ክፍል ሁለት

 ኢትዮጵያ እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃላት
በዚህ ክፍል፥ ኢትዮጵያ በአምልኮ ቋንቋ  ውስጥ ያላትን ድርሻና ለሌላው ዓለም ቋንቋዎች፥ ያደረገችውን አስተዋጽዖ እንመረምራለን። በተለይ፥ የመጽሐፍ ቅዱሳዊ ስሞችን፥ ትርጉም እና ሥርዎ ቃል በመዳሰስ፣ በመርመርና በማጥናት፥ ለማሳየት ይሞከራል። በዓለማችን ከሰባት ሺሕ የሚበልጡ ቋንቋዎች እንደሚነገሩ ይገመታል። የሁሉም ቋንቋዎች መነሻ ደግሞ አንድ የምሥራቅ አፍሪካ የቋንቋ ቤተሰብ መሆኑን ብዙ የቋንቋ አጥኝዎች ይስማማሉ። በቅዱሱ መጽሐፍም ተመዝግቦ እንዳገኘነው፥ ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች።ይላል (ዘፍ 11: 1) ስለሆነም የሰው ልጆች ሁሉ ከአንድ ቤተሰብ እንደ መጡ፥ በዓለማችን ያሉ ቋንቋዎችም የወጡት፥ ከአንድ የቋንቋ ቤተ ሰብ እንደ ሆነ መቀበል አያስቸግርም።
            ቋንቋ በባህሪው ይወለዳል፣ ያድጋል (ይስፋፋል) ይሞታል (ይጠፋል) ነገር ግን አይፈጠርም (ከየትም አይወጣም) ይህም ማለት በዓለማችን የሚገኙ፥ የተለያዩ የሚመስሉን ቋንቋዎች ሁሉ፥ አንድ የሚያደርጋቸው፣ የሚያስተሳስራቸው፣ የሚያመሳስላቸው እና የሚያገናኛቸው የዘር ሐረግ አለ።
            ከቋንቋ ክፍሎች ውስጥ ከአገር ወደ አገር፥  ከቋንቋ ወደ ቋንቋ፥ ከዘመን ወደ ዘመን ሲወራረስ እና ሲተላለፍ በቀላሉ የማይቀየር የቋንቋ ክፍልስምነው። የአንድን ነገር ስም፣ ምንጭ እና ትርጉም ማጥናት፥ በስሙ ባለቤት ዙሪያ ያለውን ታሪክና ምስጢራዊ መልእክት ለመረዳት ይረዳል።
            ስለዚህ በዚህ ክፍል ውስጥ የምናተኩረው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉትን ስሞች ብቻ ነው። የነዚህን ስሞች፥ በዘመናቸው የነበረውን ትርጉም በማወቅም፥ በዚያን ዘመን ለማስተላለፍ የተፈለገውን ቁም ነገር ለመረዳት ትልቅ አስተዋጽዎ ይኖረማል።
ስሞች እና ሌሎችም ቃላት ሦስት ዓይነት አፈታት አላቸው፥ ቀዳማዊ ፍች፥ ሥርዎ ቃሉን መሰረት ያደረገ (etymological) አውዳዊ ወይም አገባባዊ (contextual) እና ዘመናዊ ፍች (contemporary) ናቸው። ይህ ጥናት በይበልጥ ትኩረት የሚሰጠው በቀዳማዊ ትርጉሞች ላይ ነው።
            ስምማለት መጠሪያ ማለት ነው።ስምካለ አካል አለ፥ አካል ካለ ስም አለ። ስለዚህ የማይታይም ሆነ የሚታይ ነገር፥ ስም ካለ አካሉ ደግሞ አለ ማለት ነው።ምድራዊ አካል ካለ ሰማያዊ አካል ደግሞ አለእንዲል ሐዋርያው።
ስምየሚለው ቃል በራሱ ስም ነው። ይህም ስም ከቋንቋ ክፍሎች፥ አንዱ፣ ግስ ወይም ቅጽል ወይም ሌላ ያልሆነ የዓርፍተ ነገር ክፍል ማለት ነው። ስም ከግስ ይገኛል። ግስ ደግሞ ድርጊት ወይም ጠባይን ይገልጣል። ከዚህ አኳያ ስናየው ስም የሚለው ስም እራሱሰመየከሚለው ግስ መገኘቱን እንገነዘባለን።ሴምየተባለው የኖኅ ልጅ የስሙ ትርጉም፥ በእንግሊዝኛው የመጽሐፍ ቅዱስ የስም መዝገበ ቃላት ‘Sem’ means name. ይላል። ይህ  እንግዲህሴምየሚለውስምትርጉሙስምማለት ነው። ይህን ካልን፥ሴምየሚለው ቃል የመጣውምስምከሚለው ቃል ነው፥ ለማለት እንችላለን። ስሞች በብዛት የሚጨርሱት በሳድስ ፊደል ነው። በዚህምስምየሚለው ቃል ሳድስ መጨረሱን እናስተውላለን።
በሌላ በኩል፥ ግሶች የሚጨርሱት በግእዝ ነው። ይህም ማለት፥ እስከላሉት የመጀመሪያው ፊደል ማለት ነው።
በጥንት ዘመን፥ ቋንቋ ሁሉ አንድ እንደ ነበር በመጻሕፍት ተመዝግቦ  እናገኛለን። ቋንቋ እየበዛ ሲሄድ፥ በቋንቋዎች መካከል ያለውም ልዩነት እየሰፋ መጣ። ሆኖም ግን አንድ የቋንቋ ክፍል (አካል) በቋንቋዎች መካከል ጉልህ ልዩነት ሳያሳይ የቋንቋዎችን መዛመድ፥ ማሳያ ሆኖ እስከ አሁን ይገኛል። ይህም የቋንቋ አካል ስም ነው። ለምሳሌ የመጀመሪያው ሰው፥አዳምየሚለው ስም፥ ከቋንቋ ወደ ቋንቋ፥ ከዘመን ወደ ዘመን፥ ከቦታ ወደ ቦታ ሲተላለፍ፥ የጎላ ልዩነትን ሳያሳይ አሁን ካለንበት ዘመን ደርሷል። ስለዚህ ስምን ማጥናት፣ መመርመር፣ መተርጎምና መረዳት የታሪካዊና መንፈሳዊ መልክቶችን ለመረዳት፥ አመች መንገድ ሁኖ እናገኘዋለን።
ስም ከመቃብር ባላይ ይቀራል፥የሚለው አባባል፥ የስምን ባሕሪ በተሻለ ይገልጸዋል። ለዚህም ማስረጃ፥ አዳም ከሞተ፥ ከብዙ ሺሕ ዓመታት በኋላ አሁንም ስሙ ሳይጠፋ፥ ሳይለወጥ ለሁልጊዜ ፀንቶ ይኖራል።  
የግእዝ ቃላት ደግሞ የሚታወቁት፥ በግእዝ ፊደላት በመመስረታቸው ነው። አብዛኛው የግዕዝ ቃላት የተመሰረቱት በሦስት ፊደላት ብቻ ሲሆኑ፥ ሦስቱም ፊደላት ግዕዝ መሆን አለባቸው። ስለዚህ የአንድን ስም ምንጭ ወይም ግሱን ማግኘት ከተቻለ፥ የዚያን ስም ሥርዎ ቃሉ ግእዝ መሆኑን ማሳየት ይቻላል፥ ማለት ነው። ይህም ማለትስምየሚለውስምየተገኘውሰመየከሚለው ግስ ስለሆነ፥ ሰማ የሚለው ግስ ደግሞሰምአከሚለው የግእዝ ቃል ጋር አንድ መሆኑን እና የቃሉ ምንጭ መሆኑን እንረዳለን።
 ምዕራፍ አንድ
 ኢትዮጵያዊ ያምላክ ስሞች
እግዚአብሔር አምላክ፥ መመለክ የጀመረው፥ ሰውም አምላክን ያወቀው፥ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አቀራረብ፥ በዛሬዋ አፍሪካ ነው። አምላክ ከሰው ጋር፥ ለመጀመሪያ ጊዜ የተነጋገረው፥ በዛሬዋ የምሥራቅ አፍሪካ አገር፥ በኢትዮጵያ ነው። ለዚህ እንደማስረጃ ለማቅረብ፥ እግዚአብሔር፥ ራሱን ለሰው የገለጸበት ስሞች፤ ሰዎች እግዚአብሔርን የጠሩበት ስሞች እና እግዚአብሔር ሰዎችን እና ቦታዎችን የጠራበትን ስሞች በማጥናት፣ በመመርመር፣ ፍቻቸውን እና ስርዎ ቃላትን በማብራራት፥ በኢትዮጵያውያን ቃላት ውስጥ፥ እውነቱን ማሳየት ይቻላል።
በመጽሐፍ ቅዱስ ተመዝግበው ከቆዩን የእግዚአብሔር ስሞች፥ ዋና ዋናዎቹ እና በግልጽ የሚታወቁት፥ ቀጥለው የቀረቡት ናቸው፥
አባ (Abba) ኃያል (Almighty) ህያው (Jehovah) ዋስ (Surety, Saviour) [ቤዛ፣ አዳኝ፣ መድሃኒዓለም...] ጻድቅ (Righteous) ቅዱስ (Holy) አልፋና ዖሜጋ (Alpha and Omega) አማኑኤል (Immanuel, Emanuel) መሢሕ (Messiah)... እና የመሳሰሉት ናቸው።
1.   አባ (Abba)አቡ፣ አቢ፣ አቤ፣ አብ...)
አባታችን ሆይ...’ የሚለው ፀሎት የሚጀምረው፥ እግዚአብሔር አምላክን በስሙ በመጥራት ነው።አባታችንየሚለው በህብረት ሁነው ለሚጠሩት ሲሆን፥ እንደግለሰብ ሁኖ ለመጠራት ደግሞ፣ አባ፣ አባባ ወይም አባቴ ማለት ይቻላል።
አባተብሎ የሚጠራበት የአምላከ ስም፥ ከሁሉም መጠሪያ ስሞች፤ ለጠሪው ቅርበትን የሚያሳይ ነው።
አባ አባ ሆይ፥ ሁሉ ይቻልሃል፤ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን አንተ የምትወደው እንጂ እኔ የምወደው አይሁን አለ~ Abba, Father (ማር 1436) Abba The name “Abba” means father, HBN, , And he said, Abba, Father, all things are possible unto thee ...” (Mar 1436), [አባ፥ የሚለው መጠሪያ፥ በእንግሊዝኛው መጽሐፍ ቅዱስAbbaማለቱን ልናስተውል ይገባል]
ከላይ ከቀረበው ጥቅስ የምናገኘው አንድ መልክት፥ የእግዚአብሔር ልጅ፥ ጌታ ኢየሱስ፥ አባቱን ይጠራ የነበረውአባ አባእያለ እንደነበር ነው። አምላክ እግዚአብሔርን፥አባ አባ/ አባባእያሉ መጥራት፥ ከጥንት ጀምሮ የነበረ፥ የኢትዮጵያውያን ባህልና ሥርዓት ነው። የጌታ ኢየሱስ፥ አምላክንአባ አባእያለ መጥራት፥ ከኢትዮጵያውያን አጠራር ጋር ለምን እንደተመሳሰለ፥ኢትዮጵያ እና የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክበሚለው ክፍል፥ጌታ ኢየሱስ በኢትዮጵያበሚለው ምዕራፍ ሥር እናየዋለን።
 አብ’ / ‘Abየሚጀምሩ ስሞች
አባ ~ Abba: አብ፣ ወላጅ (ፈጣሪ) ትልቅ (በስልጣን፥በኃይል) አዛውንት (በእድሜ፥ በልምድ)... ማለ ነው። [ተዛማጅ ስም- ]
·       ጌታ ሱስ ቱን የጠራበ ስም፥አባ አባ ሆይ፥ ሁሉ ይቻልሃል፤ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን አንተ የምትወደው እንጂ እኔ የምወደው አይሁን አለ” (ማር 1436)
·       ሐዋርያው ጳውሎስ እግዚአብሔር አምላክን ለሮማውያን የገለጸበት ስም፥ አባ አባ ብለን የምንጮኽበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ እንደገና ለፍርሃት የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁምና። (ሮሜ 815)
·       ሐዋርያው ጳውሎስ እግዚአብሔር አምላክን ለገላ ሰዎች የገለጸበት ስም፥ ልጆችም ስለ ሆናችሁ እግዚአብሔር አባ አባ ብሎ የሚጮኽ የልጁን መንፈስ በልባችሁ ውስጥ ላከ። (ገላ 46)
አቡ ~ Abi: አብዬ አባይ፣ አባት፣ ትልቅ... ማለት ነው።
የይሁዳ ንጉሥ የአካዝ ልጅ የሕዝቅያስ ስትሆን፣ የዘካርያስ ልጅ (2 ነገ 182) (ዜና 291)
Abi: The name “Abi” means my father, HBN ... [Related name(s): - Abia, Abiah, Abijah]
አቢኤል ~ Abiel: አቢ ኤል አቤል፣ አበ ኃያል፣ አባቴ አምላኬ፣ ጌታዬ አምላኬ፣ ታላቅ አምላክ፣ ታላቅ ጌታ፣ ታላቅ ገዥ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም/ ስሞች- አቤል፣ ኤልያብ]
አብ እና ኤል ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
Abiel: Abiel” means father of strength, i.e. strong, SBD ... [Related name(s): Abel, Abihail, Eliab]
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች፥
1.     ብንያማዊው ቂስ አባት፥ (1 ሳሙ 1451)
2.     ንጉሥ ዳዊት በዘበኞቹ ላይ የሾመው (ዜና 1132 33)
አቢካኢል ~ Abihail: ኃያል፣ አባ ኃይ አሸናፊ፣ ጉልበተኛ፣ ታላቅ ኃያል ...ማለት ነው።
አበ እና ኃይል ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
Abihail The name “Abihail” means the father of strength, HBN ... [Related name(s): Abel, Abiel, Eliab...]
በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች አምስት ናቸው። የሱሪኤል ት፥ (ዘኁ 335) የአቢሱር ሚስት (ዜና 229) ከጋ ነገድ የሆነ፣ የዑሪ ልጅ (ዜና 5: 14) የዳዊት ወንድም፥ የኤልያብ ልጅ  (ዜና 11: 18) የመርዶክዮስ አጎት የአስቴር ት፥ (አስ 215)
አብያ ~ Abiah, Abijah: አበ ያህ፣ አባ ያህ አባቴ አምላኬ፣ ጌታዬ አምላኬ፣ ህያው አምላክ ዘላለማዊ ጌታ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- አቢያ]
አብ እና ያህ(ያህዌ ህያው) ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
Abiah:  The name “Abiah” means the Lord is my father, HBN... [Related name(s): Abi, Abia, Abijah]
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች፥  የነ ልጅ፥ (1 8: 2) ብኒያም ወገን፣ የቤኬር ጅ፥ (1 ዜና 78)
Abijah: “Abijah” means my father is Jehovah, SBD, ከአልዓዛር ወገን፥ስምንተኛው አብያ ዘጠኝኛው ለኢያሱ፥(1 ዜና 2411) የሮብዓም ልጅ፥ (ዜና 1216) (ነገ 421) የኢዮርብዓም ልጅ የመጀመው፥ (ነገ 14: 1) የኢዮርብዓም ልጅ ( 12: 4 17) (ዜና 24: 10) (ዜና 8: 14) በነህምያ ዘመ የነበረ  ህን፥ ( 10: 7)...
አቤል ~ Abel: አቤል፣ አበ ኤል ኃያል፣ አባቴ አምላኬ፣ ጌታዬ አምላኬ፣ ታላቅ አምላክ፣ ታላቅ ጌታ፣ ታላቅ ገዥ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- አቢኤል፣ ኤልያብ...]
አበ እና ኤል ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
Abel: አንድ ሰውና አንድ አገር በዚህ ስም ይጠሩ እንደ ነበር፥ በመጽሐፍ ቅዱስ ተመዝግቦ ይገኛል፥ ሂዋ ለተኛ ልጅ፥ (ዘፍ 42) እና የቦታ ስም፥እርሱ ግን ከእስራኤል ነገድ ሁሉ ወደ አቤል ወደ ቤትመዓካ፥ ወደ ቤሪም ሁሉ አለፈ ሰዎችም ደግሞ ተሰብስበው ተከተሉት (2 20: 14) (2 2015)
አብየሚጨርሱ ስሞች
ሞዓብ ~ Moab: መአብ አባትነት፣ ወላት፣ አባት መሆን... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም/ ስሞች- አባ፣ አባት...]
አበ ከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው።
Moab The seed of the father, EBD; The name “Moab” means of his father, HBN,
በዚህ ስም የሚታወቁ አንድ ሰውና አንድ ቦታ አሉ የሎ ልጅ፥ ሞዓብታላቂቱም ወንድ ልጅ ወለደች ስሙንም ሞዓብ ብላ ጠራችው እርሱም እስከ ዛሬ የሞዓባውያን አባት ነው” ( 19: 37) እና የቦታ ስም፥ በሞዓብ ምድር (ሩት 1: 1 2 6) እሥራኤላ ግብፅ ከወ በኋላ ያለባቸ ቦታዎ አንዱ፥ ( 21: 11)...
አክዓብ ~ Ahab: አያ ብ፣ የአባት ወንድም፣ ... ማለት ነው።
Ahab -አያ እና አብ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
[የአባት ወንድም ማለት ነው, የመ/ቅ መ/ቃ]
Ahab The name “Ahab” means uncle, or father's brother, HBN,
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች፥ የዘንበሪ ልጅ፣ እስራኤ የነገሠ አክዓብ (1 ነገ 1628) የቆላያ ልጅ አሰተኛ ነብይ፥ (ኤር 29: 21)...
ኤልያብ ~ Eliab: ኤል አብ የአባቴ አምላክ፣ አባቴ አምላኬ ኃያለ አብ፣ ኃያል አባት... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም/ ስሞች- አቤል፣ አቢኤል...]
ኤል እና አብ ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
Eliab To whom God is father, EBD
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች፥ የአሂሳሚክ ልጅ ( 31: 6) የሮቤል ጅ፣ ዳታንና አቤሮን ት፥ (ዘኁ 16112) የኬሎን ልጅ ( 1: 9 2: 7 7: 24 29 10: 16) የዳዊት ወንድም፣ የእሴ ልጅ፥ ( 16: 6 17: 13 28 1 ዜና 2: 13) በዳዊት ዘመን የነበረ መዘምር፥ (1 ዜና 15: 18 20 16: 5) ከጋድ ልጆች የጭፍራ አለቆች (ዜና 12: 10) የሕልቃና ጅ፥ (ዜና 6: 27)
ኢዮአብ ~ Joab: ኢዬአብ የአብ፣ አባታዊ፣ የእግዚአብሔር ሰው፣ የአምላክ የሆነ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም/ ስሞች- ኢዮባብ ኢዮብ ዮብ ያሱብ ዩባብ ዮባብ...]
አብ ከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው ነው።
[ትርጉሙ እግዚአብሔር አባት ነው ማለት ነው, የመ/ቅ መ/ቃ]
Joab: Jehovah is his father, EBD; The name “Joab” means paternity; voluntary, HBN
ንጉሥ ዊት እህት የጽሩያ ልጅ (2 2: 13 10: 7 11: 1ነገ 11: 15)
 2.   ኃያል ኤልEl)
“...ስምህ ታላቅና ኃያል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው” (ኤር 32: 18)
            እግዚአብሔር አምላክ ከሚጠራባቸውና ከሚታወቅባቸው፤ ባህሪውን እና ግብሩን በትክክል ከሚገልጹ ስሞች፥ ቀዳሚው እና ዋነኛውኃያልየሚለው ስም ነው።
ከዚህ ቀጥሎ የቀረቡ፥ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ስንመለከት፥ ይህንኑ እውነታ ግልጽ ያደርጉልናል።
1.     እንግዲህ አምላካችሁ እግዚአብሔር የአማልክት አምላክ የጌቶችም ጌታ፥ ታላቅ አምላክ ኃያል የሚያስፈራም፥ በፍርድ የማያደላ፥ መማለጃም የማይቀበል ነውና እናንተ የልባችሁን ሸለፈት ግረዙ፥ ክእንግዲህ ወዲህም አንገተ ደንዳና አትሁኑ።” (ዘዳ 10: 17-17)
2.     እነሆ፥ እግዚአብሔር ኃያል ነው፥ ማንንም አይንቅም እርሱም በማስተዋል ብርታት ኃያል ነው” (ኢዮ 36: 5)
3.     ስለዚህ የእስራኤል ኃያል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በጠላ...” (ኢሳ 24: 1)
4.     የጌታ ኢየሱስን ክርስቶስን አምላክነት፥ ከሚመሰክሩ ትንቢታት አንዱ፥ ገና ከመወለደኡ አስቀድሞ፥ በነብዩ ኢሳያስ ኃያል አምላክ ተብሎ መጠራቱ ነው፥ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።” (ኢሳ 6: 9) [ኢየሱስ የሚለው ስም ፍች እና ኢሳያስ የሚለው ስም ፍች፥ አንድ ዓይነት ትርጉም አላቸው።]
5.     ለብዙ ሺህ ምሕረት ታደርጋለህ፥ የአባቶችንም በደል ከእነርሱ በኋላ በልጆቻቸው ብብት ትመልሳለህ፤ ስምህ ታላቅና ኃያል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።” (ኤር 32: 18)
ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች፣ ቦታዎች እና የመሳሰሉ ነገሮች፥ኃያልከሚለው የአምልክ ስም፥ ያል (ኤል) የሚለውን ድምጽ በመውሰድ፥ ከሌላ ቃል(ስም) ጋር በማገናኘት፥ ይጠሩበታል። እንዚህንም ኤልየሚጀምሩ፣ ኤልየሚጨርሱ፣ ኤል’... በማለት ከፋፍለን ለጥናት ቀርበዋል።
የሚጀምሩ ስሞች እና ፍቻቸው፥
ኤሊ ~ Eli: ኤልይ፣ ኢላይ እላይ፣ እግዚአብሔር ... ማለ ነው። [ተዛማጅ ስም- ዔሊ ኤላ...]
የስሙ ምንጭኃይል የሚለው ቃል ነው።
Eli: Ascension, HBN, the offering or lifting up, EBD
በጌታ የትውልድ ሐረግ የተጠቀሰ፣ የማቲ ልጅ፥ (ሉቃ 3: 23)
ካህኑ ኤሊ፥ (1 19)
ኤሊኤል ~ Eliel: ኤል ኤል ጌታዬ አምላኬ፣ ጌታ ጌታዬ፣ አምላኬ አምላኬ ኃይለ ኃያል፣ የኃያላን ኃያል... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ኤልኤል]
ኤል ደጋግሞ  በመጥራት የተመሠረተ ቃል ነው።
Eliel” means to whom God is strength, SBD,
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች፥ የምናሴ ነገድ አባቶቻቸው ቤቶች አለቆች (1 ዜና 5: 24) ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤት በኢየሩሳሌም እስኪሠራ ድረስ በመገናኛ ድንኳን ማደሪያ ፊት እያዜሙ ካገለገሉ የነብዩ  ሳሙኤል ቅድመ አያት፥ (ዜና 6: 34) በኢየሩሳሌም ከተቀመጡ በትውልዶቻቸው አለቆች የነበሩ  የብንያም ነገድ አለቃ፣ የኤልፍዓል ጅ፥ (ዜና 8: 20) በኢየሩሳሌም የተቀመጡ በትውልዶቻቸው አለቆች የነበሩ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች የሰሜኢ ጅ፥ (ዜና 8: 22 23) መሐዋዊው የንጉሥ ዳዊት ወታደር፥ (ዜና 11: 46) በጺቅላግም ከቂስ ልጅ ከሳኦል በተሸሸገ ጊዜ ወደ ዳዊት የመጡ (ዜና 12: 11) የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ታቦት መጡ ዘንድ ንጉሥ ዊት ከታዘዙ፥ (ዜና 15: 9 11) በንጉሡ በሕዝቅያስና በእግዚአብሔር ቤት አለቃ በዓዛርያስ ትእዛዝ ከኮናንያና ከወንድሙ ከሰሜኢ እጅ በታች ተቈጣጣሪዎች ከነበሩ (ዜና 31: 13) ኤልኤል- (ዜና 11: 47) ...
ኤልሳቤጥ ~ Elisabeth, Elisheba: ኤል ሳባ ቤት፣ ኤል ሳቤት ኤል ሰባት፣ ምላክ ቤተሰብ፣ የጌታ ወገን... ማለት ነው።
ኤል ሳባ እና ቤት ከሚሉ ሦስት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
Elisabeth, Elisheba “Elisabeth” means the oath of God, SBD ... [Related name(s): Elisheba]
The name “Elisha” means salvation of God, HBN ... [Related name(s): Elishah, Elishua]
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች፥
·       ኤልሳቤጥ, Elisabeth: ከአሮን ገን ስትሆን የዘካርያስ ሚስት፣ የመጥምቁ የዮሐንስ እናት፥ የጌታ እናት የማርያም አክስት፥ (ሉቃ15)
·       ኤልሳቤጥ, Elisheba: የአሮን ሚስት፥ (ዘጸ 623)
ኤልቤቴል ~ Elbethel: ቤተ ኤል፣ ምላክ-ቤተመቅደስ፣ የጌታ ወገን ቤት የኃያ አም ... ማለት ነው።
ኤል እና ቤቴል ከሚሉት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
Elbethel: “Elbethel” means the God of Bethel, SBD,
ያቆ ከኢሳው በሸሸው ጊዜ እግዚአብሔር የተገለጠለት የቦታ፥በዚያም መሰውያውን ሠራ፥ የዚያንም ቦታ ስም ኤልቤቴል ብሎ ጠራው እርሱ ከወንድሙ ፊት በሸሸበት ጊዜ እግዚአብሔር በዚያ ተገልጦለት ነበርና።” (ዘፍ 357)
ኤልያስ ~ Eliah, Elijah: ኤል ዋስ፣ ኤል ያህ፣ ህያው ጌታ፣ ኃያ አምላክ፣ አም... ማለት ነው።
ኤል እናያህ (ያህዌ) ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
[ትርጉሙእግዚአብሔር አምላክ ነውማለት ነው, የመ/ቅ መ/ቃ]
Eliah, Elijah whose God is Jehovah, EBD,
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች፥
ኤልያስ, Eliah:
ብንያማዊው የነገዱ አለቃ፥ (1 ዜና 827)
ዕዝ ዘመን እግዶች ሚስቶችን ካገቡ፣ ከካሪም ጅ፥ (ዕዝ 10: 21 26)
ኤልያስ ~ Elijah: የሞተ ልጅ ያስነሳ፣ ዝናም ለሁለት ዓመት እንዳይዘንብ ሰማይን የዘጋ፣ ኤልያስ (1 ነገ 171)
ኤልያቄም ~ Eliakim: ቆም ኤል ቆመ፣ በአምላክ የጸና፣ እግዚአብሔር ያነሳው... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም/ ስሞች- ቀሙኤል ቁሚ አኪቃም አዶኒቃም ኢዮአቄም ዓዝሪቃም ያቂም ዮቂም ዮአቂም...] 
ኤል እና ቆመ ከሚሉት ሁለት ቃላት የተመሠረተ  ስም ነው።
[ትርጉሙ እግዚአብሔር ያስነሳል ማለት ነው, የመ/ቅ መ/ቃ]
Eliakim: whom God will raise up, EBD; Resurrection of God, HBN,
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች፥ የኬልቅያስ ልጅ (2 ነገ 1818) ( 36: 3) (ነገ 18: 18 26 37) በጌታ የዘ ሐረ የተጠቀሰ የዮናን ልጅ፥ (ሉቃ 330 31) (ማቴ 1: 13) የኢዮስያስ ልጅ የኢዮአክስ ንድም፥ ኢዮአቄም የቀድሞ ስም፥ (ዜና 36: 4) (ነገ 23: 34) በነህምያ ዘመን የነበረ ካህን፣ የኢየሩሳሌም ግንብ በማደስ የተባበረ፥ ( 12: 41) ...
ኤልያብ ~ Eliab: ኤል አብ የአባቴ አምላክ፣ አባቴ አምላኬ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም/ ስሞች- አቤል፣ አቢኤል...]
ኤል እና አብ ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
Eliab: To whom God is father, EBD
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች፥ የአሂሳሚክ ልጅ ( 31: 6) የሮቤል ጅ፣ ዳታንና አቤሮን ት፥ (ዘኁ 16112) የኬሎን ልጅ ( 1: 9 2: 7 7: 24 29 10: 16) የዳዊት ወንድም፣ የእሴ ልጅ፥ ( 16: 6 17: 13 28 1 ዜና 2: 13) በዳዊት ዘመን የነበረ መዘምር፥ (1 ዜና 15: 18 20 16: 5) ከጋድ ልጆች የጭፍራ አለቆች (ዜና 12: 10) የሕልቃና ጅ፥ (ዜና 6: 27)
የሚጨርሱ ስሞች
መልኪኤል ~ Malchiel: ምሉከ ኃያል፣ ኃያል አምላክ፣ ጌታ አምላክ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም/ ስሞች- መልክያ ሚካኤል ሚካያ ሚክያስ...]
መልክእናኤል ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
Malchiel: The name “Malchiel” means God is my king, or counselor, HBN,
ወደ ግብፅ ከገቡት ከእስራኤል ልጆች ወገን፥ የበሪዓ ጅ፥ መልኪኤል ( 46: 17)
ሚካኤል ~ Michael: አም ልክ እና አም ልክተኛ ሚሉ መንታ ትርጉሞች አሉት። [ተዛማጅ ስም/ ስሞች- መልኪኤል መልክያ ሚካያ ሚክያስ...]
መልከ ኤል ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ሲሆን ትርጉሙመልከ ኤልሁኖ፥ አምላክን የመሰለ ማለት ነው።  
መላከ ኤል ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ሲሆን፥ ትርጉሙመላከ ኤልሁኖ፣ የጌታ መላክ፣ የአምላክ መልክተኛ፣ እግዚአብ አገልጋይ... ማለት ነው።
Michael: “Michael” means who is like God., SBD,
በመጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ስም የሚታወቁ አሥር ሰዎች እና አንድ መልዓክ አሉ፥የሰቱር አባት፥ ሚካኤል ከአሴር ነገድ ሚካኤል ልጅ ሰቱር (ዘኁ 1313) ከጋ ወገን፥ በባሳን ምድር ከተቀመጡ፥ ሚካኤል  (1 ዜና 5: 13) የኢዬሳይ ልጅ ሚካኤል  (1 ዜና 5: 14) የሳምዓ ልጅ፥ ሚካኤል (1 ዜና 6: 40) የይዝረሕያ ጅ፥ ሚካኤል (1 ዜና 7: 3) ብኒያማዊው የበሪዓ ጅ፥ ሚካኤል (1 ዜና 8: 16) ዳዊትም ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሳኦልን ሊወጋ በመጣ ጊዜ ከምናሴ ወገን ሰዎች ወደ ዳዊት ከከዱ ሚካኤል (1 ዜና 12: 20) የዖምሪ አባት፥ ሚካኤል (1 ዜና 27: 18) የኢዮሣፍጥ ጅ፥ ሚካኤል (2 ዜና 21: 2, 4) የሰፋጥያስ ጅ፥ ሚካኤል (ዕዝ 8: 8) ... ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል የፋርስ መንግሥት አለቃ ግን ሀያ አንድ ቀን ተቋቋመኝ እነሆም፥ ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ ...” (ዳን 1013) የመላእክት አለቃ (ይሁዳ 1: 9) ...
ሰላትያል ~ Salathiel, Shealtiel: ስለተ ኤል ከአምላክ የተጠየቀ፣ የጌታ ስለት ልጅ ማለት ነው።
Salathiel-ስለት እናኤል ከሚሉ ቃላት የተገኘ ስም ነው።
Salathiel: Whom I asked of God, EBD,
ሰላትያል, Salathiel: የምርኮኛው የኢኮንያን ሰላትያል፥ (ዜና 3: 17)
ሰላትያል, Shealtiel: በጌታ የዘር ሐረግ የተጠቀሰ፥ ኢኮንያን ልጅ፥ ( 1: 12) የኔሪ ልጅ፥ (ሉቃ 3: 7)
ሳሙኤል ~ Samuel: ሰማ ል፣ ሰማ አምላክ፣ ጌታ ሰማ እግዚአብሔር አዳመጠ፣ ፀሎትን ተቀበለ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ሽሙኤል]
ሰማ እና ኤል ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
[ሳሙ ኤል ማለት የእግዚአብሔር ስም አምላካዊ ስም ማለት ነው, የመ/ቅ መ/ቃ]
Samuel: heard of God, EBD,
የሕልቃና ልጅ፣ ል፥የመፅነስዋም ወራት ካለፈ በኋላ ሐና ወንድ ልጅ ወለደች እርስዋም፦ ከእግዚአብሔር ለምኜዋለሁ ስትል ስሙን ሳሙኤል ብላ ጠራችው: ” (1 1: 20)
እስማኤል ~ Ishmael: ሰማ ኤል አምላክ ሰማ፣ ፀሎትን ተቀበለ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም/ ስሞች- ይስማኤል ሳሙኤል...]
ሰማ እና ኤል ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
[ትርጉሙእግዚአብሔር ይሰማልማለት ነው, የመ/ቅ መ/ቃ]
Ishmael: “Ishmael” means whom God hears, SBD,
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች፥ አብር ልጅ፣ አጋር የተወለደው፥ የእግዚአብሔር መልአክም አላት፦ እነሆ አንቺ ፀንሰሻል፥ ወንድ ልጅንም ትወልጃለሽ ስሙንም እስማኤል ብለሽ ትጠሪዋለሽ፥ እግዚአብሔር መቸገርሽን ሰምቶአልና። (ዘፍ 1611) ...አብራምም አጋር የወለደችለትን የልጁን ስም እስማኤል ብሎ ጠራው” ( 16: 3 21: 5) የኤሴል ጅ፥ (1 ዜና 8: 38) የናታንያ ልጅ (ዘፍ 40: 8 15) ( 40: 8) ይሁ ወገን የሆነ፥ የዝባድያ አባት፥ ይስማኤል (2 ዜና 19: 11) ይሁ ወገን የሆነ፣ ዮዳሄ ወደ ዙፋን ለማድረስ የተባበረ፣ የይሆሐናንን ልጅ ይስማኤልን፥ (2 ዜና 23: 1) ዕዝራ ዘመን እንግዳ ሚስቶቻቸውን እንዲፈቱ ከተደረጉ፣ ካህኑ፥ ይስማኤል ይስማኤል፥ (ዕዝ 10: 22) ...
ዳንኤል ~ Daniel: ል፣ ዳኘ ኤል፣ አም ኘ፣ እግዚአብሔር ፈረደ ... ማለት ነው።
ዳኝ እናኤልከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
[ትርጉሙእግዚአብሔር ፈራጅ ነው ማለት ነው”, የመ/ቅ መ/ቃ]
Daniel: God is my judge, or judge of God, EBD,
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች፥ ከቀርሜሎሳዊቱ ከአቢግያ የተወለደው፣ የዳዊት ጅ፥ (1 ዜና 31) ኢታምር (ዕዝ 8: 2) ዳንኤልእነዚህ ሦስት ሰዎች፥ ኖኅና ዳንኤል ኢዮብም፥ ቢኖሩባት በጽድቃቸው የገዛ ነፍሳቸውን ብቻ ያድናሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦” (ሕዝ 14: 14) ( 1: 6) ( 1: 3 6) ከነህም  ጋር ቃል ኪዳን ዳቤ ካተሙት ( 10: 6) ...
 3.   ህያውያሕ (Jehovah, Jah, iah...)
ፍርዴን ያስወገደ ሕያው እግዚአብሔርን! ነፍሴንም መራራ ያደረገ ሁሉን የሚችል ሕያው አምላክን!” (ኢዮብ 27:2)
ቅዱስ እግዚአብሔር፣ ቅዱስ ኃያል፣ ቅዱስ ህያው ... እንዲ ቅዳሴያችን፥ ከእግዚአብሔ ባሕርያት አንዱ ዘለዓለማዊነቱ ነው።/ ያህየሚለው መጠሪያው፥ ህያውነቱን፤ የማይሞት የማያልፍነቱን የሚገልጽ ስሙ ነው።
እግዚአብሔርም ሙሴን። ያለና የሚኖር እኔ ነኝ አለው፤ እንግዲህ ለእስራኤል ልጆች።ያለና የሚኖርወደ እናንተ ላከኝ ትላለህ አለው።” (ዘጽ 3 14)
ነገር ግን ወደ ጽዮን ተራራና ወደ ሕያው እግዚአብሔር ከተማ ደርሳችኋል፥ ወደ ሰማያዊቱም ኢየሩሳሌም፥ በደስታም ወደ ተሰበሰቡት ወደ አእላፋት መላእክት፥” (ዕብራውያን12: 22)
እግዚአብሔር ለሰዎች ካሳወቀበት ስሞች መካከል አንዱ ህያው የሚለውን ነው።
ለእግዚአብሔር ተቀኙ ለስሙም ዘምሩ ወደ ምድረ በዳ ለወጣም መንገድ አድርጉ ስሙ እግዚአብሔር ነው፥ …” Jah- ( 68: 4)
()’ የሚጀምሩ ስሞች እና ፍቻቸው
እግዚአብሔር ~ Jah, Jehovah, God: ያህ ዌ፣ ህያዊ፣ ህያው አምላክ የማይሞት፣ የማያልፍ... ማለት ነው።
Jehovah -ያህዌ ከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው።
Jah: A contraction for Jehovah, HBN; The name “Jah” means the everlasting, EBD,
እግዚአብሔር, God:
·       ቀዳማትን እና ህያውነትን ል፥በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ” ( 1: 1)
·       ሁሉ ቦታ መገኘቱን ይገልጻል፥ ለእግዚአብሔር ተቀኙ ለስሙም ዘምሩ ወደ ምድረ በዳ ለወጣም መንገድ አድርጉ ስሙ እግዚአብሔር ነው፥ …” ~ by his name Jah- ( 68: 4)
·       እግዚአብሔር, Jehovah: ለአብርሃምም ለይስሐቅም ለያዕቆብም የተገለጠበት፥ ስሙን ያሳወቀበት፥ እግዚአብሔርም ሙሴን ተናገረው አለውም፦ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ለአብርሃምም ለይስሐቅም ለያዕቆብም ሁሉን እንደሚችል አምላክ ተገለጥሁ ነገር ግን ስሜ እግዚአብሔር አልታወቀላቸውም ነበር።” (ዘጸ 623)
Jehovah:  The unchanging, eternal, self-existent God, EBD; Jehovah” means I am; the eternal living one, SBD,
ለአብርሃምም ለይስሐቅም ለያዕቆብም ሁሉን እንደሚችል አምላክ ተገለጥሁ፤ ነገር ግን ስሜ እግዚአብሔር (Jehovah) አልታወቀላቸውም ነበር።” (ኦሪት ዘጸአት 6: 3)
“And I appeared unto Abraham, unto Isaac, and unto Jacob, by the name of God Almighty, but by my name Jehovah was I not known to them.” (Exod 6: 3)
Jehovah-shalom ~ እግዚአብሔር ሰላም: Jehovah send peace, EBD,
Jehovah-shammah ~ እግዚአብሔር በዚያ አለ: The name “Jehovah-shammah” means the Lord is there, HBN, [እግዚአብሔር ይሰማል)
Jehovah-tsidkenu ~ እግዚአብሔር ጽድቃችን (the word “Jehovah-tsidkenu” doesn’t found in the English bible): The name “Jehovah-tsidkenu” means the Lord our righteousness, EBD, HBN,
Jehozadak ~ ኢዮሴዴቅ: Jehozadak” means Jehovah justifies, SBD, (1 ዜና 614 15)
እግዚአብሔር ጽድቃችን ~ Jehovah-tsidkenu: ጻድቃኑ ያህዊ ጻድቅ፣ ህያው ጻድቅ፣ እውነተኛ አምላክ፣ ዘለለማዊ ገዥ... ማለት ነው።
(the word “Jehovah-tsidkenu” doesn’t found in the latest English bible versions)
The name “Jehovah-tsidkenu” means the Lord our righteousness, EBD, HBN,
Jehovah-tsidkenu-ያህዌ እና ጽድቅነ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ነው።
የህያው አምክነት ባህሪን ለመግለጽ የተሰጠ ስም፥ በዘመኑም ይሁዳ ይድናል እስራኤልም ተዘልሎ ይቀመጣል፥ የሚጠራበትም ስም። እግዚአብሔር ጽድቃችን ተብሎ ነው።” (ኢያ 236)
()’ የሚጨርሱ
ሃሌሉያ ~ Alleluia, Hallelujah, Praise ye the Lord: ሃሌ ያህ፣ ለህያው ጌታ ዘመረ፣ የአምላክን ስም ጠራ፣ እግዚአብሔርን አመሰገነ ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም/ ስሞች- ሂሌል ማህለህ ማህለት፣ ይሃሌልኤል]
ሃሌእናያህከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ቃል ነው።
ሃሌ’- ሃሎ፣ እልል ማለት፣ መጮህ፣ መጣራት፣ ማመስገን፣ መዘመር፣ መዝፈን ማለት ነው።
’- ያህ፣ ያህዊ፣ ህያው፣ ዘላለማዊ አምላክ፣ እግዚአብሔር ማለት ነው።
[ሃሌታና እልልታ በምስጢር አንድ ነው ሰብሑ፡ እግዚእ ሰብሑ፤ ያህ እግዚእ አምላክ, ኪወክ, ]
[በዕብራይስጥእግዚአብሔርን አመስግኑማለት ነው።, የመ/ቅ መ/ቃ]
ሃሌ ሉያ, Alleluia: ዮሐንስ በራእይ ያየውን ሲናገር የተጠቀመው ቃል፥ ( 1913 4 6)
ሃሌሉያ, Praise ye the Lord: ንጉሥ ዳዊት በመዝሙር ያመሰገነበት ቃል፥ ሃሌሉያ (መዝ 116: 19)
Alleluia: The name “Alleluia” means praise the Lord, HBN, ( 191 3 4 6) [Related name(s): Hallelujah]
በበኣል ይምሉ ዘንድ ሕዝቤን እንዳስተማሩ በስሜ፦ ሕያው እግዚአብሔርን! ብለው ይምሉ ዘንድ የሕዝቤን መንገድ በትጋት ቢማሩ፥ በዚያን ጊዜ በሕዝቤ መካከል ይመሠረታሉ።” (ኤር 10: 16)
እናንተ በግብፅ ምድር የምትኖሩ ይሁዳ ሁሉ፥ ስለዚህ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ በግብፅ ምድር ሁሉ በሚኖር በይሁዳ ሰው ሁሉ አፍ ስሜ ከእንግዲህ ወዲህ፦ ሕያው እግዚአብሔርን! ተብሎ እንዳይጠራ፥ እነሆ፥ በታላቅ ስሜ ምያለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር” (ኤር 44: 26)
ሊቢያ ~ Libya: በያ፣ ልበ አም ልብ፣ እግዚአብሔር የወደደው ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም/ ስሞች- ልባዎት ልብና ብድዮስ]
ልብ ሚሉ ቃላ የተገኘ ያገር ስም ነው።
Libya: The name “Libya” means the heart of the sea; fat, HBN,
በሰሜ ምሥ አፍሪ ሚግኝ (ግብፅን ምር) (ሐዋ 2: 10)
መልክያ ~ Malchiah, Malchijah, Melchiah: ያህ የህያው መልክ፣ ህያው አምላክ ጌታ እግዚአብሔር... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም/ ስሞች- መልኪኤል ሚካኤል ሚካያ ሚክያስ...]
መልከእና ያህ ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
Malchiah: Jehovah's king, EBD,
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች፥
መልክያ, Malchiah: ጳስኮር ት፥ መልክያ ( 38: 1) የጕድፍ መጣያውን በር ያደሰ መልክያ  ( 8: 4) ከወርቅ አንጥረኞቹ አንዱ፥ መልክያ ( 3: 31) የሬካብ ልጅ መልክያ ( 3: 14)
መልክያ, Malchijah: በዳዊት ዘመን፣ ለመቅደሱ ልግ ከተመደቡ፥ መልክያ  (ዜና 24: 9) በእግዚአብሔር ቤት ያመሰግኑ መካከል፥ መልክያ ( 12: 42) የካሪም ልጅ መልክያ ( 3: 11)
መልክያ, Melchiah: የጳስኮር ት፥ ካህኑ መልክያይህም የሆነው ንጉሡ ሴዴቅያስ። የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ይወጋናልና ስለ እኛ፥ እባክህ፥ እግዚአብሔርን ጠይቅ ከእኛም ይመለስ ዘንድ ምናልባት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር እንደ ተአምራቱ ሁሉ ያደርግ ይሆናል ብሎ መልክያ ልጅ ... ወደ ኤርምያስ በላከ ጊዜ ነው” ( 21: 1)
ሴዴቅያስ ~ Zedekiah, Zidkijah: ጸደቀ ያህ ጽድቀ ዋስ፣ ህያው ጻድቅ፣ እውነተኛ አምላክ፣ ድቅ አምላክ ማለት ነው።
Zedekiah, Zidkijah-ጽድቅ እና ህያው (ዋስ) ከሚሉ ቃላት የመጣ ስም ነው።
Zedekiah: righteousness of Jehovah., EBD, “Zedekiah” means justice of Jehovah, SBD,
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሴዴቅያስ  ተብለው የተጠሩ ሦስት አሉ። ለማገናዘብ እንዲረዳ ቀጥሎ  የቀረቡትን ጥቅሶች ማነጻጸር ይበጃል። 
ሴዴቅያስ, Zedekiah: የባቢሎን ንጉሥ የዮአኪን አጎት ማታንያን፥ ሴዴቅያስ ብሎ ጠራው፥ (2 ነገ 24: 18)
የክንዓና ልጅ (1 ነገ 22: 11)
ሴዴቅያስ, Zidkijah: ልኪኑን አት ከሰ አለቆች አንዱ፥ ህኑ ሴዴቅያስ (ነህ 10: 1)
አብያ ~ Abiah, Abijah: አባ ያህ አባቴ አምላኬ፣ ጌታዬ አምላኬ፣ ህያው አምላክ ዘላለማዊ ጌታ ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- አቢያ]
አብ እና ያህ(ያህዌ ህያው) ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
Abiah: The name “Abiah” means the Lord is my father, HBN
Abijah: “Abijah” means my father is Jehovah, SBD
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች፥
አብያ, Abiah: የነ ልጅ፥ (1 8: 2) ብኒያም ወገን፣ የቤኬር ጅ፥ (1 ዜና 78) ...
አብያ, Abijah: ከአልዓዛር ወገን፥ስምንተኛው አብያ ዘጠኝኛው ለኢያሱ፥(1 ዜና 2411) የሮብዓም ልጅ፥ (ዜና 12: 16) (ነገ 4: 21) የኢዮርብዓም ልጅ የመጀመው፥ (ነገ 14: 1) የኢዮርብዓም ልጅ ( 12: 4 17) (ዜና 24: 10) (ዜና 8: 14) በነህምያ ዘመ የነበረ  ህን፥ ( 10: 7) ...
ኢሳይያስ ~ Esaias, Isaiah: እሽ ያስ ሺህ ያህ፣ የሽዋስ የሽ ዋስ የብዙ ማለት ነው።
[እግዚአብሔር ደኅንነት ነው ማለት ነው።, የመ/ቅ መ/ቃ]
Isaiah: The salvation of Jehovah, EBD
1.     ኢሳይያስ, Esaias: የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ (ማቴ 33)
2.     ኢሳይያስ, Isaiah: (ኢሳ 11)
ኤልያስ ~ Eliah, Elijah: ኤል ዋስ፣ ኤል ያህ፣ ህያው ጌታ፣ ኃያ አምላክ፣ አም ማለት ነው።
Eliah, Elijah-ኤል እናያህ (ያህዌ) ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። [ትርጉሙእግዚአብሔር አምላክ ነውማለት ነው, የመ/ቅ መ/ቃ]
Eliah: “Eliah” means my God is Jehovah, SBD, whose God is Jehovah, EBD,
Elijah: whose God is Jehovah, EBD,
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች፥
ኤልያስ, Eliah:
ብንያማዊው የነገዱ አለቃ፥ (1 ዜና 827)
ዕዝ ዘመን እግዶች ሚስቶችን ካገቡ፣ ከካሪም ጅ፥ (ዕዝ 10: 21 26)
ኤልያስ, Elijah: የሞተ ልጅ ያስነሳ፣ ዝናም ለሁለት ዓመት እንዳይዘንብ ሰማይን የዘጋ፣ ኤልያስ (1 ነገ 171)
ጦብያ ~ Tobiah, Tobijah: ጹብ ህ፣ ጹብያ፣ ጦቢያ፣ እጦቢያ፣ ኢትዮጵያ፣ የህያው ቅዱሳን፣ ብሩካን፣ መልካሞች፣ ውቦች ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- አኪጦብ ጦብ ጦባዶንያ]
Tobiah, Tobijah-ጹብ እና ያህ (ያህዌ ህያው) ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
ጹብ- መልካም፣ ሰናይ፣ ቅዱስ፣ ብሩክ፣ ጻድቅ፣ ውብ...ማለት ነው።
Tobiah: pleasing to Jehovah, EBD; “Tobiah” means goodness of Jehovah, SBD
Tobijah: “Tobijah” means goodness of Jehovah, SBD,
ጦብያ, Tobiah: የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደ እየከተማቸው ከተመለሱ ( 7: 62)
ጦብያ, Tobijah: ንጉሥ ኢዮሳፍጥ ዘመ የእግዚአብሔርን የሕጉን መጽሐፍ ይዘው በይሁዳ ያስተምሩ ከነበር (2 ዜና 17: 8)
 4.   ዋስ (ቤዛ፣ አዳኝ፣ መድኃኒ ዓለም...)
እንዲሁ ኢየሱስ ለሚሻል ኪዳን ዋስ ሆኖአል።” (ዕብ 7: 22) ዋስ ማለት፥ ፈንታ፣ ምትክ፣ ቤዛ... ማለት ነው። ጌታ ኢየሱስ አዳምን ከዘላለም ሞት ያዳነው፥ የአዳም ምትክ በመሆን የአዳምን ቅጣት በመቀበል ነው። ስለዚህም ኢየሱስ በሚለው ስም ውስጥዋስየሚል ስም እና ቤዛ የሚል ፍች ቃል አለ ማለት ነው።
እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፥ ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አፈለሰን።” (ቆላ 113-14)
እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን” (ኢሳ 535) እሱ ህመማችንን ታመመ፤ በአዳም ፋንታ ቆሰለ።
እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ።” (ኢሳ 536) አጥፊው ነጻ ሲወጣ ዋሱ በአጥፊው ፋንታ ይቀጣል።
ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?(ማቴ 1626) ገንዘብ ላጎደለ፥ ዋሱ ገንዘብ ይከፍላል፤ ነፍስ ላጎደለ ደግሞ፥ ዋሱ በነፍስ ይከፍላል ማለት ነው። እንዲሁም የሰው ልጅ ሊያገለግል ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።ማቴ 2028
ሰውስ ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል? (ማር 837) ለእስራኤል ህዝብ ነፍስ መዳን፤ የጌታ ኢየሱስ ነፍስ ቤዛ ሆነ።
የእስራኤል ጌታ አምላክ ይባረክ፥ ጐብኝቶ ለሕዝቡ ቤዛ አድርጎአልና፤” (ሉቃ 1: 68)
ራሱንም ለሁሉ ቤዛ ሰጠ፥ ይህም በገዛ ዘመኑ ምስክርነቱ ነበረ፤(1 ጢሞ 26) እንኳንስ ለህዝብ ሁሉ ነፍስ ይቅር እና የአንድን ሰው ነፍስ ዋጋ ለመክፈል የምችል ሰው ስለሌለ፤ ራሱ እግዚአብሔር ከፈለ እንላለን።
ሖሳ ~ Hosah: ዋሴ ስ፣ ዋስትና፣ አዳኝ፣ ነጻ አውጭ፣ መጠጊያ ማለት ነው።
ዋሰ (ወሐሰ) ከሚለው ግስ የመጣ ስም ነው።
Hosah:  “Hosah” means refuge, SBD ... [Related name(s): Hosea, Hoshea]
በዚህ ስም የሚጠሩ አንድ ሰው እና አንድ ቦታ አሉ።
የመራ ወገን የሆነው፣ በረኛ ሖሳ (1 ዜና 16: 38)
በአሴር ወገን ድንበር የሆነ የቦታ ስም፥ ሖሳ (ኢያ 19: 29)
ሆሣዕና ~ Hosanna: ዋሴ ና፣ አዳኘ ና፣ ጠባቂዬ ድረስማለ ነው።
[አድነና፥ አድነንኮ፡ እባክኽ አድነን... መድኅኒትነት፤ መሆን ወይም መባል።, ኪወክ, ]
ዋስ እና ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ቃል ነው።
Hosanna:  Save now!, EBN, The name “Hosanna” means save I pray thee; keep; preserve, HBN,
ጌታ ወደ ኢየሩሳሌም በገባ ጊዜ ጻና ካዜሙት ል፥ ሆሣዕና “...ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር። (ማቴ 219)
ሆሴዕ ~ Hosea: ዋሴ፣ አዳኜ፣ መድኀኒቴ... ማለት ነው።
Hosea: The name “Hosea” means savior; safety, HBN,
ከደቂቀ ነቢያት አንዱ፥ የበሪ ልጅ...በእስራኤልም ንጉሥ በዮአስ ልጅ በኢዮርብዓም ዘመን ወደ ብኤሪ ልጅ ወደ ሆሴዕ የመጣ የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው። (ሆሴ 1: 12) [አድኀነ ባልሐ፥ ረድአ፥ አውፅኣ፥ እመሥገርት ማለት ነው። / ኪወክ / ]
ሆሻማ ~ Hoshama: ሆሴ ሰማ፣ ዋሴ ሰማ፣ ዳኘ ሰማ፣ አምላኬ አዳመጠኝ... ማለት ነው።
ዋስ እና ሰማ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተገኘ ስም ነው።
የምርኮኛው የኢኮንያ ጅ፥ ሆሻማ ፈዳያ፥ ሼናጻር፥ ይቃምያ፥ ሆሻማ ነዳብያ ነበሩ። (1 ዜና 318)
Hoshama:  The name “Hoshama” means heard; he obeys, HBN; Whom Jehovah hears, SBD,
ሙሴ ~ Moses: መዋሴ፣ መዋስ፣ ዋስ መሆን፣ ችግር ማዳን፣ ት፥ ከእስራት ነጻ ማውጣት፣ ከሞት ማዳን... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም - ሙሲ]
ዋሰ (ወሐሰ)ከሚለው ግስ የተገኘ ስም ነው።
Moses: The name “Moses” means taken out; drawn forth, HBN
ሊቀ ነብያት ሙሴ፥ሕፃኑም አደገ፥ ወደ ፈርዖንም ልጅ ዘንድ አመጣችው፥ ለእርስዋም ልጅ ሆነላት። እኔ ከውኃ አውጥቼዋለሁ ስትልም ስሙን ሙሴ ብላ ጠራችው።” (ዘጸ 210) (ሐዋ 7: 22)
ሉቃስ ~ Lucas, Luke: ሊቅ ስ፣ ሊቅ፣ ቂ፣ አስተዋይ፣ የተማረ ቀዳሚ፣ መንገድ መሪ፣ አስተማሪ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም/ ስሞች- ሉክዮስ ሉቂዮስ ሊቅሒ፣ ሌካ]
ሊቅ እና ዋሰ (ወሐሰ) ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
Lucas:  Luminous; white, HBN; Luke, SBD ... [Related name(s): Lecah, Likhi, Lucius, Luke]
Luke:  “Luke” means light-giving, SBD ... [Related name(s): Lecah, Likhi, Lucas, Lucius]
ሉቃስ, Lucas: ቅዱስ ነበረ ሉቃስ (ፊል 1: 24)
ሉቃስ, Luke: ሐኪም የነበረ፣ ሐዋርያው ሉቃስ፥ (ቆላ 4: 14)
ሉክዮስ ~ Lucius: ሊቅ ስ፣ አዋቂ፣ አስተዋይ፣ የተማረ፣ መንገድ መሪ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም/ ስሞች- ሉቃስ ሉቂዮስ ሊቅሒ፣ ሌካ]
ሊቅ እና ዋስ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተገኘ ስም ነው።
Lucius: Light-giving, SBD
በአንጾኪያ ባለችው ቤተ ክርስቲያን ነቢ መምህ የነበረ ሉክዮስ (ሐዋ 13: 1)
መልእክት ወደ ሮሜ ሰዎች የጻፈ ጤርጥዮስ የጠቀሰው አገልጋይ፥ ሉክዮስ (ሮማ 16: 21)
ማቴዎስ ~ Matthew: ዋስ፣ ቲው፣ ማቲ፣ ብዙ ዋስ ብዙዎችን የሚያድን ማለት ነው።
ማቲእና ዋስ ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
Matthew: Gift of God, EBD; The name “Matthew” means given; a reward, HBN,
ጌላ አንዱ፥ ቀራጩ ማቴዎስ ( 9: 9)
እልፍዮስ ~ Alphaeus: እልፍ ዋስ፣ የሽሕዎች ዋስ፣ የብዙዎ አዳኝ ማለት ነው።
እልፍእና  ዋስ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
Alphaeus (Alpheus) “Alphaeus” means changing, SBD, The name “Alpheus” means a thousand; learned; chief, HBN,
ከአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት የአንዱ የያዕቆብ አባት፥ (ማቴ 10: 30)
ዘኬዎስ ~ Zacchaeus: ዘኬዎስ፣ ዘኬ ዋስ፣ ዝክር፣ ታዋ በጸሎት የሚያስብ ማለት ነው።
ዘኬ እና ዋስ ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። [ተዛማጅ ስሞች : ዘኩር ዘካርያስ ዘካይ ዘኬዎስ ዛኩር...]
ኢየሱስ በቤ ተናገደ የቀራጮች አለቃ ( 19: 2)
Zacchaeus - “Zacchaeus” means pure, SBD,
ኤልያስ ~ Eliah, Elijah: ኤል ዋስ፣ ኤል ያህ፣ ህያው ጌታ፣ ኃያ አምላክ፣ አም... ማለት ነው።
Eliah, Elijah-ኤል እናያህ (ያህዌ) ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
[ትርጉሙእግዚአብሔር አምላክ ነውማለት ነው, የመ/ቅ መ/ቃ]
Eliah: “Eliah” means my God is Jehovah, SBD,
Elijah: whose God is Jehovah, EBD,
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች፥
ኤልያስ, Eliah: ብንያማዊው የነገዱ አለቃ፥ (1 ዜና 827) ዕዝ ዘመን እግዶች ሚስቶችን ካገቡ፣ ከካሪም ጅ፥ (ዕዝ 10: 21 26) ...
ኤልያስ, Elijah: የሞተ ልጅ ያስነሳ፣ ዝናም ለሁለት ዓመት እንዳይዘንብ ሰማይን የዘጋ፣ ኤልያስ (1 ነገ 171)
ኢያሱ ~ Hoshea, Jehoshua, Jeshua, Jesus, Joshua: የሽሕዋ፣ ያህሽዋ ሽሕስ፣ የሽዎች ጌታ፣ የብዙሃን አምላክ፣ የሽዎች አዳኝ፣ የብዙዎች ነጻነት ሰጭ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ሆሴዕ ኢየሱስ]
የሽህ እናዋስ ከሚሉት ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
[እግዚአብሔር ያድናል አዳኝ ማለት ነው, የመ/ቅ መ/ቃ]
Hoshea: Hoshea” means salvation, SBD
Jehoshua: “Jehoshua” means whose help is Jehovah; Help of Jehovah or savoiur, SBD
Jeshua (h): A savior, EBD; Jeshua” means a saviour, SBD
Jesus: Joshua, EBD; the name “Jesus” means savior; deliverer, HBN,
Joshua: “Joshua” means saviour, or whose help is Jehovah, SBD
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች፥
ኢያሱ, Hoshea: የነዌ ልጅ (ዘዳ 3244) የዓዛዝያ ልጅ ሆሴዕ- (ዜና 27: 20) ከነህምያ ጋር የቃል ኪዳኑን ደብዳቤ ያተመ፥ ሆሴዕ- ( 10: 23)
ኢያሱ, Jehoshua: ከኤ ነገድ የሆነ፥ የነዌ ልጅምድሪቱን ይሰልሉ ዘንድ ሙሴ የላካቸው ሰዎች ስም ይህ ነው። ሙሴም የነዌን ልጅ አውሴ ኢያሱ ብሎ ጠራው” (ዘኁ 1316) (ዜና 7: 27)
ኢያሱ, Jeshua: ለዘጠነኛ ሊቀ ካህናት የነበረ፥ ኢያሱ (ዕዝ 2: 36) (1 ዜና 24: 11) በንጉሡም በሕዝቅያስና በእግዚአብሔር ቤት አለቃ በዓዛርያስ ትእዛዝ በካህናቱ ከተሞች በየሰሞናቸው ክፍላቸውን በእምነት ይሰጡ ከተመደቡ፥ (2 ዜና 31: 15) የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደ እየከተማቸው ከተመለሱት የአገር ልጆች (ዕዝ 2: 6 ዕዝ 7: 11) የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደ እየከተማቸው ከተመለሱት የአገር ልጆች (ዕዝ 2: 40  7: 43) ዊያዊ፥ (ዕዝ 8: 33) ከባቢሎን መልስ የኢየሩሳሌምን ቅጥር ካደሱ፥ ( 3: 19) ዕዝራ የእግዚአብሔር ማወቅ ያስተምር የእግዚአብሔርን ሕግ መጽሐፍ ካአነበቡ ( 8: 7 9: 45) ይሁ ከተማ፥ኢያሱ በሞላዳ፥ በቤትጳሌጥ፥ በሐጸርሹዓል፥( 11: 26) የቀድምኤል ልጅ ( 12: 24) ...
ኢያሱ, Jesus: ከሐዋርያው ጳውሎስ ጋር በጉዞው ላይ የነበረ፥ (ቆላ 4: 11) በመቀጠል ሕዝበ እስራኤልን ወደ ቃልኪዳን አገራቸው የመራ፥ ኢያሱ አሳርፎአቸው ኖሮ ቢሆንስ፥ ከዚያ በኋላ ስለ ሌላ ቀን ባልተናገረ ነበር። (ዕብ 4: 8) ...
ኢያሱ, Joshua: የነዌ ልጅ አውሴ- (ዘጸ 17: 9) (ሐጌ 1: 112 2: 24 ዘካ 3: 13689)
·       እንዲህም አለ፦ እግዚአብሔር ዓለቴ አምባዬ መድኃኒቴ ነው፤” (2 ሳሙ 22: 2)
·       ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና መድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤” (ቲቶ  2: 12-13)
·       እኛም አይተናል አባትም ልጁን ዓለም መድኃኒት ሊሆን እንደ ላከው እንመሰክራለን።” (1ዮሐ 4: 14)
·       እንዲሁ የሰው ልጅም ሊያገለግልና ነፍሱን ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።” ~ ransom (የማርቆስ ወንጌል 1045)
·       እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፥ ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አፈለሰን።” ~ delivered (ቆላ 113-14)
·       አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ፤ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።” ~ salvation (ትንቢተ ዘካርያስ 99)
ምዕራፍ ሁለት
 ኢትዮጵያዊ የሰው ስሞች
በዚህ ምዕራፍ፥ የጌታን፣ የአበውን፣ የነብያትን፣ የሐዋርያትን... ስሞች፥ ፍች እና ስርዎ ቃላት፥ ከኢትዮጵያውያን ቋንቋ ጋር በተገናኘ፤ ለመመርመር፣ ለማብራራት እና ለማጥናት እንሞክራለን።
·       ነጠላ (አንድ) ቃል (ስሞች)
·       ጥምር (ድርብ) ቃላት (ስሞች)
·       ሥሉስ (ሦስት) ቃላት (ስሞች)
 ነጠላ ቃል ስሞች
ከአንድ ቃል ወይም ግስ የተገኙ ስሞች እና ፍቻቸው።
መምሬ ~ Mamre: ሪ፣ መም ምህር፣ መሪ፣ አስተማሪ... ማለት ነው።
Mamre: manliness, SBD,
መሪ ከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው።
አብርም፥ በኬ ያረፈበ የቦታ ስም፥ ( 14: 13 24)
ሴም ~ Sem, Shem: ሴም፣ ስም፣ ዝና፣ እውቅና... ማለት ነው።
The name “Sem” means same as Shem, HBN; Name, SBD, “Shem” means name, SBN,
ስም ከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው። ሰየመየሚለው ግስም መሰርት ነው።
ሴም, Sem: ከሦስቱ የኖ አንዱ ስም፥ ( 3: 36)
ሴም, Shem: የኖኅ ልጅ፥ ( 5: 32)
ሴት ~ Seth, Sheth: ሴተ ሰጠ፣ ተካ ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ሤት]
Seth: Appointed, compensation, EBD,
Sheth: “Sheth” means compensation, SBD,
ሰጠከሚለው ግስ የመጣ ስም ነው።
ሴት, Seth: ተኛ ልጅ፥አዳም ደግሞ ሚስቱን አወቀ ወንድ ልጅንም ወለደች። ስሙንም፦ ቃየን በገደለው በአቤል ፋንታ እግዚአብሔር ሌላ ዘር ተክቶልኛል ስትል ሴት አለችው። ( 4: 25) ( 4: 25 6: 3) (ዜና 1: 1)
ሤት, Sheth: ( 24: 17)
አሞጽ ~ Amos, Amoz: አመጽ፣ አመጻ፣ በደል፣ ግፍ፣ ተቃውሞ፣ ውንብድናማለት ነው። [ተዛማጅ ስም/ ስሞች- አማሢ፣ አማሲ፣ አማሳይ፣ ዓማሣይ፣ አማስያ፣ ዓማስያ፣ አሜሳይ፣ ዓሜሳይ፣ አሜስያስ...]
አመጸከሚለው ግስ የመጣ ስም ነው።
Amos:  borne; a burden, EBD
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች፥
በይሁዳ ንጉሥ በዖዝያን ዘመን፥ በእስራኤልም ንጉሥ በዮአስ ልጅ በኢዮርብዓም ዘመን የነበረ ነብይ፥ (አሞ 11)
የነብዮ ኢሳይያስ አባት፥ (2 ነገ 19220) (2 ነገ 19: 2 20 20: 1 ኢሳ 1: 1 2: 1)
ኤፍሬም ~ Ephraim: የፍሬያም ፍሬያም፣ ፍርያማ፣ ዘረ ብዙ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም/ ስሞች- ኤፍራታ ኤፍሮን ኦፊር ፉራ ፍሬ]
ፍሬያም ከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው። የስሙ ምንጭ ፍሬ የሚለው ቃል ነው።
Ephraim: The name “Ephraim” means fruitful; increasing, HBN,
ግብፅ የተወለደው፣ የዮሴፍ ልጅ፥ የሁለተኛውንም ስም ኤፍሬም ብሎ ጠራው፥ እንዲህ ሲል፦ እግዚአብሔር በመከራዬ አገር አፈራኝ (ዘፍ 4152)
            ያቆብ ~ Jacob: ያቅብ፣ ያስቀር፣ ይጠብቅ፣ ያግድ፣ ይከልክል... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም/ ስሞች- ያዕቆባ ያዕቆብ] [ትርጉሙተረከዝን ይይዛልማለት ነው, የመ/ቅ መ/ቃ]
አቀበ ከሚለው ግስ የተገኘ ስም ነው።
Jacob: one who follows on another's heels; supplanter, EBD,
ይስ ልጅ፥ራሔልም ለያዕቆብ ልጆችን እንዳልወለደች ባየች ጊዜ በእኅትዋ ቀናችባት ያቆብንም። (ዘፍ 31: 1)
ያዕቆብ ከዚያም በኋላ ወንድሙ ወጣ፥ በእጁም የዔሳውን ተረከዝ ይዞ ነበር፤ ስሙም ያዕቆብ ተባለ። እርስዋ ልጆችን በወለደቻቸው ጊዜ ይስሐቅ ስድሳ ዓመት ሆኖት ነበር። (ዘፍ 2526)
ይስሐቅ ~ Isaac: ይሳቅ ይስሐቅ፣ መሳቅ፣ ፈገግታ ማሳየት፣ ጥርስን በደስታ መግለጥ... ማለት ነው። [ትርጉሙይስቃልማለት ነው, የመ/ቅ መ/ቃ]
ሳቀ ከሚለው ግስ የመጣ ስም ነው።
Isaac: “Isaac” means laughter, SBD,
የአብርሃም እና ሣራ ልጅ አብርሃምም የተወለደለትን ሣራ የወለደችለትን የልጁን ስም ይስሐቅ ብሎ ጠራው። (ዘፍ 211-3) ሣራም፦ እግዚአብሔር ሳቅ አድርጎልኛል ይህንንም የሚሰማ ሁሉ በእኔ ምክንያት ይስቃል አለች።” (ዘፍ 216)
ደሊላ ~ Delilah: ደልላ፣ ደላላ፣ መደለል፣ ማባበል፣ ማግባባት፣ ማስማማት፣ ማደራደር... ማለት ነው።
ደለለ ከሚለው ግስ የተገኘ ስም ነው።
Delilah: Delilah” means languishing, SBD,
በሶሬቅ ሸለቆ የነበረች ፍልስጤማዊት ት፥ ሶምሶን የወደዳት፥ (መሣ 16: 4)
ዳን ~ Dan: ን፣ ዳኝ፣ ዳኛ፣ ዳኘ፣ ፈረደ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም/ ስሞች- ደና ዲና]
ዳኝ’  ከሚለው ቃል የተገኘ  ስም ነው። [ትርጉሙዳኛማለት ነው, የመ/ቅ መ/ቃ]
Dan: A judge, EBD; The name “Dan” means judgment; he that judges, HBN,
በዚህ ስም የሚታወቁ አንድ ሰውና አንድ ቦታ አሉ።
የቦታ ስም፥ ሌሳ ተባለች፥ አብራምም ወንድሙ እንደ ተማረከ በሰማ ጊዜ ... ፍለጋቸውንም ተከትሎ እስከ ዳን ድረስ ሄደ።” (ዘፍ 1414) ከተማይቱንም ከእስራኤል በተወለደው በአባታቸው ዳን ስም ዳን ብለው ጠሩአት የከተማይቱም ስም አስቀድሞ ሌሳ ነበረ።” (መሣ 18: 29)
የራሔል ባሪያ ባላ ለያቆ የወለደት፥ራሔልም። እግዚአብሔር ፈረደልኝ ቃሌንም ደግሞ ሰማ፥ ወንድ ልጅንም ሰጠኝ አለች ስለዚህ ስሙን ዳን ብላ ጠራችው: ” (ዘፍ 306) ዳን በወገኑ ይፈርዳል፥ ከእስራኤል ነገድ እንደ አንዱ። (ዘፍ 49: 16)
ጦብ ~ Ishtob, Tob: ጡብ፣ ጹብ፣ ውብ፣ መልካም፣ ቅዱስ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- አኪጦብ ጦብያጦባዶንያ]
Ishtob- ሽህ እና ጹብ ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
Ishtob, Tob: “Ishtob” means men of Tob, SBD,
ጦብ, Ishtob: የአገር ስም፥ (2 ሳሙ 1068)
ጦብ, Tob: የልዩ ሴት ልጅ ነህና በአባታችን ቤት አትወርስም ብለው ዮፍታሔ ያሳዱት የሸሸበ አገር፥ ( 11: 3 5)
 ድርብ ቃል ስሞች
የድርብ ስሞች ማለት፥ የሰውንና የሰውን፣ የሰውና የቦታን፣ የሰውን እና ያምላክን ... ያጣመሩ ማለት ነው።
መልከ ጼዴቅ ~ Melchisedec, Melchizedek: ስሙ ምንጭ መንታ (ሁለት) ሲሆን፥ ትርጉሙም ሁለት ነው። ይኽውምመላክእናየሚሉት ናቸው። [የጽድቅ ንጉሥ, የመ/ቅ መ/ቃ]
መልክ እና ጼዴቅ ከሚሉ ቃላት የተገኘውመልከ ጼዴቅየሚለው ስም ነው። ትርጉሙም፡ መልከ ጼዲቅ፣ የእውነት መልክ የአምላክ መልክ፣ የጌታ አምሳያ... ማለት ነው።
መላክ እና ጽድቅ ከሚሉ ቃላት የተገኘውመላከ ጽድቅየሚለው ስም ነው። ትርጉሙም፡ መላ ጻድቅ መላክ፣ የጽድቅ መላክተኛ... ማለት ነው።
Melchisedec, Melchizedek: “Melchisedec” means king of righteousness, SBD,
The name “Melchizedek” means king of justice, HBN, “Melchizedek” means king of righteousness, SBD,
መልከጼዴቅ, Melchisedec: የሳሌም ንጉሥና የልዑል እግዚአብሔር ካህን “...አንተ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ካህን ነህ ይላል። (ዕብ 5: 6)
መልከጼዴቅ, Melchizedek: አብርሃም ኮሎዶጎምርንና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ነገሥታት ወግቶ ከተመለሰ በኋላ ተቀ የባረከው፥ አስትንም አብር የተቀበለ ንጉሥና ካህን፥ ( 14: 18-20)
ማርታ ~ Martha: መሪ እታ፣ መሪ እህት፣ የመጀመሪያ ሴት ልጅ፣ ታላቅ እህት... ማለት ነው።
መሪ እናእታከሚሉ ቃላት የተገኘ ስም ነው።
Martha: “Martha” means a lady, SBD,
የአላዛርና የማሪያም እህት፥ ማርታ (ሉቃ 10: 38)
ሳሙኤል ~ Samuel: ሰማ ል፣ ሰማ ኃያል፣ ሰማ አምላክ፣ ጌታ ሰማ እግዚአብሔር አዳመጠ፣ ፀሎትን ተቀበለ ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- ሽሙኤል እስማኤል...] [ሳሙ ኤል ማለት የእግዚአብሔር ስም አምላካዊ ስም ማለት ነው, የመ/ቅ መ/ቃ]
ሰማ እና ኤል ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
Samuel: heard of God, EBD,
የሕልቃና ልጅ፣ ል፥የመፅነስዋም ወራት ካለፈ በኋላ ሐና ወንድ ልጅ ወለደች እርስዋም፦ ከእግዚአብሔር ለምኜዋለሁ ስትል ስሙን ሳሙኤል ብላ ጠራችው: ” (1 1: 20)
በኣል ሻሊሻ ~ Baal-shalisha: በዓለ ሽላሼ በዓለ ላሴ፣ ላሴ በዓል፣ ሦስትነት... ማለት ነው።
በዓል እና ሥላሴ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተገኘ ስም ነው።
Baal-shalisha: The name “Baal-shalisha” means the god that presides over three; the third idol, HBN,
ለኤ ምግብና መጠጥ ያመጣ ሰው፥ የቦታ ስም፥ አንድ ሰውም በኣልሻሊሻ የበኵራቱን እንጀራ...” (2 ነገ 442)
ኤልያቄም ~ Eliakim: ቆም ኤል ቆመ፣ በአምላክ የጸና፣ እግዚአብሔር ያነሳው ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም/ ስሞች- ቀሙኤል ቁሚ አኪቃም አዶኒቃም ኢዮአቄም ዓዝሪቃም ያቂም ዮቂም ዮአቂም]  [ትርጉሙ እግዚአብሔር ያስነሳል ማለት ነው, የመ/ቅ መ/ቃ]
ኤል እና ቆመ ከሚሉት ሁለት የተመሠረተ ስም ነው።
Eliakim: whom God will raise up, EBD,
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች፥ የኬልቅያስ ልጅ (2 ነገ 1818) ( 36: 3) (ነገ 18: 18 26 37) በጌታ የዘ ሐረ የተጠቀሰ የዮናን ልጅ፥ (ሉቃ 330 31) (ማቴ 1: 13) የኢዮስያስ ልጅ የኢዮአክስ ንድም፥ ኢዮአቄም የቀድሞ ስም፥ (ዜና 36: 4) (ነገ 23: 34) በነህምያ ዘመን የነበረ ካህን፣ የኢየሩሳሌም ግንብ በማደስ የተባበረ፥ ( 12: 41) ...
ዘማራይም ~ Zemaraim: ዘማሪያም ማሪያማዊ፣ የማሪያም ወገን፣ የማሪያም አገር ማለት ነው።
እናማሪያም ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
Zemaraim: “Zemaraim” means double fleece of wool, SBD,
ከብንያም ልጆች ነገድ ከተሞች አንዱ፥ቤትዓረባ፥ ዘማራይም ቤቴል፥ ( 18: 22) (2 ዜና 13: 4-20)
ጥበልያ ~ Tebaliah: ጠበለ ያህ፣ ጸበለ ያህ፣ ቅዱስ ጸበል፣ ህያው ውኃ ማለት ነው።
ጸበል እና ያህ(የህዌ ህያው) ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
Tebaliah: The name “Tebaliah” means baptism, or goodness, of the Lord, HBN,
በእግዚአብሔር ቤት ያገለግሉ ዘንድ የበረኞች አለቆች ከሰሞነኞች የሖሳ ጅ፥ ጥበልያ (ዜና 26: 11)
ጦብያ ~ Tobiah, Tobijah: ጹብ ህ፣ ጹብያ፣ ጦቢያ፣ እጦቢያ፣ ኢትዮጵያ፣ የህያው ቅዱሳን... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- አኪጦብ ጦባዶንያ]
Tobiah, Tobijah: ጹብ እና ያህ (ያህዌ ህያው) ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
Tobiah, Tobijah: “Tobijah” means goodness of Jehovah, SBD ... [Related name(s): - Tobadonijah, Tobiah]
ጦብያ, Tobiah: የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደ እየከተማቸው ከተመለሱ ( 7: 62)
ጦብያ, Tobijah: ንጉሥ ኢዮሳፍጥ ዘመ የእግዚአብሔርን የሕጉን መጽሐፍ ይዘው በይሁዳ ያስተምሩ ከነበር (2 ዜና 17: 8 2 ዜና 17: 8)
 ሥሉስ ቃላት ስሞች
ሥሉስ ስሞች የሚመሰረቱት፥ የአምለክን እና  የሰውን፣ የአምላክን ሁለት ስሞች፣ የሰውን እና የሰውን ስሞች...  በማገናኘት የድርጊትን ወይም የግብርን መግለጫ፥ አለዚያም የሌላን ነገር ስም በመጨመር ይሆናል።
ብልጣሶር ~ Belshazzar: ባለ ሽህ ር፣ ባለብዙ ዘር፣ ሀብታም ኃያ... ማለት ነው።
Belshazzar-ባለ ሽህ እና ዘር ከሚሉ ስት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
Belshazzar: The name “Belshazzar” means master of the treasure, HBN,
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች፥ የጃንደረቦች አለቃ አስፋኔዝ ወደ ከተማረጉት ለዳ ያወጣለ ስም፥የጃንደረቦቹም አለቃ ስም አወጣላቸው ዳንኤልን ብልጣሶር …” (ዳን 1: 7) የባቢሎን ንጉሥ፥ንጉሡ ብልጣሶር  ለሺህ መኳንንቶቹ ትልቅ ግብዣ አደረገ፥ በሺሁም ፊት የወይን ጠጅ ይጠጣ ነበር። ( 5: 1) ...
ኤልሳቤጥ ~ Elisabeth, Elisheba: ኤል ሳባ ቤት፣ ኤል ሳቤት ኤል ሰባት፣ ምላክ ቤተሰብ፣ የጌታ ወገን ...ማለት ነው።
ኤል ሳባ እና ቤት ከሚሉ ሦስት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
Elisabeth, Elisheba:  “Elisabeth” means the oath of God, SBD ... [Related name(s): Elisheba]
The name “Elisha” means salvation of God, HBN ... [Related name(s): Elishah, Elishua...]
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የሚታወቁ ሰዎች፥
ኤልሳቤጥ, Elisabeth: ከአሮን ገን ስትሆን የዘካርያስ ሚስት፣ የመጥምቁ የዮሐንስ እናት፥ የጌታ እናት የማርያም አክስት፥ (ሉቃ 15)
ኤልሳቤጥ, Elisheba: የአሮን ሚስት፥ (ዘጸ 623)
ጦባዶንያ ~ Tobadonijah: ጹብ ዳኝ ያህ፣ ጦቢያዊ ህያው አዳኝ፣ ጹባዊ ህያው ጌታ፣ ቅዱስ አምላካ አዳኝማለት ነው። [ተዛማጅ ስም- አኪጦብ ጦብያ ጦብ ...]
Tobadonijah: The name “Tob-adonijah” means my good God; the goodness of the foundation of the Lord, HBN ... [Related name(s): Tobiah, Tobijah]
ጹብ ዳኛ እና ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
ንጉሥ ኢዮሳፍጥ ዘመ የእግዚአብሔርን የሕጉን መጽሐፍ ይዘው በይሁዳ እንዲያስተምሩ ከተላኩ፥ (2 ዜና 17: 8)
 
 
ምዕራፍ ሦስት
ኢትዮጵያዊ የቦታ ስሞች
ሰው በቦታ ስም ይጠራል፥ ቦታም ደግሞ በሰው ስም ይጠራል። እስራኤል የሚለውን ስም ብንወስድ፥ መጀመሪያ  የተሰጠው ለሰው ሲሆን፥ ያም ስም ለቦታው፥ ላገሩ መጠሪያ ሁኖ  እስከዛሬ ያገለግላል።
እንዲሁም፥ ቤተ ልሔም የሚለው ስም፥ የቦታ እና የሰው መጠሪያ ሆኖ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተመዝግቦ ይገኛል።
ሊቢያ ~ Libya: በያ፣ ልበ አም ልብ፣ እግዚአብሔር የወደደው... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም/ ስሞች- ልባዎት ልብና ብድዮስ]
ልብ ሚሉ ቃላ የተገኘ ያገር ስም ነው።
Libya: The name “Libya” means the heart of the sea; fat, HBN,
በሰሜ ምሥ አፍሪ ሚግኝ (ግብፅን ምር) (ሐዋ 2: 10)
ሎዛ ~ Luz: ለውዛ፣ ለውዝ፣ የለውዝ ተክል ማለት ነው።
Luz: A nut-bearing tree, the almond, EBD,
ቤቴል ተብላ የተጠራች፥ ጥን የከነዓን ከተማ ያዕቆብም ያንን ስፍራ ቤቴል ብሎ ጠራው አስቀድሞ ግን የዚያች ከተማ ስም ሎዛ ነበረ።(ዘፍ 28: 19 35: 6)
በኬጢያውያን የነበረ ቦታ ስም፥ “... ስምዋንም ሎዛ ብሎ ጠራት...” (መሣ 1: 26)
ቃዴስ ~ Kadesh, Kedesh: ቅዱስ፣ ለጌታ የተለየ የከበረ፣ የተባረከ የተመሰገነ... ማለት ነው። [ቅዱስ ማለት ነው, የመ/ቅ መ/ቃ]
Kadesh:  Holy, EBD, The name “Kadesh” means holiness, HBN,
Kedesh: “Kedesh” means a sanctuary, SBD,
በዚህ ስም የሚታወቁ ሦስት ቦታዎች አሉ።
ቃዴስ, Kadesh: እስራኤላ ግብፅ ከወ በኋላ ካለፋባቸ ቦታዎች፥መልሰውም ቃዴስ ወደ ተባለች ወደ ዓይንሚስፓጥ መጡ...” (ዘጸ 14: 7)
ቃዴስ, Kedesh: ይሁ በስተደቡብ ድንበር፥ ( 15: 23) ይሳኮር ነገድ የሰፈረበት፥  (ዜና 6: 72) ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ ( 19: 37)  (መሣ 4: 6)
            በኣል ሻሊሻ ~ Baal-shalisha: በዓለ ሽላሼ በዓለ ላሴ፣ ላሴ በዓል፣ ሦስትነት በዓል ... ማለት ነው።
በዓል እና ሥላሴ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተገኘ ስም ነው።
Baal-shalisha: The name “Baal-shalisha” means the god that presides over three; the third idol, HBN,
ለኤ ምግብና መጠጥ ያመጣ ሰው፥ የቦታ ስም፥ አንድ ሰውም በኣልሻሊሻ የበኵራቱን እንጀራ...” (2 ነገ 442)
በኣልጋድ ~ Baal-gad: ባለ ገድ አምላክ የረዳው፣ እድል የቀናው፣ ባለ እድል፣ እድለኛ... ማለት ነው።
በኣለ እና ገድ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ የቦታ ስም ነው።
Baal-gad: lord of fortune, or troop of Baal, EBD,
እግዚአብሔር ኢያሱን፥ በተራራማውም አገር የሚኖሩትን ሁሉ ከሊባኖስ ጀምሮ እስከ ማሴሮን ድረስ ሲዶናውያን ሁሉ እነዚህን ከእስራኤል ልጆች ፊት አባርራቸዋለሁ እንዳዘዝሁህም ምድራቸውን ለእስራኤል ርስት አድርገህ አካፍላቸው ያዘዘ የቦታ ስም፥ (ኢያ 135 11: 17 12: 7-8)
ቤተልሔም ~ Bethlehem: ቤተ ህም፣ የላሕም ቤት፣ የላም ቤት፣ የከብቶች ማደሪያ... ማለት ነው። [የእንጀራ ቤት ማለት ነው/ የመ/ቅ መ/ቃ]
ቤተ እና ላም ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
Bethlehem: “Bethlehem” means house of bread, SBD,
በዚህ ስም የሚታወቁ ቦታ እና ሰው፥
ያቆብ ከመስጴጦምያ በመጣ ጊዜ፥ ወደ ኤፍራታ ለመግባት ጥቂት ሲቀር በመንገድ ሳለ፥ራሔል በከነዓን ምድር ሞተችብኝ በዚያም በኤፍራታ መንገድ ላይ፥ እርስዋም ቤተ ልሔም ናት፥ ቀበርኋት...(ዘፍ 487) “...አንተም በኤፍራታ ባለ ጠጋ ሁን፥ ስምህም በቤተ ልሔም ይጠራ።” (ሩት 4: 11)
ጌታ ኢየሱስአንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ ...” ( 5: 2) (1  17: 12) ቤተልሔም ይሁ ( 2: 4) የዛብሎን ልጆች ርስት ቀጣት፥ ነህላል፥ ሺምሮን፥ ይዳላ፥ ቤተ ልሔም አሥራ ሁለት” ( 19: 15)
·       የካሌብ ልጅ፣ የሰልሞን ልጅ፥የቤተ ልሔም አባት ሰልሞን...” (1 ዜና 2: 51)
ኢትዮጵያ, Ethiopia, Cushan: ኢትዮጵያ ጦቢያ፣ ጹብ ጹብ ህ፣ ቅዱስ፣ ምድራዊ ገነት፣ መንፈሳዊ ዓለም... ማለት ነው። [ተለዋጭ ስም/ ስሞች- ኩሽ፣ ሳባ፣ አዜብ፣ ምድያም የደቡብ አገር፣ የአለም ዳርቻ]
Ethiopia, Cushan: The land of Cush, EBD, “Cushan” means blackness, SBD,
ኢትዮጵያ, Ethiopia: ኢት ግዮን ንዝ መገኛየሁለተኛውም ወንዝ ስም ግዮን ነው እርሱም ኢትዮጵያ ምድር ሁሉ ይከብባል።” (ዘፍ 213)
ኢትዮጵያ, Cushan: የአብርሃም ልጅ፥ የምድያም ር፣ ኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ አየሁ ምድያም አገር መጋረጃዎች ተንቀጠቀጡ” (እንባ 37)
ናዝሬት ~ Nazareth: ንጽት፣ ናጽራ ነጻ አነጣጣሪ፣ አስተዋይ፣ የወደፊቱን አርቆ የሚያይ፣ ብይ፣ ባህታዊ፣ መናኝ... ማለት ነው።
ነጸረ ከሚለው ግስ የመጣ ስም ነው።
[ትርጉሙ የተቀደሰ ማለት ነው, የመ/ቅ መ/ቃ]
Nazareth: netser, a "shoot" or "sprout." Some, however, EBD,
ለእስራኤል ልጆች ንገራቸው። ሰው ወይም ሴት ለእግዚአብሔር ራሱን የተለየ ያደርግ ዘንድ ናዝራዊነት ስእለት ቢሳል፥” ( 6: 2-21)
ናዝራዊነት መለያ ባሕርያት: -
ከወይን ጠጅና ከሚያሰክር መጠጥ ራሱን የተለየ ያድርግ ከወይን ወይም ከሌላ ነገር የሚገኘውን ሆምጣጤ አይጠጣ፥ የወይም ጭማቂ አይጠጣ የወይን እሸት ወይም ዘቢብ አይብላ።
ራሱን ለመለየት ስእለት ባደረገበት ወራት ሁሉ በራሱ ላይ ምላጭ አይደርስም ለእግዚአብሔር የተለየበት ወራት እስኪፈጸም ድረስ የተቀደሰ ይሆናል፥ የራሱንም ጠጕር ያሳድጋል
ለእግዚአብሔር ራሱን የተለየ ባደረገበት ወራት ሁሉ ወደ ሬሳ አይቅረብ።
ለአምላኩ ያደረገው እስለት በራሱ ላይ ነውና አባቱ ወይም እናቱ ወይም ወንድሙ ወይም እኅቱ ሲሞቱ ሰውነቱን አያርክስባቸው።ራሱን የተለየ ባደረገበት ወራት ሁሉ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ነው
ሰውም በአጠገቡ ድንገት ቢሞት የተለየውንም ራሱን ቢያረክስ፥ እርሱ በሚነጻበት ቀን ራሱን ይላጭ በሰባተኛው ቀን ይላጨው።
ካህኑም አንዱን ለኃጢአት መሥዋዕት ሁለተኛውንም ለሚቃጠል መሥዋዕት ያቀርበዋል በሬሳም የተነሣ ኃጢአት ሠርቶአልና ያስተሰርይለታል፥ በዚያም ቀን ራሱን ይቀድሰዋል
ራሱን የተለየ ያደረገበትን ወራትም ለእግዚአብሔር ይቀድሳል፥ የአንድ ዓመትም ተባት ጠቦት ለበደ መሥዋዕት ያምጣ ናዝራዊነቱ ግን ረክሶአልና ያለፈው ወራት ሁሉ ከንቱ ይሆናል
ኤፍራታ ~ Ephrath, Ephratah: የፍሬያት ያፍራ ያብዛ፣ ያበርክ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም/ ስሞች- ኤፍሬም ኤፍሮን ኦፊር ፉራ ፍሬ]
ፍሬያት ከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው።
Ephrath, Ephratah:  The name “Ephratah” means abundance; bearing fruit, HBN; Fruitful, EBD
ከቤቴ መለ ያረፈበ ቦታ (ዘፍ 3516)
የካሌ ሚስት፥... ካሌብም ኤፍራታ አገባ እርስዋም ሆርን ወለደችለት። (1 ዜና 2: 50) የቤተ ልሔም አባት (1 ዜና 4: 4)
ፍልስጥኤም ~ Philistines: ፍልሰታም፣ ፍልሰታ፣ ፍልሰት፣ የፈለሰ፣ ፈላሻ፣ ከርስቱ ከግዛቱ የተፈናቀለ ማለት ነው።
ፍልሰታም ከሚለው ቃል የተገኘ ስም ሲሆን ምንጩ ደግሞፈለሰየሚለው ግስ ነው።
Philistines: “Philistines” means immigrants, SBD,
እስራኤልን ከግብፅ ምድር እንዳወጣ ሁሉ ፍልስጥኤማውያንንም ከከፍቶር ያወጣ እግዚአብ የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን? ይላል እግዚአብሔር፦ እስራኤልን ከግብፅ ምድር፥ ፍልስጥኤማውያንንም ከከፍቶር፥ ሶርያውያንንም ከቂር አላወጣሁምን?” (አሞ 9: 7)
በጌራራ ንጉሥ አቢሜሌክ ሥር ይተዳደር የነበር አገር፥በቤርሳቤህም ቃል ኪዳንን አደረጉ። አቢሜሌክና የሙሽራው ወዳጅ አኮዘት የሠራዊቱ አለቃ ፊኮልም ተነሥተው ወደ ፍልስጥኤም ምድር ተመለሱ። ( 21: 32)
 

No comments:

Post a Comment

ማውጫ

መግቢያ                                                                                                     ክፍል አንድ፡ ኢትዮጵያ እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ታ...