅ፤ ሥራውን ጨርሶ፥ አእምሮውን እና አካሉን እንደሰው አሳረፈ፥ ማለት እንዳልሆነ ልንገነዘብ ይገባል።
የእግዚአብሔር እረፍት የተባለው፥ ለሰው የተፈጠረው አዲስ ሥርዓትና ህግ፤ በልጁ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የተመሰረተው፤ የክርስትና ህይወት ነው። ይህን የበለጠ ግልጽ ለማድረግ፤ የቅዱስ ጳውሎስን ወደ ዕብራውያን በላከው መልእክት፤ የገለጸውን ማቅረብ ያስፈልጋል። ቅዱስ ጳውሎስ፥ በእምነት ወደ ሰንበት እና የእግዚአብሔር መንግሥት መግባትን፥ ወደ እረፍቴ በማለት ገልጾታል፥ሥራው ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ምንም እንኳ ቢፈጸም፦ እንዲህ፦ ወደ ዕረፍቴ አይገቡም ብዬ በቁጣዬ ማልሁ እንዳለ፥ እኛስ ያመንን ወደ ዕረፍቱ እንገባለን።” (ዕብ 43)
በቅንነት፥ በመታዘዝ ወደ ሰንበት፤ እንደሚገባም ሲያበረታታን፥ እንግዲህ እንደዚያ እንደ አለመታዘዝ ምሳሌ ማንም እንዳይወድቅ ወደዚያ ዕረፍት ለመግባት እንትጋ።” (ዕብ 411)
ቅዱስ ዳዊት፤ ከርሱ አምስት መቶ ዓመት በፊት፥ ስለነበሩ የእስራኤላውያን አባቶችና፥ አንድ ሺሕ ዓመት ከእርሱ በኋላ ስለመጣው፥ ስለ ክርስቶስ የተናገረውን፥ ቅዱስ ጳውሎስ ሲያብራራ፥ ድምፁን ብትሰሙት ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ በፊት እንደ ተባለ፥ ይህን ከሚያህል ዘመን በኋላ በዳዊት ሲናገር፦ ዛሬ ብሎ አንድ ቀን እንደ ገና ይቀጥራል። ኢያሱ አሳርፎአቸው ኖሮ ቢሆንስ፥ ከዚያ በኋላ ስለ ሌላ ቀን ባልተናገረ ነበር እንግዲያስ ሰንበት ዕረፍት ለእግዚአብሔር ሕዝብ ቀርቶላቸዋል። ወደ ዕረፍቱ የገባ፥ እግዚአብሔር ከሥራው እንዳረፈ፥ እርሱ ደግሞ ከሥራው አርፎአልና።” (ዕብ 4: 7-11) ይህም የሚያስረዳን፥ እስራኤላውያን የዘላለም እረፍትን የሚያገኙት በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በመግባት እንጅ፤ በኢያሱ መሪነት ወደ ከነዓን ምድር ስለገቡ እንዳልሆነ ለማስገንዘብ ነው። እዚህ ላይ ለማስተላለፍ የተፈለገው ቁም ነገር፤ የእግዚአብሔር ሰንበት፣ የእግዚአብሔር እረፍት፣ የአምላክ ሰው መሆን እና የእግዚአብሔር መንግሥት የተባሉ ጉዳዮች፥ ሁሉም የኢየሱስ ክርስቶስን የማዳን ሥራ የሚያንጽባርቁ ክንዋኔዎች እና እሳቤዎች ናቸው።
አይሁድ ሰንበትን እንዳልተቀበሉና፤ ወደ ዘላለማዊ ድህነት፥ ወደ ክርስትና እንዳልገቡ ይገልጻል፥ እንዲሁ፦ ወደ ዕረፍቴ አይገቡም ብዬ በቍጣዬ ማልሁ።” ~ my rest (ዕብ 3: 11)
የሰንበት ዕረፍት ለአመኑ፥ ክርስቶስን ለተቀበሉ እንደሆነ በዚህ እንረዳለን፥ሥራው ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ምንም እንኳ ቢፈጸም፦ እንዲህ፦ ወደ ዕረፍቴ አይገቡም ብዬ በቁጣዬ ማልሁ እንዳለ፥ እኛስ ያመንን ወደ ዕረፍቱ እንገባለን።(ዕብ 43)
የጌታ እረፍት፥ ሞቱን ብቻ ሳይሆን ትንሳኤውንም የሚጨምር መሆኑን ሲያሳስብ፥ ንጉሥ ዳዊት፥ እንደዚህ ይላል፥ አቤቱ፥ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦት።(መዝ 132: 8) ታቦት ሲጠቀስ፥ አስርቱ ትእዛዛት አብረው ይታወሳሉ። አስርቱ ትእዛዛት ሲታወሱ ደግሞ ከአስሩ አንዱ የሆነው ትእዛዝ፥ ሰንበትን ጠብቅ፥ የሚለው ይወሳል። ስለዚህ፥ወደ እረፍትካለ፥ የእግዚአብሔር ዕረፍት ሰንበትን፥ ማለቱ ነው።
የሰንበትን እረፍት አስገኝነት የሚያሳዩ ተጨማሪ ጥቅሶች፥
1.     አሁንም፥ አቤቱ አምላክ ሆይ፥ ከኃይልህ ታቦት ጋር ወደ ዕረፍትህ ተነሣ፤ አቤቱ አምላክ ሆይ፥ ካህናትህ ደኅንነትን ይልበሱ ቅዱሳንህም ደስታ ደስ ይበላቸው።~ thy resting place (ዜና 6: 41)
2.     ቅዱሳን ልብ በአንተ ስራ ስለ ዐረፈ ወንድሜ ሆይ፥ በፍቅርህ ብዙ ደስታንና መጽናናትን አግኝቼአለሁና።~ refreshed (ፊል 1: 7)
3.     አምላካችሁ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ዕረፍት ርስት እስከ ዛሬ ድረስ አልገባችሁምና።~ the rest and to the inheritance (ዘዳ 12: 9)
4.     በዚህ ጊዜ ቸል ብትዪ ዕረፍት መዳን ለአይሁድ ከሌላ ስፍራ ይሆንላቸዋል፥ አንቺና የአባትሽ ቤት ግን ትጠፋላችሁ፤ ደግሞስ ወደ መንግሥት የመጣሽው እንደዚህ ላለው ጊዜ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?” ~ deliverance (አስ 4: 14)
5.     በራሳችን ላይ ሰውን አስረገጥኸን፤ በእሳትና በውኃ መካከል አለፍን፥ ወደ ዕረፍት አወጣኸን።~a wealthy place (መዝ 66: 12)
6.     እንግዲህ እንደዚያ እንደ አለመታዘዝ ምሳሌ ማንም እንዳይወድቅ ወደዚያ ዕረፍት ለመግባት እንትጋ።(ዕብ 411)
1.1.4.   ዛሬ፥
ኢየሱስ ግን፦ አባቴ እስከ ዛሬ ይሠራል እኔም ደግሞ እሠራለሁ ብሎ መለሰላቸው።” (ዮሐ 5: 17)  አይሁድ፥ ሰንበትን ሽረሃል፥ ብለው ላቀረቡበት ወቀሳ፤ የሰጣቸው ምላሽ ነው።
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ከሱ ጋር ለተሰቀለውና የኢየሱስን መሲሕነት ለአመነው አመጸኛ ሰው፥ኢየሱስም፦ እውነት እልሃለሁ፥ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ አለው” (ሉቃ 2343) (ዮሐ 5: 17) የብሉይ እና የአዲስ ኪዳናት ያሉት፥ በእግዚአብሔር፥ በአንድ ቀን ውስጥ መሆናቸውን ቀጥሎ በቀረበው ጥቅስ እንረዳለን።ትእዛዙን እናገራለሁ፤ እግዚአብሔር አለኝ፦ አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወለድሁህ።” (መዝ 2: 7) ቅዱስ ዳዊት ከዘመኑ አንድ ሺሕ ዓመት ቀድሞ፥ ስለ ጌታ እየሱስ መወለድ ዛሬ በማለት ገልጾታ። በጌታሺሕ ዓመት እንደ አንድ ቀንነውና።  በሌላ አገላለጽ፥ ንጉሥ ዳዊት እና ጌታ ኢየሱስ የነበሩት በእግዚአብሔር ዘንድ፥ በአንድ ቀን ውስጥ ነው። ያም ቀን ሰባተኛው ቀን ወይም ሰንበት ነው። በእግዚአብሔር ዘንድ ሌላ ቀን አይጠበቅም። ሁሉም ዛሬ ነው።
ጌታ በሰንበት፥ ወደ ራብ ገብቶ ሲያነብ፥እርሱም፦ ዛሬ ይህ መጽሐፍ በጆሮአችሁ ተፈጸመ ይላቸው ጀመር።” (ሉቃ 421) ጌታ በምኩራብ ለአይሁድ ያነበበላቸው፥ ከመወለዱ፥ ከሰባት መቶ ዓመት በፊት ነብዩ ኢሳያስ፥ እንዲህ ብሎ የተናገረውን ነው፥የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና፤ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩትም ነጻነትን ለታሰሩትም መፈታትን እናገር ዘንድ ልኮኛል።” (ኢሳ 611) ጌታ ዛሬ ያለው፥ በእለቱ ለታደሙት አይሁዳውያን ብቻ አይደለም፤ ዛሬም፥ በየቀኑም የእግዚአብሔርን ቃል ለሚሰሙ ሁሉ እንጅ። [ኢየሱስ የሚለው ስም እና ኢሳያስ የሚለው ስም ፍቻቸውም ሆነ ስርዎ ቃላቱ አንድ መሆኑን ልንገነዘብ ይገባል።]
ቃለ እግዚአብሔር የሚያስፈልገን ሁልጊዜ መሆኑንና፤ የመዳን ቀን ዛሬ መሆኑን ለማሳውቅ፤ ከሁለት ሺሕ ዓመትም በኋላ... “የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን...” (ማቴ 6: 11) እያልን እንድንጸልይ አስተማረን። ምናልባትም፥ ከዛሬ ሁለት ሺሕ ዓመት በኋላ የሚመጣውም ትውልድ፥ ‘...ዛሬ ስጠን እያለ...’ ሁሉም ቀን በጌታ አንድ ቀን መሆኑን ይመሰክር ይሆናል።
ይህ ከሆነ፥ እያንዳንዱ ቀንሰንበትነው፥ ማለት እንችላለን። እግዚአብሔር ዛሬም፥ በእያንዳንዱ ቀንም፥ የማዳን ሥራውን ይሠራልና።
በእግዚአብሔር ዘንድ፥ አንድ ቀን እንደ ሺሕ ዓመት ነው፤ ሺሕ ዓመትም እንደ አንድ ቀን ማለት ነው” (2ጴጥ 38) እንዲል፥ ሰባተኛው ቀን፥ በእግዚአብሔር ዛሬ ነው። የሰንበት ቀን፥ ዛሬ እንጅ፥ ትላንት ወይም ነገ አይደለም። የእግዚአብሔር ሰባተኛ ቀን፥ ለሰው የተተወ ዛሬ ነው። የመዳን ቀን ዛሬ ነው...
ሰው በአመነበት እለት ይድናል፥ ጌታ ኢየሱስ አብሮት የተሰቀለውን፤ኢየሱስም፦ እውነት እልሃለሁ፥ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ አለው።” (ሉቃ 23 43) ከጌታ፥ ከርሱ ጋር የተሰቀለውን፥ ጌታ ከሐጢያቱ ነፃ እንዳወጣው፥ ሲያበስረው፥ ... ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ አለው።
በሰንበት ፈውስንና ድኅነትን ሲፈጽም ያዩ፥ሰንበትን ሻረብለው ሲከሱት፥ ኢየሱስ ግን፦ አባቴ እስከ ዛሬ ይሠራል እኔም ደግሞ እሠራለሁ ብሎ መለሰላቸው።” (ዮሐ 5: 17) ይህ ጥቅስ የሚያመለክተን፥ እግዚአብሔር፥ አዳም በኅጢያት ከወደቀበት ቀን ጀምሮ፥ አዳምን ወደቀደመ ክብሩ ለመመለስ፤ ከሚያደርገው ሥራ እንዳላቋረጠ ነው። የእግዚአብሔር እረፍት የተባለው ቀን፤ የማዳን ሥራን የሠራበት እንጅ፤ ሥራ ያቆበት ቀን አይደለም።
      ሰንበት ዛሬ መሆኑን ያሚያጸኑ ተጨማሪ ጥቅሶች፥
1.     ኢየሱስም፦ እርሱ ደግሞ የአብርሃም ልጅ ነውና ዛሬ ለዚህ ቤት መዳን ሆኖለታል፤” (ሉቃ 19: 9)
2.     ይህን ተስፋ እግዚአብሔር በሁለተኛው መዝሙር ደግሞ፦ አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወለድሁህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ ኢየሱስን አስነሥቶ ለእኛ ለልጆቻቸው ፈጽሞአልና።” (ሐዋ ሥራ 13: 33)
3.     የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን፤” (ማቴ 611)
4.     ኢየሱስ ግን፦ አባቴ እስከ ዛሬ ይሠራል እኔም ደግሞ እሠራለሁ ብሎ መለሰላቸው” (ዮሐ 517)
5.     በምድረ በዳ እንደ ተፈታተኑት እንዳስቈጡት ጊዜ፥ ዛሬ ድምፁን ብትሰሙ ልባችሁን አታጽኑ።” (መዝ 95: 8)
1.1.5.   አሁን
ተወደደ ሰዓት ሰማሁህ በመዳንም ቀን ረዳሁህ ይላልና፤ እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ እነሆ፥ የመዳን ቀን አሁን ነው” (2 ቆሮ 6: 2)
ሰንበት፥ ኢያንዳንዷ ቅጽበታዊ ጊዜ መሆኑን፥አሁንበሚለው ቃል ይገለጻል። ድኅነት፥ ቀጠሮ የማያስፈልገው፥ ጊዜ የማይሰጠው ድርጊት መሆኑን፥ የሚያስገነዝበን ሌላው ማስረጃ፤ ጌታ ወደሱ የቀረቡትን ድውያን ሁሉ፥ በቃልና በድርጊት፥ ወዲያውኑ ይፈውስ ነበር።
አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል (ኤፌ 2: 13) ለዚህም በኢትዮጵያ፥ ቁር [ሥጋዎ ደሙ] ቅዳሴ በእየለቱ አለ፤ ይህም ማለት ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርበን፥ ሥጋዎ ደሙን፥ በየቀኑ ትሰጣለች ማለት ነው።
እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ሙታን የእግዚአብሔርን ልጅ ድምፅ የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል እርሱም አሁን ነው፤ የሚሰሙትም በሕይወት ይኖራሉ” (ዮሐ 5: 25)
ሙታን...’ የተባሉት፥ እግዚአብሔርን ያላወቁ፤ ከአምላክ የራቁ፥ የመዳን ተስፋ ያልነበራቸውን አሕዛብን ነው። ...የእግዚአብሔር ልጅ ድምጽ...’ የተባለው፥ የኢየሱስ ክርስቶስን አስተምሮ እና መልክት ነው።የሚሰሙበት ሰዓት...’ የተባለው የሚድኑበት ጊዜን አሁን በማለት ገልጾታል። ከአሁን ጀምሮ ... ‘በህይወት ይኖራሉበማለት ያረጋግጣል። በእግዚአብሔር ዘንድ፥ ቀን ሁሉ አንድ ነው፤ እሱም ዛሬ ነው። በተለይም ከዛሬ ይልቅ፥ የጌታን ጊዜአሁንየሚለው ይገልጸዋል።
በጌታ ቀን ፍርድም፥ ፍትህም፣ ድኅነትም፣ ጽድቅም... ዛሬ ነው። በሌላ መልኩ፥ ያመነውዛሬበገነት ከኔ ጋር ትሆናለህ እንደተባለ፤ የካዱትምአሁንይፈረድባቸዋል። ንጉሥ በተገኘበት የተሰጠ ውሳኔ፤ ወዲያውኑ የሚፈጸምና ይግባኝ የሌለው ነው። ክርስቶስ ወንጌል ተመርተው፥ ወደ እግዚአብሔር የቀረቡበትን እና የዳኑበት ቀን፥ አሁን ተብሎ ተጠራ። ቀድሞ ጨለማ ነበራችሁና፥ አሁን ግን በጌታ ብርሃን ናችሁ፤እንዲል (ኤፌ 5: 8)
እግዚአብሔርን መቀበልና መዳንን አሁን እንደተባለ ሁሉ፤ ጌታን ሰምቶ ባለማመን፤ የሚሰጠውን የርግማንን ፍርድ ፍጻሜ፥ አሁን በማለት ጊዜውን፥ ገልጾታል፥ በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ ማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል” (ዮሐ 3: 18) ፍርድ አሁን ነው። ድኅነትም አሁን ነው። በእግዚአብሔር ዘንድ ሁሉ ነገር አሁን ነው። ትላንት ወይም ነገ የሚሉ ጊዚያት፤ ሰውን እንጅ እግዚአብሔርን አይወስኑትም። የዓለም መጀመሪያም፥ የዓለም መጨረሻም፤ በእግዚአብሔር ዘንድ አሁና እና ቅጽበታዊ ነው። አሁን ግን ወደ ላከኝ እሄዳለሁ ከእናንተም፦ ወዴት ትሄዳለህ? ብሎ የሚጠይቀኝ የለም።” (ዮሐ16: 5) አሁን ብሎ፤ እስከ ዕርገቱ ለአርባ ቀን ከነሱ ጋር ቆይቷል። እንዲሁም ሰንበትና የመዳን ቀን ቀጠሮ የማይሰጠው፤ ለነገ ይደር የማይባል ጉዳይ መሆኑን ሲነግረን፥ ... እነሆ፥ ተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ እነሆ፥ የመዳን ቀን አሁን ነው።” (2ቆሮ 6: 2) የመዳን ቀን በእግዚአብሔር ዘንድ፥ ነገ አይደለም፣ በአርባ ቀን አይደለም፣ በሰማኒያ ቀን አይደለም፣ በሰላሣ ዓመትም አይደለም... ነገር ግን ከዛሬም ባጠረ፤ ከሰዓትም ባነሰ፣ ቅጽበታዊ በሆነው ጊዜ፥አሁንነው።
1.1.6.   የጌታ ቀን
ከቀናት ሁሉ የከበረ፥ ከሰንበት የሚበልጥ፥ ምንም ዓይነት ቀን እንደሌለ የታወቀ ነው። ታላቅ የሆነ የተሰማም የጌታ ቀን ሳይመጣ ፀሐይ ወደ ጨለማ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣሉ።” (ሐዋ 2: 20) ይህ የጌታ ቀን የተባለው፥ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር አንድ የሆነበት ቀን ነው። ቀኑም ሰባተኛው፥ ወይም ሰንበት ነው።
ይህ ሰባተኛው ቀን፥ ሰንበት መሆኑን የምንገነዘበው፥ በምስጢራዊነቱ ነው፥ ጌታ ቀን ሌባ በሌሊት እንደሚመጣ፥ እንዲሁ ይመጣ ዘንድ ራሳችሁ አጥብቃችሁ አውቃችኋልና።” (1 ተሰ 5: 2) ጌታ ከመጣና ካዳንን፤ ሥራውንም ካየን፤ አውቀናል ማለት እንጅ አምነናል ማለት አይደለም።ማመን በመስማት ነው።እንዲል። ጌታ ቀን በመንፈስ ነበርሁ፥ በኋላዬም የመለከትን ድምፅ የሚመስል ትላቅ ድምፅ ሰማሁ፥” (ራእ 1: 10)
1.1.7.   የመዳንም ቀን
በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ መዳንም ቀን ረዳሁህ ይላልና፤ እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ እነሆ፥ መዳን ቀን አሁን ነው” (2 ቆሮ 6: 2)
አንድ ሰው፥ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የድኅነት ሥራ በአመነና፥ የእግዚአብሔር ልጅነትን በተቀበለበት ቀን፤ ሰው በዚያ ቀን፥ ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ህይወት ተሸጋገረ ይባላል። ያም ቀን ለዚያ ምዕመን መዳን ቀን ነው።
1.1.8.   የዘመኑ ፍጻሜ
ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤ (ገላ 44)
የዘመኑ ፍጻሜ ማለት፥ የአዳም፥ የግዞትና፥ የቅጣት ዘመን ፍጻሜን፥ የዓመተ ዓለምን፣ የዓመተ ፍዳን ፍጻሜ ... ለመግለጽ፥ የተነገረ ነው።
ዮሐንስም አልፎ ከተሰጠ በኋላ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል እየሰበከና፦ ዘመኑ ተፈጸመ የእግዚአብሔርም መንግሥት ቀርባለች ንስሐ ግቡ ወንጌልም እመኑ እያለ ወደ ገሊላ መጣ።” (ማር 114-15)
ወንጌል ሁለት ዓይነት ፍችዎች አሉት፤ የመጀመሪያው፤ ከለይ በቀረበው ጥቅስ መሰረት፥ የምሥራች፣ ደስታን የሚያበስር፣ የእግዚአብሔር መንግሥትን መምጣት... የሚገልጽ ቃል ሁኖ ነው። የእግዚአብሔር መንግሥት መቅረብ ማለት፥ የቅኝ ቅዛት፣ የባርነት፣ የግፍ፣ የአድሎ፣ የመከራ ዘመን ... ፍጻሜ፥ የነጻነት፣ የፍትሕ፣ የሰላም ዘመን... ጅማሬ ማለት ነው።
ሌላው የወንጌል ፍች፥ ወንጀል (crime) ማለት ነው። አራቱ ወንጌላውያን የጻፉት፥ የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን፥ ክሱን፣ ወንጀሉን፣ ጥፋቱን፣ የተላለፈውን ህግ... እና ፍርዱን፣ ፍዳውን፣ መከራውን፣ ቅጣቱን፣ ሞቱን... በተለይም ለሞት ቅጣት ያበቃውን ጥፋት ወይም ወንጀል ነው። በትግሬኛ ቋንቋ፥ ወንጌል የሚሉት የአማርኛውንወንጀልሲሆን፤ወንጌልየሚሉት ደግሞ የአማረኛውን ወንጀል ነው። በሌላ አገላለጽ፥ አንድ ሰው አጥፍቶ ትግራይ ፍርድ ቤት ሲቀርብ፥ወንጌለኛተብሎ ይፈረድበታል። በሌላ መልኩ፤ ቃለ እግዚአብሔርን የሚያስተምርንና መጽሐፍ ቅዱስን የሚሰብክን ሰውወንጀልንአስተማረ ይሉታል፥ ማለት ነው።
ሰንበት፥ የመክራ ዘመን ፍጻሜ፥ መሆኑን የሚያሳይ፥ ተጨማሪ ጥቅስ፥ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ፦ ተፈጸመ አለ፥ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ።” ~ finished (ዮሐ 19: 30)
 3.   የሰንበት ሰባዊ ባሕሪ፥ (ሰንበት፥ ማን ነው)
ሕጉ ሊመጣ ያለው የበጎ ነገር እውነተኛ አምሳል ሳይሆን  የነገር ጥላ አለውና፥ ስለዚህም በየዓመቱ ዘወትር በሚያቀርቡት በዚያ መሥዋዕት የሚቀርቡትን ሊፈጽም ከቶ አይችልም።” (ዕብ 101)
ሰንበትማን ነው?  ለሚለው ጥያቄ አጭሩ መልስ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ረዘም ያለው መልስ ደግሞ፥ መንግሥተ ሰማያት እና እግዚአብሔር ሰውን ለማዳን ያዘጋጀው ሥርዓት  ነው።
እነዚህ ሊመጡ ያሉት ነገሮች ጥላ ናቸውና፥ አካሉ ግን የክርስቶስ ነው” (ቆሮ 217)
በኦርት ዘመን በጊዜ (በቀን) እና በስም የተገለጸው ሰንበት፤ የሚመጣው የሰባዊው (አካሉ) ጥላ ነው።
ሰንበት ሰባዊማለት፥ አካላዊው ሰንበት፥ ማለት ነው።ሰብዓዊ ማለትም፥ ሰውኛ፣ ሰውነት፣ ሥጋን መልበስ፣ ሰው መሆን... ማለት ነው።
ኢትዮጵያ፥ በኩሽ፥ ኩሽቲክ ወይም ኩሻውያን ሲሉ፥ በኩሽ ልጅ፥ በሳባ ደግሞ ሳባዊ ይላሉ። ለዚህም ነው፥ ኢትዮጵያውያንቤተ ሳባወይም ቤተሰብ የሚሉት።
የሳባ ንግሥት፥ሳባያስባላት ሁለት ምክኛቶች አሉ። አንደኛው የሳባ ወገን፥ የኩሽ ልጅ ከሆነ ሕዝብ ስለመጣች ነው። ሁለተኛው ደግሞሳባየሚለው ስምሰውየሚል ፍች ስላለው፤የሰውማለት ደግሞ ለሰው ልጆች ሁሉ ከተሰጠው ስያሜ በተጨመሪየሌላየሚል ፍች አለው። ይህም፥ የሰው ሀብት፣ የሰው አገር፣ የሰው ልጅ፣ የሰው ንግሥት ... ማለት ይሆናል።
እንግዲህ፥ ንግሥተ አዜብን፥ የሳባ ንግሥት ያሰኛት እና ጌታ ኢየሱስን የሰው ልጅ፣ ያስባለው ሳባዊነታቸው እና የሌላ ሰውነታቸው ነው።
ቅዳሜ (የብሉይ ሰንበት) ቀዳሚ፥ አንደኛ፥ መጀመሪያ... ሰንበት፥ ሰባት፥ መጀመሪያ እና መጨረሻ አንድምታ አለው።
እሁድ (የአዲስ ኪዳን ሰንበት) እሑድ፥ አሐድ፥ አንደኛ... ሰንበት፥ ሰባት፣ መጨረሻ፥ መጀመሪያ እና መጨረሻ አንድምታ አለው።
            የኢየሱስ ሰንበትነት በጊዜ ሲገለጽ፥ የቅዳሜም የእሁድም ሰንበት እሱ ነው። የቅዳሜ ሰንበትነት፥ እግዚአብሔር ከዓለሙ ጋር ለመታረቅ፤ እግዚአብሔር አብ፥ ለመሰዋዕትነት ያቀረበው የበኩር ልጅ ነው። የእሁድ ሰንበትነት፥ ዓለሙ ከእግዚአብሔር ጋር እንዲታረቅ፥ ከእመቤታችን ድንግል ማሪያም፥ ለመሥዋዕትነት የቀረበ የበኩር ልጅ ነው። የኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር የበኩር ልጅነት፥ መጠሪያ የተገኘው፤ በእናቱ በድል ማሪያም የበኩር ልጅነት መሆኑን ልናስተውል ይገባል። ግልጽ ለማድረግ ያህል፥ ብኩርና የሚባለው የእናትን ማህጸን ከፍቶ በመውጣት የሚገኝ በመሆኑ እንጅ፥ የአባት የመጀመሪያ ልጅ መሆን በራሱ፥ በኩር የሚለውን መጠሪያ አያስገኝም። የይስሐቅን ለአብርሃም የበኩር ልጅነት ስናይ፤ ከይስሐቅ በፊት ለአብርሃም እስማኤል የሚባል ልጅ እንዳለው፥ ልንዘነጋ አይገባም። አልፋና ዖሜጋ የሚለው መጠሪያ ፍችው፥ መጀመሪያ እና መጨረሻ ማለት ሲሆን፤ የመጀመሪያና የመጨረሻነቱም፥ ለመቤታችን ልጅነቱ ነው።
ወልደ ሰንበት እና ወለተ ሰንበት፥ የሰንበት ልጅ፥ ማለት ሲሆን፤ በሰንበት ቀን የተወለደ() ማለት ሳይሆን፤ ሰንበት የሆነው፥ የኢየሱስ ክርስቶስ ልጅ፥ ማለት ነው። በሌላ አገላለጽ፥ ወልደ መድኅን እና ወለተ መድኅን ማለት ነው።
የሰንበት ትእዛዛት መጠበቅ፣ መቀደስ እና ማክበር፥
ዮሐንስም ከደቀ መዛሙርቱ ሁለት ወደ እርሱ ጠርቶ፡የሚመጣው አንተ ነህን ወይስ ሌላውን እንጠብቅ? ብሎ ወደ ኢየሱስ ላከ።” (ማቴ 11 : 319)
§  ሰንበትን ጠብቁ (keeping, waiting)
የእስራኤልም ልጆች ለልጅ ልጃቸው ለዘላለም ቃል ኪዳን ሰንበት ያርፉ ዘንድ ሰንበትን ይጠብቁ” (ዘጸ 31: 16)
ሰንበትን ጠብቁ የሚለው ትእዛዝ፥ ከአሥሩ ትእዛዛት አንዱ ሲሆን፥ በውስጡም፥ ቀድሱ እና አክብሩ የሚሉ ሁለት ትእዛዛት ይገኛሉ።
ሰንበት፥ በቅድሚያ ከትእዛዝነቱ ይልቅ ቃል ኪዳን ነው። የትእዛዛትን እና የቃል ኪዳናትን ልዩነት ለማየት፥ ትእዛዛት፥ አድርግ አታድርግ፥ በሚሉ ቀጥታ በመመሪያ የሚሰጡ ናቸው። እነዚህም በመጽሐፍ ቅዱስ፥ በቁጥር 613 ይሆናሉ። ለምሳሌ፥ አትዋሽ፣ አትስረቅ፣ አታመንዝር፣ አትግደል... የሚሉት ትእዛዛት እንጅ ኪዳናት አይደሉሙ።
በአንጻሩ፥ ቃል ኪዳናት፥ እንዲህ ብታደርግልኝ እንዲህ አደርግልሐለሁ፥ በሚል በሁለት ወይም ከዚያ በላይ ባሉ አካላት የሚደረግ ውል ነው። ለምሳሌ የኖህን እና የአምላክን፤ የአብርሃምን እና የአምላክን፤ የሙሴን እና የአምላክን... ቃል ኪዳናት እናገኛል።
እንግዲህ የሰንበት ትእዛዝ፥ ከሌሎች ዘጠኝ ትእዛዛት ጋር የተሰጠ ቃል ኪዳን ሲሆን፥ ለዓለም መዳን ትልቁን ምስጢር የያዘ ድርጊት ነው።
ጠብቁየሚለው ቃል፥ ከሰንበትና ትእዛዝ ጋር በተያያዘ፥ ሁለት ዋና ዋና ፍችዎች አሉት፤
አንደኛውመጠበቅማለት፥ የተሰጠንን ትእዛዝ፥ መጠበቅ፣ ማክበር፣ መፈጸም.. ማለት ሲሆን፥
ሁለተኛውመጠበቅማለት ደግሞ፥ የሚመጣን ትእዛዝ ለመፈጸም፥ መጠበቅ፣ መጠባበቅ፣ ሲጠብቁ መቆየት... ማለት ነው። ይህ ሁለተኛው መጠበቅ፥ መንግሥተ ሰማያትን፣ የጌታን ቀን፣ የመዳንን ቀን መጠበቅ... ነው። ይህም ቀን ጌታ ኢየሱስ ከመጣ በኋላ፥ዕረፍት፣ ዛሬ፣ አሁን... ማለት ነው፥ተብሎ ይፈታል።
በእርግጥ ሲጠበቅ የነበረው ሰንበት፥ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። ሲጠበቅ የነበረው፥ ከመጣ ደግሞ መጠበቅም፥ የሚጠበቅም ነገር አይኖርም።
ስለዚህ ለእናንተ ቅዱስ ነውና ሰንበትን ጠብቁ የሚያረክሰውም ሰው ሁሉ ፈጽሞ ይገደል፥ ሥራንም በእርሱ የሠራ ሰው ሁሉ ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጥፋ።” (ዘጸ 31: 14)
እነሆም፥ በኢየሩሳሌም ስምዖን የሚባል ሰው ነበረ፥ ይህም ሰው የእስራኤልን መጽናናት ይጠባበቅ ነበር፤ ጻድቅና ትጉህም ነበረ፥ መንፈስ ቅዱስም በእርሱ ላይ ነበረ።” (ሉቃ 2: 25) የእስራኤልን መጽናናት መጠበቅ ማለት፤ የእስራኤልን ነጻነት፣ የንጉሧን መምጣት፣ የመንገሥተ ሰማያትን መቅረብ... ይጠብቅ ነበር ማለት ነው።
ሌላው ሰንበትን ወይም የጌታን መንግሥት ይጠብቅ የነበረ፥ ዮሴፍ የተባለው ሰው ነው፥ እርሱም ደግሞ የእግዚአብሔርን መንግሥት ይጠባበቅ ነበር፤ ደፍሮም ወደ ጲላጦስ ገባና የኢየሱስን ሥጋ ለመነው። በእንግሊዝኛው መጽሐፍ ቅዱስ ~ waited for the kingdom of God (ማር 15: 43) ይህም በምክራቸውና በሥራቸው አልተባበረም ነበር፤ አርማትያስም ከምትባል ከአይሁድ ከተማ ሆኖ እርሱ ደግሞ የእግዚአብሔርን መንግሥት ይጠባበቅ ነበር።~ waited for the kingdom of God (ሉቃ 23: 51) ለዚህም “...በጉና ጻድቅ ሰው...” ተብሏል።
መጠባበቅየሚለው ቃል፤ በእንግሊዝኛው ቋንቋwaited forተብሎ ሲፈታ፤መጠበቅየሚለውን ደግሞ ‘Keeping’ ብለውታል። ይህም የመጠበቅን ትርጉም በትክክል እንዳይረዱት ያግዳቸዋል። የአማረኛውመጠበቅ ግን፥ መጠባበቅ ብሎ መረዳት ያስችላል። ይህም የሰንበትንመጠበቅትክክለኛ ፍች ግልጽ ያደርገዋል። ሰንበቴን ጠብቁ ማለቱ፥ ተጠባበቁ ማለት ስለሆነ።
ሌላው፥ ሰንበቴን ጠብቁትዛዝ፥ የተላለፈውን መመሪያ፥ በአግባቡ መፈጸምና ማስፈጸም ማለት ነው። ክርክርም በሆነ ጊዜ ለመፍረድ ይቁሙ፤ እንደ ፍርዴ ይፍረዱ፤ በበዓላቴ ሁሉ ሕጌንና ሥርዓቴን ይጠብቁ ሰንበታቴንም ይቀድሱ። ~ keep, hallow (ሕዝ 44: 24) ይህኛውን አገባብ እንኳ፥ በሌላ ቋንቋ የተጻፈላቸውም ቢሆኑ ይረዱታል።
የእግዚአብሔር መንግሥት የተባለው፤ የጌታን ቀን በመካከላችሁ ናት ያለው፤ የሰንበት ቀን... ማለት ነው። ይህን አባባል ሊያጸኑልን የሚችሉ፥ ቀጥለው የቀረቡ ጥቅሶችን እናያለን።
1.     እግዚአብሔር ሰንበቴን ለሚጠብቁ ደስ የሚያሰኘኝንም ነገር ስለሚመርጡ ቃል ኪዳኔን ለሚይዙ ጃንደረቦች እንዲህ ይላልና (ኢሳ 564)
2.     ከእናንተ ሰው ሁሉ እናቱንና አባቱን ይፍራ፥ ሰንበታቴን ጠብቁ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።(ዘሌ 193)
3.     ሰንበታቴ ጠብቁ መቅደሴንም አክብሩ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።” ~ keep my sabbaths (ዘሌ 19: 30)
4.     ሰንበታቴ ጠብቁ መቅደሴንም ፍሩ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።(ዘሌ 262)
5.     ስለዚህ ለእናንተ ቅዱስ ነውና ሰንበትን ጠብቁ የሚያረክሰውም ሰው ሁሉ ፈጽሞ ይገደል፥ ሥራንም በእርሱ የሠራ ሰው ሁሉ ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጥፋ።” (ዘጸ 31: 14)
ሰንበትን ቀድሱ፥
ሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ።“ (ዘጸ 208)
ቅዱስማለት ክቡር፣ ምስጉን፣ ልዩ፣ ምርጥ፣ ንጹህ፣ ጽሩይ...ማመስገን፣ መሥዋትና ጸሎት ማቅረብ፣ አምልኮ መፈጸም...ማለት ነው። (ኪወክ)
ስለዚህቀድሱማለት ደግሞ፥ ለእግዚአብሔር ልዩ... ማለት ነው። በስም በጊዜና በአካል... ‘ቀደሰማለት፥ ለየ፣ መረጠ፣ አከበረ... ክርክርም በሆነ ጊዜ ለመፍረድ ይቁሙ፤ እንደ ፍርዴ ይፍረዱ፤ በበዓላቴ ሁሉ ሕጌንና ሥርዓቴን ይጠብቁ፥ ሰንበታቴን ይቀድሱ ~ keep, hallow (ሕዝ 44: 24)
የሰው ልጅ የሰንበት ጌታ ነውና።~ For the Son of man is Lord even of the sabbath day (ማቴ 128)
የሰው ልጅየተባለው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።የሰንበት ጌታማለት ደግሞ በሳባውያን ዘንድ ያለውን ጌትነት፣ ንግሥና፣ ክብር... ሲገልጽ ነው። ሰንበት የሆነው፥ የማዳን ሥርዓት (ክርስትና) የተፈጠረው፥ ሰውን ለማዳን እንደሆነ የሚያብራራ አባባል ነው። ደግሞ፦ ሰንበት ስለ ሰው ተፈጥሮአል እንጂ ሰው ስለ ሰንበት አልተፈጠረም፤~ The sabbath was made for man (ማር 2: 27) ሕግ የተፈጠረው ሰዎች ስለአልተስማሙ፣ ስለተሟገቱ፣ ስለተከራከሩ እንጅ፥ የምንከራከረው፣ የምንሟገተውና የማንስማማው ሕግ ስላለ አይደለም።
ንበት ስለ ሰው ተፈጥሮአል..’ ማለት መድኃኒት ስለ በሽታ ተፈጠረ  እንጅ፥ በሽታ ስለ መድኃኒት አልተፈጠረምእንደማለት ነው። ትምህርት ስለ ማሐይምነት ተፈጠረ፥ ምግብ ስለርሃብ ተዘጋጀ... እንደ ማለት ነው። ኀጢያት ባይኖር፥ ክርስትና ባላስፈለገ። አዳም ባይስት ክርስቶስ ባልተወለደ። አዳም ባይፈረድበት፤ ምህርት ባላስፈለገው። በሽተኛ ባይገኝ ፈውስ ባላስፈለገ። እንደዚሁም ሁሉ፤ ሰንበት ስለሰው ተፈጥሯል ማለት... ጎስቋላውን ሰው፥ ለመፈወስ፥ ሟቹን ሰው ለማዳን፣ የታሰረውን ለማስፈታት... ክርስትና ለሰው ልጆች መመስረቱን የሚገልጽ ነው።
ስለዚህ ሙሴ መገረዝን ሰጣችሁ፤ ከአባቶችም ነው እንጂ ከሙሴ አይደለም፤ በሰንበትም ሰውን ትገርዛላችሁ።~ circumcise a man (ዮሐ 7: 22) በሰንበት፥ የድህነትን ሥራ መስራት፥ ሰንበትን ለተቀደሰለት አላማ ማዋል እንጅ፥ ህግን እና ትዛዛትን መተላለፍ አይደለም።
እንግዲያስ የሰንበት ዕረፍት ለእግዚአብሔር ሕዝብ ቀርቶላቸዋል።~ a rest to the people of God (ዕብ 4: 9)
ክህ አገልግሎት፣ የፈውስ የእርቅ፣ የድህነት አገልግሎቶች መፈጸም ሰንበትን እንደማያሽር፤ እንዲያውም ሰንበት የተቀደሰችው ለእንደዚህ ዓይነት አገልግሎት እንደሆነ እንገዘባለን። ካህናትም በሰንበት በመቅደስ ሰንበትን እንዲያረክሱ ኃጢአትም እንዳይሆንባቸው በሕጉ አላነበባችሁምን?” ~profane (ማቴ 12: 5)
በሰንበት ያርፉ ዘንድ ሰንበትን ይጠብቁ ማለት ይጠባበቁ...ማለት ነው። ሰንበት የሆነ፥ የሚመጣ፥ እረፍትን የሚያስገኝ ...  ማለት ሲሆን፥ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ፥ ሰንበት እሱ፣ የዘለዓለምን እረፍት፥ የሚያስገኝ እሱ፥ በነብያት ዘመን ይመጣል ተብሎ የሚጠበቅ እሱ፥ መጥቶ ያዳነን ስለሆነ፥ እንደሚመጣ ዛሬ ሰንበትን አንጠብቅም። ሰንበትን እንቀድሳለን፥ እናከብራለን እንጅ፥ ሰንበትን ጠብቁ ብሎ ጌታ አላስተማረንም።
ሰንበትን አክብሩ፥
ሰንበትን ማክበር፥ ከትእዛዛት አንዱ ነው። ሰንበትንማክበርማለት ምን ማለት ነው? እንዴትስ ይከበራል?
ማክበርማለት፥ መወደድ፣ ማደግ፣ መብለጥ፣ ታላቅ መኾን... ልዕልና፣ ላቂያ፣ ብልጫ፣ ሹመት...ማለት ነው።(ኪወክ)
እንዲህ ከሆነ፥ የሰንበት ትእዛዝ የተሰጣቸው፥ ሰንበትን፥ ማለትም የዓለምን መድኀኒት፥ ኢየሱስ ክርስቶስን የመውደድ፣ የማላቅ፣ የማብለጥ፣ ሹመቱን የመቀበል፥ ግዴታ... አለባቸው ማለት ነው። ማክበር ትእዛዝ ስለሆነ፤ ትእዛዝን የምይፈጽም ደግሞ ቅጣትን ይቀበላል።
ከፈሪሳውያንም አንዳንዶቹ፦ ይህ ሰው ሰንበትን አያከብርም ከእግዚአብሔር አይደለም አሉ። ሌሎች ግን፦ ኃጢአትኛ ሰው እንደነዚህ ያሉ ምልክቶች ሊያደርግ እንዴት ይችላል? አሉ። (ዮሐ 916)
ከዚህ ጥቅስ የምንረዳው፥ማክበርመፍራት ማለት ነው። ከፍ አድርጎ ማየት፣ ኃያልነቱን ማመን፣ መታዘዝ፣ ፈቃደኛነትን ማሳየት... በአይሁድ አረዳድ ሰንበትን ማክበር ማለት፥ በሰንበት ቀን ምንም ሥራ አለመሥራት፥ የድኅነትም ሥራንም ቢሆን እየሱስ የሰንበት ጌታ እና የሚከበረው እሱ መሆኑን አልተገነዘቡም የሠራው ሥራ  እንደማያስጠይቀው፥ ያውቃሉ፥ በክፋ መንፈስ እየተመሩ ፈውስን እና ሌሎች መልካም ነገሮችን መሥራትንም ቢሆን ይቃወማሉ።


No comments:

Post a Comment

ማውጫ

መግቢያ                                                                                                     ክፍል አንድ፡ ኢትዮጵያ እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ታ...