ክፍል አንድ

ኢትዮጵያ እና የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ
በዚህ ክፍል፥ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ ታዋቂ ሰዎችን እያነሳን፤ ህይወታቸው፥ እንዴት ከኢትዮጵያ ጋር የተቆራኘ እና የተሳሰረ እንደሆነ ለማየትና ለመመርመር ይሞከራል። ከምናነሳቸው ሰዎች መካከል ዋና ዋናዎቹ፣ አብርሃም፣ ሙሴ፣ ጌታ ኢየሱስ... እና ሌሎችም ናቸው።
 ምዕራፍ አንድ
 አብርሃም በኢትዮጵያ፥
 አብርሃም፥ በዚህ ምድር ከኖረበት አንድ መቶ ሰባ አምስት ዓመት፤ ከሰማኒያ አምስት አመቱ ጀምሮ፤ ቀሪውን ዘጠና ዓመት እድሜውን የኖረውና ሙቶ የተቀበረው፤ በዛሬዋ ኢትዮጵያ (በአዜብ ምድር፣ በምሥራቅ አፍሪካ...) ውስጥ ነው።
በቅድሚያ፥ አብርሃምና ቤተሰቡ፥ ወደቃል ኪዳን አገር/ ከነዓን (የዛሬዋ እስራኤል) ስለአለመግባታቸው፥ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ እንይ፥
አብርሃም የተባለው ርስት አድርጎ ሊቀበለው ወዳለው ስፍራ ለመውጣት በእምነት ታዘዘ፥ ወዴትም እንደሚሄድ ሳያውቅ ወጣ። ለእንግዶች እንደሚሆን በተስፋ ቃል በተሰጠው አገር በድንኳን ኖሮ፥ ያን የተስፋ ቃል አብረውት ከሚወርሱ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር፥ እንደ መጻተኛ በእምነት ተቀመጠ፤ (ዕብ 118 እና 9) “እነዚህ ሁሉ አምነው ሞቱ፥ የተሰጣቸውን የተስፋ ቃል አላገኙምና ዳሩ ግን ከሩቅ ሆነው አዩትና ተሳለሙት፥ በምድሪቱም እንግዶችና መጻተኞች እንዲሆኑ ታመኑ።(ዕብ 1113)
እነዚህም ሁሉ በእምነታቸው ተመስክሮላቸው ሳሉ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አላገኙም(ዕብ 1139)እነዚህ ሁሉ...’ የተባሉት፥ አብርሃምን፣ ይስሐቅን፣ ያቆብን፣ ሙሴ እና ሌሎችን አባቶች ማለት ነው።
ከቅዱስ ጳውሎስ በተጨማሪ፥ ቅዱስ እስጥፋኖስ፥ አብርሃም ወደ ቃል ኪዳን አገር፥ ወደ ከነዓን እንዳልገባ እንዲህ በማለት መስክሯል፥በዚችም የእግር ጫማ ስንኳ የሚያህል ርስት አልሰጠውም ነገር ግን ልጅ ሳይኖረው ለእርሱ ከእርሱም በኋላ ለዘሩ ርስት አድርጎ ይሰጠው ዘንድ ተስፋ ሰጠው።” (ሐዋ 7 4 እና 5)
እንግዲህ፥ አብርሃም ከግብጽ ከወጣ እና ከነዓን ካልገባ፥ አብርሃም የኖረው የት ነው? ብለን ስንጠይቅ፥ መልሱ የዛሬዋ ኢትዮጵያ ሆኖ እናገኘዋለን።
አብርሃም፥ ከከለዳውያን ዑር ተነስቶ፥ እግዚአብሔር ወደ አዘጋጀለት አገር ለመሄድ የወጣው፤ በዚያን ዘመን አዜብ ወደተባለችው የዛሬዋ ኢትዮጵያ ነው(ዘፍ129) ይህንም ቅዱስ ጳውሎስ፥ ወደ ዕብራውያን በላከው ደብዳቤ እንዲህ ብሎ ገልጾታል፥ አብርሃም ርስት አድርጎ ወደሚቀበለው ስፍራ እንዲሄድ በተጠራ ጊዜ በእምነት ታዘዘ፤ ወዴት እንደሚሄድ ባያውቅም፣ እሺ ብሎ ሄደ።” (ዕብ 118) ከከለዳውያን ዑር ተነስቶ፥ ከአባቱ ከታራን፣  ከወንድሙ ልጅ ከሎጥ እና ከሚስቱ ከሣራ ጋር ሁኖ ወደ ካራን ሄዱ። አባቱ ታራን፥ በካራን ሙቶ በዚያው ተቀበረ። ከካራን ተነስተው ደግሞ ወደ ከነዓን መጡ። [በዚያን ዘመን፥ ከነዓናውያን እና ፍልስጤማውያን በኢትዮጵያው ግዛት ስር ነበሩ።አቤሜሌክና የሙሽራው ወዳጅ አኮዜት ከዚያ ተነስተው ወደ ፍልስጤም ሄዱ።ዘፍ 2123]
አብርሃም ከከነዓን ተነስቶ ወደ ኢትዮጵያ ባደረገው ጉዞ፤ በርሃብ ምክንያት ወደ ግብፅ ወረደ። አብራምም ከዚያ ተነሣ፥ እየተጓዘም ወደ አዜብ ሄደ” ~ toward the south (ዘፍ 12: 9) 
በግብፅ የተወሰኑ ዓመታትን ከቆዩ በኋላ ወደ ዛሬዋ ኢትዮጵያ መጡ። አብራምም ከግብፅ ወጣ እርሱና ሚስቱ ለእርሱ የነበረውም ሁሉ ሎጥ ከእርሱ ጋር ወደ አዜብ ወጡ” (ዘፍ 131)
“...ከግብጽ ወጣየሚለው አገላለጽ፥ ግብጽን ትቶ ወደ ሌላ አገር መሄዱን ነው። ወጣ’ የሚለውም ቃል፥ ገባ ለሚለው ተቃራኒ ነው። በሌላ በኩል፥ “... ወደ አዜብ ወጡየሚለው አገላለጽ፥ ወደግብጽ ወረዱ ለሚለው ተቃራኒ ነው። ይህም ማለት፥ “...ወደ አዜብ ወጡ/ went upማለት፥ ከዝቅተኛ የመሬት አቀማመጥ፥ ወደ ከፍተኛ የምድር አካል መሄድን ይጠቁማል።ወደ አዜብ ወጡየሚለው፥ ኢትዮጵያ ለግብፅ በስተደቡብ ብትሆንም፥ በከፍታ ከላይ ናት። ለዚህም ነው፥ ውኃ ከላይ ወደ ታች ስለሚፈስ፤ የአባይ ወንዝ ከኢትዮጵያ ወደ ግብፅ የሚፈሰው። በአንጽሩ ከኢትዮጵያ ወደ ግብፅ ሲሄዱ፤ወደግብፅ ወረዱይላል።ዮሴፍም ወደ ግብፅ ወረደ... (ዘፍ 391 ዘፍ 423 4315...) መጽሐፍ ቅዱስን የጻፉት፥ ኢትዮጵያውያን ቢሆኑ ኑሮ፥ከግብፅ ወጦ ወደ አዜብ ወጡሳይሆን፥ከግብፅ ወጦ ወደ አዜብ መጡይሉት ነበር።
አዜብ ባደረገው በጕዞውም ወደ ቤቴል በኩል ሄደ፤ ያም ስፍራ አስቀድሞ በቤቴልና በጋይ መካከል ድንኳን ተክሎበት የነበረው ነው፤” (ዘፍ 133) ቤቴል፥ የተባለው ስም ምንጩ፥ ቤተ ኃያል ከሚለው ሁኖ፥ ፍችውም የኃያል ቤት፥ የአምላክ ቤት፣ የእግዚአብሔር ቤት፣ ቤተ እግዚአብሔር ... ማለት ነው። የእግዚአብሔር ቤት ወይም ቤተ እግዚአብሔር የሚባል ነገር፤ ከእስራኤል በፊትም ሆነ ዛሬ የሚገኘው፤ በኢትዮጵያ (ብቻ) ነው። ዛሬ በዓለም ላይ፥ ቤቴል የሚባሉ ቦታዎች፥ ከሃምሳ ባላይ አሉ። በአሜሪካ ብቻ፥ ሰላሳ አራት፥ ቤተል በመባል የሚጠሩ ቦታዎች አሉ። ከእነዚህ ሁሉ የሚቀድመው ግን፥ ከአብርሃም በፊት የነበረችው፥ የኢትዮጵያዋ፥ ቤቴል ናት።
አብርሃም፥ በኬብሮን የሰፈረበት የመምህሬ ያአድባር ዛፍ የነበረው በዛሬዋ ኢትዮጵያ ነው። አብራምም ድንኳኑን ነቀለ መጥቶም በኬብሮን ባለው መምሬ አድባር ዛፍ ተቀመጠ፤ በዚያም ለእግዚአብሔር መሠውያን ሠራ።” (ዘፍ13:18)
ዛሬ በእስራኤል የሚገኘው ኬብሮን የተሰየመው፥ ከመጀመሪያው ኬብሮን አምስት መቶ ዓመት በኋላ ነው። መምሬየሚለው ስም የእንግሊዝኛውን መጽሐፍ ቅዱስን ጨምሮ በሌሎችም ቋንቋዎች የሚነበበውMamre ተብሎ ሲሆን፥ ስርዎ ቃሉም ሆነ ፍችው የኢትዮጵያ ነው። የዕብራይስጥ ቋንቋም፥ በዚያን ዘመን አልተፈጠረም። የቃሉን ምንጭ እና ፍች ስንመረምረው፥
መምሬ ~ Mamre: manliness, SBD,
ሪ፣ መም ምህር፣ መሪ አስተማሪ ማለት ነው።
መሪ ከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው። ( 14: 13 24)
ሌላው ደግሞየአድባር ዛፍየሚለው እሳቤና ድርጊት፥ በዚያን ዘመንም ሆነ ዛሬ ያለው፥ በኢትዮጵያ ነው።
ሎጥ ከግብፅ ወጥቶ፤ ከአብርሃም ጋር ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱ፤ በኢትዮጵያም የሞዓባውያንን እና የአሞናውያንን ነገዶች መመስረቱ፤ ገሞራና ሰዶማ የሚባሉ ቦታዎች፥ ዛሬም በሰሜን ምሥራቅ ኢትዮጵያ መኖራቸው፤ በቂ ማስረጃ ነው።
አብርሃምም ከዚያ ተነሥቶ ወደ አዜብ ምድር ሄደ፥ ቃዴስ ሱር መካከልም ተቀመጠ፤ በጌራራም በእንግድነት ተቀመጠ።” (ዘፍ 201)
ቃዴስየሚለው ቃል ፍችቅዱስሲሆን፤ቀደሰየሚለውም ግስ የሚገኘውም በኢትዮጵያውያን ቋንቋ ነው።ቅድስናእናጽድቅየሚሉ እሳቤዎችም፥ ከእስራኤል መወለድ፣ መመረጥና መቀደስ በፊት፥ በኢትዮጵያ (ብቻ) የነበሩ ናቸው።
ኢትዮጵያው ንጉሥ፥ አቤሜሊክ፤ አብርሃም ከግብፅ ሲመጣ ተቀብሎ አስተናገደው። ሳራንም እህቴ ናት ስለአለው ለሚስትነት ወሰዳት። ነገር ግን እግዚአብሔር ለአቤሜሌክ በህልም ተገልጦ፤ ሳራ ለአብርሃም ሚስቱ ናትና መልስለት ያለዚያ ትቀሰፋለህ አለው። አቤሜሌክም እኔ እህቴ ናት ስላለኝ በቅንነት አደረግሁት ካለ ብኋላ “...አቤቱ ጻድቁ ህዝብ ደግሞ ታጠፋለህን?” (ዘፍ 204) በማለት የራሱንና የሚያስተዳድረውን የኢትዮጵያን ህዝብ ጻድቅነት መስክሯል። እንግዲህ አብርሃም አምኖ ጻድቅ ሳይባል፤ ገና እስራኤል ሳይወለድ፤ ህዝቡም ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ሳይባል፤ ኢትዮጵያውያን ግን ጻድቅ ነበሩ።
በኦሪት ዘመን፥ ጻድቅ የተባሉ ብዙ ሰዎች አሉ። ጻድቅ ኖህ፣ ኢዮብ፣ አብርሃም፣ ሎጥ፣ ዮሐንስ፣ ዮሴፍ... እነዚህ ሰዎች ሁሉ፥ በግል ምግባራቸው ጻድቅነታቸውን እግዚአብሔር መስክሮላቸዋል። እንደ ህዝብ ደግሞ ጻድቅ ተብሎ የተጠራ፤ ከኢትዮጵያ ህዝብ ውጭ ሌላ የለም።
ሱርከግብፅ በስተደቡብ የሚገኝ የቦታ ስም ሲሆን፥ በአብርሃም ዘመን፥ በኢትዮጵያውያን ነገሥታት ይተዳደር ነበር። ከአምስት መቶ ዓመት በኋላ፥ ሙሴ እስራኤላውያንን ከግብፅ ባርነት ነጻ ሲያወጣ፥ ወደዚህ ስፍራ እንዳመጣቸውና ስሙም እንዳልተቀየረ እናያለን። (ዘጸ 1522)
አብርሃምን በአዜብ (በኢትዮጵያ) በእንግድነት ተቀብለው ያኖሩት እነ አቢሜሌክ፣ መልከጼዲቅ... ኢትዮጵያውያን ነገሥታት ናቸው።
ስለዚህ አብርሃም ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱን ከተረዳን፤ ሥላሴን በቤቱ ተቀብሎ ያስተናገደው እና የግርዛትን የቃል ኪዳን ምልክት ከእግዚአብሔር ጋር ያደረገው፥ በዛሬዋ ኢትዮጵያ መሆኑ ግልጽ ይሆናል። አብርሃምም የቍልፈቱን ሥጋ በተገረዘ ጊዜ የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው ነበረ(ዘፍ 1724) እንዲሁም፥ ስሙ፥ ከአብራምነት ወደ አብርሃምነት የተቀየረው፥ የሚስቱ ስም ሦራም ወደ ሳራነት የተቀየረው በዛሬዋ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው። ይህ ብቻ አይደለም፥ በሰማኒያ ስድስት ዓመቱ እስማኤልን ከግብጻዊቷ የሳራ አገልጋይ፥ ከአጋር የወለደው፤ በኢትዮጵያ እየኖረ ነው። የእግዚአብሔር መልአክም አላት፦ እነሆ አንቺ ፀንሰሻል፥ ወንድ ልጅንም ትወልጃለሽ፤ ስሙንም እስማኤል ብለሽ ትጠሪዋለሽ፥ እግዚአብሔር መቸገርሽን ሰምቶአልና።(ዘፍ 1611) እስምኤል የሚለውን የስሙን ፍችና ስርዎ ቃል ስንመረምር፥ የኢትዮጵያ ቃላት ሁነው እናገኛቸዋለን።
እስማኤል ~ Ishmael: ሰማ ኤል ሰማ ኃያል፣ አምላክ ሰማ፣ ፀሎትን ተቀበለ... ማለት ነው።
ሰማ እና ኤል ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
[ትርጉሙእግዚአብሔር ይሰማልማለት ነው, የመ/ቅ መ/ቃ]
“Ishmael” means whom God hears, SBD,
በመቶ ዓመቱ ይስሐቅን ከሳራ የወለደው በዛሬዋ ኢትዮጵያ ነው። ይህንም፥ ይስሐቅ በሚለው የስሙ ፍች እና ሥርዎ ቃል፥ ኢትዮጵያዊነቱን እናሳያለን።
ይስሐቅ ~ Isaac: ይሳቅ ይስሐቅ፣ መሳቅ፣ ፈገግታ ማሳየት፣ ጥርስን መግለጥ... ማለት ነው። [ትርጉሙይስቃልማለት ነው, የመ/ቅ መ/ቃ]
ሳቀ ከሚለው ግስ የመጣ ስም ነው።
Isaac: “Isaac” means laughter, SBD,
የይስሐቅ እና የእስማኤል፥ የልጅነታቸው ቅርበትና መብት የሚለያየው፤ እስማኤል የተወለደው፥ አብርሃም ከመገረዙ በፊት፤ ይስሐቅ የተወለደው ደግሞ፥ ከተገረዘ በኋላ በመሆኑ ነው። አብርሃምም የቍልፈቱን ሥጋ በተገረዘ ጊዜ የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው ነበረ፤ (ዘፍ 1724)
በተጨማሪም፥ የአብርሃም ሚስት ሳራ፥ በመቶ ሃያ ሰባት ዓመቷ ስትሞት የቀበራት፥ ኬጢያውያን ከሚባሉ የኢትዮጵያ ጎሳዎች በገዛው መሬት ነው።
ሌላው፥ ብዙ ጊዜ ተደባብሶና ተለባብሶ የሚታለፈው ታሪክ፥ አብርሃም፥ ሳራ ከሞተች በኋላ፥ ኬጡራ የተባለች፥ ከኬጢያውያን ጎሳ የሆነች ኢትዮጵያዊት አግብቶ ስድስት ወንድ ልጆችን መውለዱን ነው። አብርሃምም ደግሞ ስምዋ ኬጡራ የተባለች ሚስት አገባ።” (ዘፍ 25: 1) እርስዋም ዘምራንን፥ ዮቅሳንን፥ ሜዳንን፥ ምድያምን፥ የስቦቅን፥ ስዌሕን ወለደችለት። ከኬጡራ ልጆች በተጨማሪ፥ አብርሃም፥ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ቁባቶቹ፥ ስማቸው እና ቁጥራቸው ያልተጠቀሰ ልጆችን ወልዷል። በመጨረሻም፥ አብርሃም አርጅቶ በመቶ ሰባ አምስት ዓመቱ ሲሞት፥ ከኬጢያውያን በገዛው የመቃብር ቦታ፥ ከሚስቱ ጎን የተቀበረው፥ በዛሬዋ የኢትዮጵያ ምድር ነው። ልጆቹ ይስሐቅና እስማኤልም በመምሬ ፊት ለፊት ባለው በኬጢያዊ በሰዓር ልጅ በኤፍሮን እርሻ ላይ ባለ ድርብ ክፍል በሆነው ዋሻ ውስጥ ቀበሩት።” (ዘፍ 25: 9)
ከዚህ ቀጥለን፥ አብርሃም ወደ አዜብ ካደረገው ጉዞ ጋር በተያያዘ፥ የአንዳንድ ቦታዎችን እና ሰዎችን እየጠቀስን፥ ማብራሪያ እና ማስረጃዎችን እናያለን።
 
 
አብርሃም እና የቦታ ስም (ስሞች)
አዜብ (ኢትዮጵያ) አብርሃም፥ ከግብፅ ወጥቶ የኖረበት አገር፥
አብርሃምም ከዚያ ተነሥቶ ወደ አዜብ ምድር ሄደ፥ በቃዴስና በሱር መካከልም ተቀመጠ በጌራራም በእንግድነት ተቀመጠ።” (ዘፍ 131 እና 201)
አዜብ ተብሎ በመጽሐፍ ቅዱስ የተጠቀሰው አገር፥ የዛሬዋ ኢትዮጵያ ናት። የሳባ ንግሥት፥ የሰሎሞንን ጥበብ ሰምታ በእንቆቅልሽ ልትፈትነው፤ ከኢትዮጵያ እንደሄደች ስለሚታወቅ፤ ጌታ ኢየሱስ፥ንግሥተ አዜብሲል ጠርቷታል።ንግሥተ ዓዜብ በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥታ ትፈርድበታለች፤ የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳር መጥታለችና፥ እነሆም፥ ከሰሎሞን የሚበልጥ ከዚህ አለ” (ማቴ 1242 እና ሉቃ 1131) የሳባ አገር፣ የአዜብ ምድር፣ የምድያም አገር፣ ኢትዮጵያ ... ሁሉም የአንድ ግዛትና ርስት መጠሪያዎች ናቸው።
የቃሉ ትርጉም፥ ደቡብ እና/ ወይም ደቡብ ምዕራብ ማለት ሲሆን፥ የቦታ መጠሪያም ሁኖ ያገለግላል። ደቡብነቱም ለግብፅ እና ለእስራኤል ነው። ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ የሚተርከው፤ የአብርሃምን ጉዞ ከግብፅ ተነስቶ ወደ አዜብ መምጣትን ነውና። በእንግሊዝኛ መጽሐፍ ቅዱስ “South” ተብሎ ተመዝግቦና ተተርጉሞ እናገኘዋለን። ይህም ከግብፅና ከእስራኤል በስተደቡብ የሚገኝ አገር መሆኑን ያመለክታል።ከግብፅ ተነስቶ ወደ ደቡብ ተጓዘካልን፥ ወደ ኢትዮጵያ፣ ምሥራቅ አፍሪካ፣ አፍሪካ... እንጅ ወደ ሌላ ወደ የትም ሊውስደን አይችልም።
የአብርሃም ልጅ፤ ይስሐቅ ተወልዶ ያደገው በኢትዮጵያ ስለነበር፥ ሚስቱም የመጣችለት በዚያ ሲኖር ነው፥ይስሐቅም ብኤርለሃይሮኢ በሚሉአት ምንጭ መንገድ መጣ፤ አዜብ ምድር ተቀምጦ ነበርና።” (ዘፍ 2462)
 
 
ቃዴስ፥ አብርሃም ከግብጽ ወጥቶ ያረፈበት፥ የኢትዮጵያ ግዛት፥
የስሙ ፍች፥ ቅዱስ ማለት ነው። ሥርዎ ቃሉ ቀደሰ የሚለው ግስ ነው።
ቤርሳባ፥ የኢትዮጵያው ንጉሥ አቤሜሌክ እና አብርሃም ቃል ኪዳን የፈጸሙበት፥
የስሙ ፍች፥ የሳባ በር፣ የሳባ ቤት፣ የሳባ ልጅ፣ ቤተ ሳባዊ፣ ኢትዮጵያዊ...
 አብርሃም እና ሌሎች ሰዎች በኢትዮጵያ፥
አቢሜሌክ የጻድቅ ሕዝብ፥ ኢትዮጵያዊ ንጉሥ፥
አቢሜሌክ ግን አልቀረባትም ነበር፤ እንዲህም አለ፦ አቤቱ፥ ጻድቁን ሕዝብ ደግሞ ታጠፋለህን?”
አቢሜሌክ፥ በአብርሃም ዘመን፥ በአዜብ ምድር የነበረ ኢትዮጵያ ንጉሥ ነው። የአቢሜሌክ ኢትዮጵያዊነት አንዱ ማሳያ፥ የስሙ ፍች እና ሥርዎ ቃል፥ ሁለት የኢትዮጵያ ቃላት መሆናቸው ነው። እነሱምአብእናመለከየሚሉት ሲሆኑ፥ ፍችውም፥የንጉሥ አባትማለት ነው።
አብርሃም፥ ከግብፅ ወደ አዜብ ሲመጣ በግዛቱ በኢትዮጵያ ተቀብሎ እንዲቀመጥ የፈቀደ ንጉሥ ነው። የአብርሃም ሚስት ሳራ፥ የአብርሃም እህት መስላው ሊያገባት ከውሰዳት በኋላ፥ የአብርሃም ሚስቱ እንደሆነች እግዚአብሔር ሲነግረው፥ ከነክብሯ የመለሰ ንጹህ ሰው ነው።
ንጉሡም፥ ከዛሬዋ ኢትዮጵያ እስከ ፍልስጤም ያስተዳድር ነበር። ቤርሳቤህ ቃል ኪዳንን አደረጉ። አቢሜሌክ የሙሽራው ወዳጅ አኮዘት የሠራዊቱ አለቃ ፊኮልም ተነሥተው ወደ ፍልስጥኤ ምድር ተመለሱ።” (ዘፍ 21: 32) ቤርሳቤህ፥ የኢትዮጵያ ግዛትና የቦታ ስም፥ ፍችውና ሥርዎ ቃሉ የኢትዮጵያ ስለመሆኑ፥ ፍችውምየኢትዮጵያ ልጅ፥ የሳባ በር፥ የሳባ ቤት፣ ቤተ ሳባ... የቃል ኪዳን ምልክትተብሎ መተርጎሙን ያመለክታል።
አቢሜሌክ የሚለው ስም፥ ከእስራኤል መፈጠር በፊትም የነበረ፥ የኢትዮጵያውያን ሰዎች መጠሪያ እንደነበር መገንዘብ ያስፈልጋል። ስለሆንም፥ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱት፥ ከአራት የማያንሱ አቢሜሌኮች፥ ሁሉም በሚባል ደረጃ፥ የኢትዮጵያዊ የትውልድ ሐረግ የነበራቸው ናቸው። ዳዊትም ኬጢያዊው አቢሜሌክንና የጽሩያን ልጅ የኢዮአብን ወንድም አቢሳን፦ ወደ ሳኦል ወደ ሰፈሩ ከእኔ ጋር የሚወርድ ማን ነው? ብሎ ጠየቃቸው፤ አቢሳም፦ እኔ ከአንተ ጋር እወርዳለሁ አለ” (1ሳሙ 26: 6) (አቢሳ፥ ማለት አበሻ ማለት ነው። እና ተለዋዋጭ ስለሆኑ እንጅ) የንጉሥ ዳዊት፥ ከመንገሡ በፊትም ሆነ በኋላ፥ ታማኝ ወታደሮቹ እንደ ኦሪዮን የመሳሰሉ፥ ኬጤያውያን (ኢትዮጵያውያን) እንጅ፥ እስራኤላውያን አልነበሩም። አቤሜሌክን ኬጢያዊው ያለው፥ ኢትዮጵያዊ እንጅ፥ እስራኤላዊ አለመሆኑን በግልጽ የሚያሳይ ነው። [አቢሜሌክ እና አቤሜሌክ አንድ ዓይነት ስሞች እና ትርጉማቸውም አንድ ነው። ልዩነታቸው የድምጽ ቅላጼ/ accent ብቻ ነው።)
በአብርሃም ዘመን ከነበረው፥ ከመጀመሪያው አቤሜሌክ፤ እስከ ነብዩ ኤርምያስ ዘመን የተጠቀሰው፥ አቤሜሌክ፥ የአንድ ሺህ አምስት መቶ ዘመን ልዩነት ቢኖርም፥ ሁለቱም አቤሜሌኮች የታወቁ ኢትዮጵያውያን ነበሩ፥ በንጉሡም ቤት የነበረው ጃንደረባ ኢትዮጵያዊው አቤሜሌክ ኤርምያስን በጕድጓዱ ውስጥ እንዳኖሩት ሰማ። ንጉሡም በብንያም በር ተቀምጦ ነበር።” (ኤር 38: 7)
ኑኃሚን እና ባሏ አቤሜሌክ፤ በርሃብ ምክንያት፥ ከቤተልሔም ይሁዳ፣ የተሰደዱት ወደ ኢትዮጵያ ነበር።  ይህም የሆነው፥ አቤሜሌክ የኢትዮጵያ ሰው ስለሆነ ነው፥ የሰውዮውም ስም አቤሜሌክ የሚስቱም ስም ኑኃሚን፥ የሁለቱም ልጆች ስም መሐሎንና ኬሌዎን ነበረ፤ የቤተ ልሔም ይሁዳም የኤፍራታ ሰዎች ነበሩ። ወደ ሞዓብም ምድር መጡ በዚያም ተቀመጡ።” (ሩት 1: 2) ሞዓብ የሎጥ ልጅ ሁኖ፤ በኢትዮጵያ፥ የሞዓባውያን ነገድን የመሰረተ ነው።
ኢትዮጵያዊቱን ሩት ያገባው፥ የአቤሜሌክ ወገን ቦዔዝ፥ የትውልድ ሐረጉ ኢትዮያዊ እንጅ እስራኤላዊ አይደለም፥  ለኑኃሚንም ባል የሚዘመደው አቤሜሌክ ወገን የሆነ ኃያል ሰው ስሙ ቦዔዝ የተባለ ሰው ነበረ።” (ሩት 2:1) [ከቤተልሔም ወደ ሞአብ ምድር (ኢትዮጵያ) መምጣታቸው፤ መጀመሪያውኑ ትውልዳቸው ከኢትዮጵያ መሆናቸውን ያሳያል።]
እስራኤላውያን ከግብፅ ወጥተው በኢትዮጵያ ምድር አርባ ዓመት ከኖሩ በኋላ፥ የከነዓንን ምድር ለመውረስ ሲገቡ፥ ብዙ ኢትዮጵያውያን አብረዋቸው እንደገቡ ብዙ ማስረጃዎች አሉ። በአንጻሩም፥ ብዙ የእስራኤል ወገኖችም ቤት ሰርተው፥ እርሻ መስርተው በኢትዮጵያ እንደቀሩም የታወቀ ነው።
እሴይ የንጉሥ ዳዊት አባት ሲሆን፤ የትውልድ ሐረጉ ከኢትዮጵያውያን ከሩት እና ከናዖሚን ባል፤ ከአቢሜሌክ ወገን፥ ከቦኤዝ ነው።
ሰልሞንም ራኬብ ቦኤዝ ወለደ፤ ቦኤዝ ሩት ኢዮቤድ ወለደ፤ ኢዮቤድ እሴይ ወለደ፤(ማቴ 15) እሴይ ደግሞ የንጉሥ ዳዊት አባት ነው።
ይህም ብቻ አይደለም፥ ንጉሥ ሰሎሞን፥ ከቤርሳባ በመወለዱ፥ በግማሽ ኢትዮጵያዊ መሆኑን ያሳያል። እንግዲህ፥ ንጉሥ ዳዊትን በከፊል ኢትዮጵያዊ መሆኑና ልጁ ሰሎሞን በግማሽ ኢትዮጵያዊ መሆኑ፤ የሰሎሞን የትውልድ ሐርግ እስራኤላዊ ከማለት፥ ኢትዮጵያዊ ነበር፤ የሚለው የበለጠ ያሳምናል።
መልከጼዴቅ (ኢትዮጵያዊ ንጉሥም፥ ካህንም) አብርሃምን ያቆረበ፥ አስራትንም ከአብርሃም የተቀበለ፥
መልከጼዴቅ፥ በአብርሃም ዘመን፤ ማለትም የዛሬ አራት ሺሕ ዓመት ገደማ፤ በአዜብ ምድር(በኢትዮጵያ) የነበረ፥ ኢትዮጵያዊ ካህን እና ንጉሥ ነው። አምልኮተ እግዚአብሔር፥ በመልከ ጼዴቅ ዘመን በኢትዮጵያ ተጀመረ፥ ለማለት ባያስችልም፤ እስራኤላውያን የመጀመሪያ ካህናቸው፥ አሮን፥ ከመሾሙ አምስት መቶ ዓመት በፊት የነበረ ካህን፤ የመጀመሪያ ንጉሣቸው ሳዖል ከመሾሙ፥ አንድ ሺሕ ዓመት አስቀድሞ፥ የነበረ ንጉሥ ነው። ከመልከጼዴቅና ከአብርሃም ሁለትና ሦስት ሺሕ ዓመት በፊት፤ በእነ ሄኖክና በእነ ኖኅ ዘመንም፥ እግዚአብሔር በኢትዮጵያውያኖች ዘንድ፥ ይመለክ እንደነበር፥ የተረጋገጠ ነው።
የመልከጼዴቅ ኢትዮጵያዊነት፥ የሚነግረን ሌላው ቁም ነገር፥ አብርሃም፥ ከመልከ ጼዴቅ ቁርባን (ወይን እና ህብስት)  መቀበሉ፥ አብርሃም፥ እግዚአብሔርን ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳወቀ አስረጅነቱ ነው።
እንዲሁም፥ አብርሃም፥ ለመልከጼዴቅ አሥራትን መስጠቱ፥ እስራኤላውያን ወደ ቃል ኪዳን አገራቸው ሲገቡ፥ ለኢትዮጵያ ነገሥታት፥ ግብር መሥጠት እንዳለባቸው ያስገነዝበናል።
ከመልከ ጼዴቅ ዘመን አራት መቶ ዓመት በኋላ የተሰጠው የአሮን ክህነት፥ ከኢትዮጵያውያን የክህነት ማእረግ እኩል ያለመሆኑ፥ ሌዋውያን ከእስራኤላውያን ከሚሰበስቡት አስራት፥ ለመልከጼዴቃውያን ክህነት፥ ለኢትዮጵያውያን መንበር፥ መገበር እንዳለባቸውና መታዘዝ እንደሚገባቸው፥ ያስገነዝበናል።ትንሹም በታላቁ እንዲባረክ... ” (ዕብ 77) ባለው ይታወቃል።
የመልከ ጼዴቅን ኢትዮጵያዊነት ለመመርመር፣ ለማብራራት እና ለማስረዳት፥ ሦስት ዋና ዋና ትምህርቶችን፥ ማቅረብ ያስፈልጋል።
1.1.1.            የቃላት ማስረጃዎች
1.1.2.          የታሪክ ማስረጃዎች
1.1.3.          የአምልኮ ማስረጃዎች
1.1 የቃላት ማስረጃ፥
የስሙ ፍች እና ስርዎ ቃል፥መልከ ጼዴቅየሚለው ስም፥ መልከ ጼዴቅ ሁኖ፥ ገብረ ጼዴቅ እና ወልደ ጼዴቅ ከሚሉ ስሞች ጋር ተዛማጅነት አለው።
የስሙ መሰረት (ስርዎ ቃል) ሁለት ናቸው፥
1.     መልክ፣ መለከ/ ምሉክ እና መላክ (መልአክ፣ መላእክ...)
·       መላከ ገነት፣ መላከ ሰላም፣ መላከ ኃያል...
·       መልከ ማርያም (መልካ፣ መልክ፣ መልከዓ) መልከ ኢየሱስ (መልካ፣ መልክ፣ መልከዓ)... እንደማለት ...
·       መለክ፣ የሚመለክ፣ የሚገዛ ንጉሥ ማለት ነው
2.     ጼዴቅ፥እውነት ማለት ነውተብሎ ይተረጎማል። ይህ ግን (አውደ ንባባዊ/ contextual እና ዘመናዊ/ contemporary ፍች ነው) እንጅ ጥንታዊና መሰረታዊ/ etymological ፍችው ግን አይደለም። ጸደቀ ከሚለው ግስ ሁኖ፥ ህያው ሆነ፣ ህይወት ኖረው...የሚል ፍች ይሰጠናል።
·       መልከ ጸዲቅ፣ መላከ ጼዴቅ፣ ምሉከ ጽድቅ...
·       ጸዲቅየሚለውን ሌሎችሳዲክወይምዛዲክይሉታል።ጸደቀየሚለው ግስ እናጸ፣ ..የሚሉ ድምጾች፥ በትክክል የሚባሉት በኢትዮጵያውያን ልሳን ነው። (ጽዮን፣ ጽድቅ፣ ጸበል... የሚሉትም)
ጻዴቅየሚለው ስም የመጣው ሳዴክወይምዛዴክከሚሉ ሰዎች ቢሆን ኑሮ፤ ኢትዮጵያውያን ሳዴክ እና ዛዴክ እያሉ መጥራት ባልተሳናቸው ነበር። [ጼዴቅ የሚለው ስም እና ጽድቅና ኩነኔ የሚባሉ እሳቤዎች፥ ከአብርሃም መጠራት በፊት፤ በኢትዮጵያ (ብቻ) የነበሩ ናቸው።]
 
ወይን፥
ወይን፥ የሚለው ስም አስረጅነት፥ በመልከ ጼዴቅ ዘመን የነበረ ቃል/ ስም...
መልከ ጼዴቅ፥ ለአብርሃም ህብስት እና ወይንን ያቀበለው፥ ኢትዮጵያ ውስጥ መሆኑን ያሳያል...
የኢትዮጵያ ቃል መሆኑ፥ወይን ጠጅወይን አረግወይን አበባወይን እሸት’... ሌሎች ግን፥ ወይን/ Wine የሚለውን ስም ከሌላ ስም ጋር አጣምረው፥ አይጠቀሙም።
በዓለም ላይ፥ በብዙ አገር ቋንቋዎችይንተብሎ ሲጠራ... “ግእዝ በመሆኑ፥ ኢትዮጵያ ውስጥይንሲባል በውጭ ቋንቋዎች ደግሞይሆናል። ቃሉ ወይም ስሙ የመጣው ይንቢሆን ኑሮ፥ እኛም  ይንብለን መጥራት ባልተሳነን ነበር። ይህም በሌላ ምሳሌ ለማስገንዘብ፥ኮፊእናጎድየሚሉትን ስሞችን እንውሰድ።ኮፊየተገኘው ከፋ አገር ስለሆነ፤ ስሙም ከዚያ ወጥቷል። ከጎንደር የመጣን ጎንደሬ፤ ከሐረር የመጣን ሐረሬ፥ እንደምንል፤ ከከፋ የመጣንከፌሲሆን፥ግእዝ በመሆኑማለት ሲሳናቸውወይምብለው፥ ~ Café” ወይም ~ Coffee” እንደሚሉት ማለት ነው። በተመሳሳይም፥ገድየሚለውን፥ግዕዝ በመሆኑ፥ “GAD/ ጋድ ወይም GOD/ ጎድ፣ ጋድእንደሚሉት ማለት ነው። ፊደላቸው፥ በትክክል ሊጽፈው እንደማይችል የተረዱና፥ እነሱም በትክክል መጥራት እነደማይችሉ ያመኑ፥ G*D ብለው ይጽፉታል።
ስለዚህም፥ ከዘመነ ኖኅ ጀምሮ እንኳን የወይን ዘለላ፥ወይንየሚል ስም ተሰጥቶት፥ ስሙም በሌላ ቋንቋዎች ሳይቀየር እስከ ዛሬ፥ ከአምስት ሺሕ ዓመት በላይ ቆይቷል።
 
1.2 . የታሪካ ማስረጃ፥
አብርሃም፥ ከግብፅ ወጥቶ ወደ አዜብ (ኢትዮጵያ) መምጣቱ፤ አብራምም ከግብፅ ወጣ፤ እርሱና ሚስቱ ለእርሱ የነበረውም ሁሉ ሎጥም ከእርሱ ጋር ወደ አዜብ ወጡ” (ዘፍ 131)And Abram went up out of Egypt, he, and his wife, and all that he had, and Lot with him, into the south.” (ዘፍ 131)
አብርሃም፥ ለእግዚአብሔር መስዋእትን ያቀረበው በኢትዮጵያ ነው፥አብራምም ድንኳኑን ነቀለ መጥቶም በኬብሮን ባለው መምሬ የአድባር ዛፍ ተቀመጠ፤ በዚያም ለእግዚአብሔር መሠውያን ሠራ።” (ዘፍ 1318) [መምሬ የሚለው በእንግሊዝኛው መጽሐፍ ቅዱስMamreተብሎ መጻፉን ልናስተውል ይገባል።]
አብርሃምም ከዚያ ተነሥቶ ወደ አዜብ ምድር ሄደ፥ ቃዴስ ሱር መካከልም ተቀመጠ፤ በጌራራም በእንግድነት ተቀመጠ።” (ዘፍ 201)
ቃዴስማለት ቅዱስ ማለት ነው።
አዜብ፡ ደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ የሳባ አገር፣ south… ኢትዮጵያ፣ የምድር ዳር፣ ምሥራቅ አፍሪካ፣ አፍሪካ..
ንግሥተ አዜብ በፍርድ ከዚህ ትውልድ ሰዎች ጋር ተነሥታ ትፈርድባቸዋለች፤ የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳር መጥታለችና፥ እነሆም፥ ከሰሎሞን የሚበልጥ ከዚህ አለ።” (ማቴ 1242 እና ሉቃ 1131)
የመልከ ጼዴቅ የትውልድ ሐረግ አለመገለጹ፤ ኢትዮጵያዊ እንጅ እስራኤላዊ አለመሆኑን ያረጋግጣል።ትውልዱ ከነሱ የማይቆጠረው...” ይለዋል፥ ቅዱስ ጳውሎስ፥ (ዕብ 76)]
በመጽሐፍ ቅዱስ፥ እስራኤላዊ ባላመሆናቸው፥ የትውልድ ሐረጋቸው ካልተጠቀሱ ሰዎች ውስጥ፡ በአዜብ (ኢትዮጵያ) የጌራራ ንጉሥ አቤሜሌክ፣ ኤርሚያስን ከጉድጓድ ያወጣው ኢትዮጵያዊው አቤሜሌክ፣ የናዖሚን ባል አቢሜሌክ፣ ካህኑ ዮቶር፣ የአብርሃም ሚስት ኬጡራና ስድስቱ ልጆቻቸው፣ ሞባዊቷ ሩት፣ ንግሥተ ሳባ/ ንግሥተ አዜብ፣ ኦሪዮን እና ቤርሳባ... እመቤታችን ድንግል ማርያም...
እንደ ሄኖክ ሁሉ መልከጼዴቅም ኢትዮጵያዊ እንጅ እስራኤላዊ ባለመሆኑ የህይወት ታሪኩንም ሆነ የትውልድ ሐረጉን፥ አብዝተው መጻፍ አላስፈለጋቸውም።
ዓለሙ ሁሉ፥ የኢትዮጵያ ዘር አለበት፥ ማለት ይቻላል፤ ሆኖም ግን፥ ኢትዮጵያውያን የሌላው ዓለም ዘር አላቸው፥ ማለት ግን አይደለም።
1.3 . የአምልኮ ማስረጃ፥
ክህነት፥
ክህነትም ሆነ አምልኮ ከእስራኤላውያን በፊት፥ በኢትዮጵያ (ብቻ) የነበረ ስልጣን ስለመሆኑ...
በአብርሃም ዘመን፥ ከአሮን ክህነት አምስት መቶ ዓመት በፊት የነበረ፥ ኢትዮጵያዊ ካህን መልከ ጼዴቅ... “...እርሱም የልዑል እግዚአብሔር ካህን ነበረ” (ዘፍ 1418)
ቁርባን፥
የሳሌም ንጉሥ መልከ ጼዴቅ እንጀራንና የወይን ጠጅ አወጣ፤ እርሱም የልዑል እግዚአብሔር ካህን ነበረ።” (ዘፍ 1418) መልኬጼዴቅ፥ አብርሃምን ማቁረቡ (ምሥጢረ ቁርባን) ከክርስቶስ መወለድ፣ መሰቀልና ከሙታን ተለይቶ ከመነሳቱ ሁለት ሺሕ ዓመት ቀድሞ፥ በኢትዮጵያ መኖሩን ያስረዳል... ለአዲስ ኪዳን፥ ሥጋዎ ደሙ፥ የመልከ ጼዴቅ ህብስት እና ወይን ለአብርሃም ማቀበል፤ ምንጭ እና መሰረት ኢትዮጵያ መሆኗን ያመለክታል።
ከዚህም በተጨማሪ፤ የቃሉን ፍች ስንመረምር፥ ምንጩ ኢትዮጵያ ሁኖ አናገኛለን፥
ቍርባን ~ Corban: ቁርን፣ ቆረበ፣ ቀረበ፣ ከአምላክ ጋር ተዋሐደ፣ ህብረት ፈጠረ፣ ወደ እግዚአብሔር ተጠጋ... ማለት ነው።
ቀረበ ከሚለው ግስ የመጣ ቃል ነው።
Corban: an offering to God of any sort, bloody or bloodless, but particularly in fulfillment of a vow. The law laid down rules for vows, SBD,
በማርቆስ ወንጌልቁርባንየተባለው በማቴዎስ መባ ተተርጉል፥ እናንተ ግን ትላላችሁ። ሰው አባቱን ወይም እናቱን። ከእኔ የምትጠቀምበት ነገር ሁሉ ቍርባን ማለት መባ ነው ቢል፥ (ማቴ 15: 5 11  7: 11) ቁርባን የእስራኤላውያን ቃል ቢሆን ኑሮ፥ መባ ተብሎ መተርጎም አያስፈልግም ነበር። 
ግርዘት፥
በእኔና በአንተ መካከል፥ ከአንተም በኋላ በዘርህ መካከል ምትጠብቁት ቃል ኪዳኔ ይህ ነው፤ ከእናንተ ወንድ ሁሉ ይገረዝ” (ዘፍ 1710)
የአብርሃም የቃል ኪዳን ምልክት የሆነው፥ ግርዛት፥ የተፈጸመው በኢትዮጵያ መሆኑ...
የአክሱምን ሐውልት ጨምሮ፤ በኢትዮጵያውያን ወንዶች አካል ላይ፥ የቃል ኪዳኑ ምልክት እስከ አሁን አለ።
አብርሃም፥ ሥላሴን በድንኳኑ ተቀብሉ ያስተናገደው፥ በኢትዮጵያ መሆኑ...
 ሎጥ፥ የሞባውያን እና አሞናውያን ነገዶች በኢትዮጵያ፥
ከአጎቱ፥ ከአብርሃም ጋር ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት፥ የሞባውያንን እና አሞናውያንን ጎሳዎች በኢትዮጵያ መስርቶ ያለፈ ጻድቅ አባት ነው።
የታራም ትውልድ እነሆ ይህ ነው። ታራ አብራምንና ናኮርን ሐራንንም ወለደ፤ ሐራንም ሎጥ ወለደ።” (ዘፍ 1127)
የአብርሃም ወንድም፥ ሐራን ልጅ ሲሆን፥ የተወለደው በከለዳውያን ዑር ነው። በጉዞው ሁሉ ከአብርሃም አልተለየም። ከአብርሃም ጋር ከግብፅ ከወጡ በኋላ፤ በኢትዮጵያ ሲኖሩ፤ አለመስማማት ስለተፈጠረ፤ አብርሃም በምዕራብ ኢትዮጵያ ሲቆይ፤ ሎጥ ወደ ምሥራቅ፥ ወደ ዛሬው እሳተ ገሞራ አገር፥ ሂዶ መኖር ጀመረ...ሎጥም በዮርዳኖስ ዙሪያ ያለውን አገር ሁሉ መረጠ፤ ሎጥም ወደ ምሥራቅ ተጓዘ፤ አንዱም ከሌላው እርስ በርሳቸው ተለያዩ።(ዘፍ 1311)ሰዶም ይኖር የነበረውን የአብራምን የወንድም ልጅ ሎጥን ደግሞ ከብቱንም ወስደው ሄዱ።” (ዘፍ1412)  ሰዶም፥ ሰዶማ ሲሆን ዛሬም በኢትዮጵያ ሰሜናዊ ምሥራቅ አካባቢ የሚገኝ የቦታ ስም ነው። ገሞራም፥ እሳት የወረደበት ቦታ ሲሆን፤ ዛሬም የገሞራ እሳት (እሳተ ገሞራ) በሰሜን ምሥራቅ ኢትዮጵያ የሚገኝ የቦታ ስም ነው። [ዮርዳኖስ የተባለው ወንዝ፥ ዛሬ ተከዜ የሚባለው ሲሆን፤ በእስራኤል ያለው ዮርዳኖስ ወንዝ የተሰየመው፤ መጀመሪያ ከተጠቀሰው ዮርዳኖስ አምስት መቶ ዓመት በኋላ ነው።]
ከእስራኤል መመረጥ በፊት፤ በአብርሃም ዘመን፤ ጽድቅ እና ኩነኔ የሚባሉ እሳቤዎች የነበሩት፥ በኢትዮጵያ ብቻ ነበር።ጻድቅ ሎጥ በመካከላቸው ሲኖር እያየና እየሰማ ዕለት ዕለት በዓመፀኛ ሥራቸው ጻድቅ ነፍሱን አስጨንቆ ነበርና በዓመፀኞች ሴሰኛ ኑሮ የተገፋውን ያን ጻድቅ ካዳነ፥” (2 ጴጥ 27 እና8) በዚህም ሎጥ፥ ይኖር የነበረው በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ እንደነበር እንገነዘባለን።
በዚያም መልአክት ጎበኙት፤ መልአክቱም ከተማውን ሲያጠፋ፤ ሸሽቶ ከሁለት ልጆቹ ጋር በዞዓር ተቀመጠ። ሚስቱ የጨው አምድ ሆነች። አሞንን እና ሞአብን ወለደ። እነሱም የሞአብአውያን እና የአሞንውያን ነገዶች ሁነው በኢትዮጵያ ኖሩ። የንጉሥ ዳዊት ቅድመ አያት የሆነችው ሩት የሞአባውያን ነገድ የሆነች፥ ኢትዮጵያዊት መሆንዋን ልብ ልንል ይገባል። አቤሜሊክና ናኦሚንም እንደዚሁ። ሌላው የኢትዮጵያዊነቷ ማስረጃ፤ የስሟ ፍች እና ሥርዎ ቃል ነው፥
ሩት ~ Ruth: ርትዑ፣ ት፣ ርትኢት፣ ርእቱ፣ ሒሩት... ቅን እውነተኛ፣ አሸናፊ... ማለት ነው።
ርቱዕከሚለው ቃል የተገኘ ስም ነው።
ኑኃሚን ት፥ በጌታ የትውልድ ሐረግ የተጠቀሰች፥ እነርሱም ሞዓባውያን ሴቶች ሚስት አገቡ የአንዲቱ ስም ዖርፋ የሁለተኛይቱም ስም ሩት ነበረ። ...” (ሩት 1: 4) (ማቴ 1: 5)
 እስማኤል፥ የእስማኤላውያን ነገድ በኢትዮጵያ፥
እስማኤል የተወለደው፣ ያደገው፣ የኖረው፣ የእስማኤላውያንን ነገድ የመሰረተው፣ የሞተው እና የተቀበረው በዛሬዋ ኢትዮጵያ ነው።
የስሙን ፍችና ሥርዎ ቃል ስንመረምር፥ ኢትዮጵያ ሁኖ እናገኘዋለን። እስማኤል ~ Ishmael: ሰማ ኤል ሰማ ኃያል፣ አምላክ ሰማ፣ ፀሎትን ተቀበለ... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም/ ስሞች- ይስማኤል ሳሙኤል...]
ሰማ እና ኤል ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። [ትርጉሙእግዚአብሔር ይሰማልማለት ነው, የመ/ቅ መ/ቃ]
የእግዚአብሔር መልአክም አላት፦ እነሆ አንቺ ፀንሰሻል፥ ወንድ ልጅንም ትወልጃለሽ፤ ስሙንም እስማኤል ብለሽ ትጠሪዋለሽ፥ እግዚአብሔር መቸገርሽን ሰምቶአልና።(ዘፍ 1611)
እናቱ አጋር ትባላለች። አገሯ ግብፅ ነው። የሳራ አገልጋይ ሁና ከግብፅ ወደ ኢትዮጵያ መጣች። ሳራ መውለድ እንደማትችል ስትገነዘብ፥ ከአጋር እንዲወልድ ለአብርሃም መከረችው።
እስማኤል የተገረዘው በአሥራ ሦስት ዓመቱ ነው፥ እስማኤል የቍልፈቱን ሥጋ በተገረዘ ጊዜ የአሥራ ሦስት ዓመት ልጅ ነበረ።” (ዘፍ 1725) ግርዛት በኦሪት ዘመን፥ በኢትዮጵያ ብቻ የነበረ ሥርዓት በመሆኑ፥ እስማኤል የተወለደውና ያተገረዘው ኢትዮጵያ ውስጥ መሆኑን ያስረዳል።
እግዚአብሔር ለአብርሃም፥ ቃል ኪዳኑን በልጁ በይስሐቅ በኩል እንደሚጠብቅ ቢያስታውቀውም፥ ልጁን እስማኤልምን ታላቅ ህዝብ እንደሚያደርገው ቃል ገብቶለታል፥ስለ እስማኤል ሰምቼሃለሁ፤ እነሆ ባርኬዋለሁ፥ ፍሬያምም አደርገዋለሁ፤ እጅግም አበዛዋለሁ፤ አሥራ ሁለት አለቆችንም ይወልዳል፥ ታላቅ ሕዝብም እንዲሆን አደርገዋለሁ።” (ዘፍ1720)
እስማኤልና እስማኤላውያን የሚታወሱበት ሌላው ታሪክ፤ ከወንድሞቹ፥ ከምድያማውያና ጋር ሁነው፥ ዮሴፍን ለግብፅ ነጋዴዎች በሃያ ብር መሸጣቸው ነው፤የምድያም ነጋዶችም አለፉ፤ እነርሱም ዮሴፍን አንሥተው ከጕድጓድ አወጡት፤ እስማኤላውያን ዮሴፍን በሀያ ብር ሸጡት፤ እነርሱም ዮሴፍን ወደ ግብፅ ወሰዱት።” (ዘፍ 3728) ይህም ነገር የተደረገው በዛሬዋ የኢትዮጵያ ምድር ነው። ምድያማውያን ኢትዮጵያውያን እንደሆኑ ስለሚታወቅ፥ የምድያም ወንድም እስማኤል ኢትዮጵያዊ መሆኑ አያጠያይቅም።
ምድያማውያን እና እስማኤላውያን የአንድ አገር ሰዎች መሆናቸውን የምንረዳው፤ ዘፍጥረት ምዕራፍ 37 ቁጥር 36 እነዚያ የምድያም ሰዎች ግን ዮሴፍን በግብፅ ለፈርዖን ጃንደረባ ለዘበኞቹ አለቃ ለጲጥፋራ ሸጡትብሎ፤ ዘፍጥረት ምዕራፍ 30 ቁጥር 1 ላይ፥የፈሮዖን ጃንደረባ የዘበኞቹም አለቃ የሚሆን የግብፅ ሰው ጲጥፋራ ወደ ግብፅ ካወረዱት እስማኤላውያን እጅ ገዛው
እስማኤል የኖረበት የዕድሜው ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው፤ ነፍሱን ሰጠ ሞተም ወደ ወገኖቹም ተከማቸ።” (ዘፍ 2571)
እንግዲህ፥ እስማኤል የተወለደው፣ ያደገው፣ የእስማኤላውያንን አሥራ ሁለት ነገዶች (ምናልባትም እስልምናን) የመሰራተውና ሙቶ የተቀበረው በዛሬዋ ኢትዮጵያ ነው።
 ይስሐቅ፥ ከኢትዮጵያ ያልወጣው የህይወት ታርክ፥
ይስሐቅ የተወለደው፣ ያደገው፣ ያገባው፣ የወለደው፣ የሞተውና የተቀበረው በዛሬዋ ኢትዮጵያ ነው።
ለዚህም አንዱ ማስረጅ፥ የስሙም አወጣጥ እና ፍች፥ ከኢትዮጵያ ቋንቋ ጋር የተያያዘሳቅየሚል ግስ እና ፍች ያለው፥ ሁኖ እናገኘዋለን።
ይስሐቅ ~ Isaac: ይሳቅ፣ ይስሐቅ፣ መሳቅ፣ ፈገግታ ማሳየት፣ ጥርስን መግለጥ... ማለት ነው።
ሳቀከሚለው ግስ የመጣ ስም ነው። [ትርጉሙ ይስቃልማለት ነው /  የመ/ቅ መ/ቃ]
የአብርሃም እና ሣራ ልጅ አብርሃምም የተወለደለትን ሣራ የወለደችለትን የልጁን ስም ይስሐቅ ብሎ ጠራው።” (ዘፍ 211-3) ሳራ በእርጅና ዘመኗ ስለወለደችው እንዲህ አለች፥ ሣራም፦ እግዚአብሔር ሳቅ አድርጎልኛል ይህንንም የሚሰማ ሁሉ በእኔ ምክንያት ይስቃል አለች። (ዘፍ 216)
ከአባቱ ከአብርሃም እና ከልጁ ከያዕቆብ (እስራኤል) በእጅጉ ያነሰ ወይም በበቂ ያልተጻፈበት ምክንያት፤ የይስሐቅ ታሪክ የሚያያዘው ከእስራኤል ይልቅ ከኢትዮጵያ ታሪክ ጋር ስለሆነ ነው።
                  የይስሐቅ ሚስት ወደ ኢትዮጵያ የመጣችው ከካራን ነው። ይስሐቅም ብኤርለሃይሮኢ በሚሉአት ምንጭ መንገድ መጣ አዜብ ምድር ተቀምጦ ነበርና። (ዘፍ 24: 62)
                  ርብቃ፥ ሚስቱ የሞተችውና የተቀበረችው በዛሬዋ ኢትዮጵያ ነው። አብርሃምና ሚስቱ ሣራ ከዚያ ተቀበሩ፤ ይስሐቅና ሚስቱ ርብቃ ከዚያ ተቀበሩ ከዚያም እኔ ልያን ቀበርኋት፤(ዘፍ 4931)
ሙቶ የተቀበረውም በኢትዮጵያ መሆኑ፥ ምክንያቱም ወደሌላ አገር መሰደዱን የሚጠቁም ምንም ዓይነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥቅስ አይገኝም።
 ያዕቆብ፥ የእስራኤላውያንን ኢትዮጵያዊነት ማስረጃ፥
የይስሐቅ ልጅ ሲሆን፥ የተወለደው በዛሬዋ ኢትዮጵያ ነው። እናቱም ርብቃ ትባላለች። በኢትዮጵያ ለመወለዱ አንዱ ፍንጭ የስሙ ፍች ነው።
ያዕቆብ ~ Jacob ያቆብ፣ ያቅብ ያስቀር፣ ይጠብቅ፣ ያግድ፣ ይከልክል... ማለት ነው። [ተዛማጅ ስም/ ስሞች- ያቆብ ያዕቆባ...]
አቀበ ከሚለው ግስ የተገኘ ስም ነው።
ይስ ልጅ፥ከዚያም በኋላ ወንድሙ ወጣ፥ በእጁም የዔሳውን ተረከዝ ይዞ ነበር ስሙም ያዕቆብ ተባለ።” (ዘፍ 2526)
ሁለተኛ ስሙ እስራኤል ነው፥ አለውም፦ ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ እስራኤል ይባል እንጂ ያዕቆብ አይባል ከእግዚአብሔር ከሰውም ጋር ታግለህ አሸንፈሃልና” (ዘፍ 3228) እስራኤል የሚለው ስም የተሰጠውም ኢትዮጵያ ውስጥ ሲሆን፥ ፍችውም፥ ሥራ ኤል፥ የእግዚአብሔር ሥራ፥ ማለት ነው።
የወንድሙን ብኩርና አጭበርብሮ ስለገዛ፥ ከወንድሙ ከኤሳው ሸሽቶ ወደ ካራን ኮበለለ።
ሊያ እና እህቷን ራሄልን አግብቶ፥ ከአገልጋዮቻቸው ጭምር በጠቅላላው አሥራ ሁለት ወንዶችና እና አንድ ሴት ልጅን ወለደ።
ከአሥራ አራት ዓመት የስደት ኑሮ በኋላ፥ ከሚስቶቹና ከልጆቹ ጋር ወደ አገሩ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰና መኖር ጀመረ።
በርሃብ ምክንያት ከአሥራ ሁለት ልጆቹ ጋር ወደ ግብፅ ወረደ። በዚያም ሞተ።
ያዕቆብ፥ በመቶ አርባ ሰባት ዓመቱ፥ በግብፅ ሲሞትም፥ አምጥተው የቀበሩት በተወለደበት፥ በኢትዮጵያ እና በአባቶቹ መቃብር ነው። ያዕቆብ ልጆቹን እንዲህ ብሎ እንዳዘዛቸው፥እንዲህ ብሎም አዘዛቸው፦ እኔ ወደ ወገኖቼ እሰበሰባለሁ፤ ኬጢያ በኤፍሮን እርሻ ላይ ባለችው ዋሻ ከአባቶቼ ጋር ቅበሩኝ፤” (ዘፍ 499) ኬጢያውያን የኢትዮጵያ ጎሳዎች መሆናቸው የተረጋገተጠ እውነት ነው።
ዮሴፍና ወንድሞቹ አባቱንም ሊቀብሩ ከእርሱ ጋር የወጡት ሰዎች ሁሉ አባቱን ከቀበረ በኋላ ወደ ግብፅ ተመለሱ” (ዘፍ 5014) ቀብረው ወደ ግብፅ የተመለሱት፥ ከኢትዮጵያ እንጅ ከሌላ ከየትም አይደለም።
 ኤሳው፥ ከኢትዮጵያ የማይወጣው፥ የኤዶማውያን ነገድ፥
ኤሳው የተወለደው፥ በዛሬዋ የኢትዮጵያ ምድር ወይም በአዜብ ምድር ነው። የይስሐቅ ልጅ ሁኖ የያዕቆብ መንትያ ነው። እናቱ ርብቃ ትባላለች። ሌላው ስሙ ኤዶም ነው ኤዶም፥ የሚለው ስም ፍችም፥ ደም ወይም ቀይ ማለት ነው።  
የይስሐቅ የበኩር ልጅ ሲሆን፥ ብኩርናውን በፈቃዱ ለወንድሙ፥ ለያቆብ በምስር ወጥ ሸጠ። ኤዶም የሚለው ስም የተሰጠበትም ምክንያት፥ ከቀይ ወጡ ታሪክ ጋር በማያያዝ ነው፥ዔሳውም ያዕቆብን፦ ከዚህ ከቀዩ ወጥ አብላኝ፥ እኔ እጅግ ደክሜአለሁና አለው፤ ስለዚህ ስሙ ኤዶም ተባለ።” (ዘፍ 25 30)
ከትውልድ ቀየው ብዙም ሳይርቅ በዛሬዋ ኢትዮጵያ፥ የሰሜን ምሥራቅ ክፍል፥ ህይወቱን ገፍቷል። የኤዶማውያን ነገድ መስራችና አባት ነው።
ኤዶማውያን፥ በሰሜን ምሥራቅ አፍሪካ (ኢትዮጵያ) ስለኖሩ፥ ቀደም ብሎ ጨው ባሕር እና አረባ ባሕር ይባል የነበረው፥ ቀይ ባሕር ተባለ።
ሴይርየተባለው ተራራ እና መሬትም በኢትዮጵያ ውስጥ ያለ፥ የኤሳው ግዛት ነው።ዔሳውም በሴይር ተራራ ተቀመጠ፤ ዔሳው ኤዶም ነው።” (ዘፍ 36 8)
 ዮሴፍ፥ በካራን ተወልዶ፣ በኢትዮጵያ አድጎ፣ በግብፅ የሞተ...
ዮሴፍ፥ የያዕቆብ ልጅ ሁኖ፥ የተወለደው፥ በአያቶቹ አገር በካራን (በዛሬዋ ሶርያ) አካባቢ ነው።አሁንም ልጄ ሆይ ቃሌን ስማ፤ ተነሣና ወደ ካራን ምድር ወደ ወንድሜ ወደ ላባ ሂድ፤” (2743)ያዕቆብም ቤርሳቤህ ወጥቶ ወደ ካራን ሄደ።” (ዘፍ 2810)
እናቱም ያቆብ የሚወዳት ሚስቱ ራሄል ናት። ያቆብ ከወንድሙ ከኤሳዊ፥ ከሽሽት ሲመለስ፤ ዮሴፍም ወደ አባቱ አገር ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ አደገ።ራሔልም ዮሴፍን ከወለደች በኋላ ያዕቆብ ላባን እንዲህ አለው፦ ወደ ስፍራዬ ወደ አገሬ እመለስ ዘንድ አሰናብተኝ።” (ዘፍ 3025)
የስሙ ፍች፥ መስፋት፣ መብዛት፣ መጨር ... ማለት ነው። ስሙንም፦ እግዚአብሔር ሁለተኛ ወንድ ልጅን ይጨምርልኝ ስትል ዮሴፍ ብላ ጠራችው” (ዘፍ 30: 24)
በህልሙ ምክንያት፥ በቅናት፥ በወንድሞቹ ለግብፅውያን ተሸጠ። ዮሴፍ፥ ከኢትዮጵያ በወንድሞቹ ወደ ግብፅ መሸጡን እንረዳለን።እነዚያ ምድያም ሰዎች ግን ዮሴፍን በግብፅ ለፈርዖን ጃንደረባ ለዘበኞቹ አለቃ ለጲጥፋራ ሸጡት።(ዘፍ 3736)
የሸጡት ምድያማውያን፥ ማለት በኢትዮጵያ የነበሩ የአብርሃም ወገኖች፥ የምድያም ጎሳዎች ናቸው። እስማኤላውያንም ወደ ግብፅ የወሰዱት ኢትዮጵያውያን ናቸው። የምድያም ነጋዴዎች፥ ኢትዮጵያውያን ጎሳዎች፤ እስማኤላውያንም ሌላ የኢትዮጵያ ጎሳዎች ናቸው። እነሱም ለግብፅ ነጋዴዎች ዮሴፍን ሸጡት...ምድያም ነጋዶችም አለፉ፤ እነርሱም ዮሴፍን አንሥተው ከጕድጓድ አወጡት፤ እስማኤላውያንም ዮሴፍን በሀያ ብር ሸጡት፤ እነርሱም ዮሴፍን ወደ ግብፅ ወሰዱት።” (ዘፍ 37: 28)
ወንድሞቹንና አባቱን ከኢትዮጵያ ወደ ግብፅ አስወሰደ።
በግብፅ ሁለቱን ልጆቹን፥ ምናሴንና ኤፍሬምን ወለደ።
የዮሴፍም ሆነ የሁለቱ ልጆቹ የስማቸው ፍች፥ የኢትዮጵያውያንን ቋንቋ መሰረት ያደረገ ነው። ለምሳሌ፥ኤፍሬምየተባለውን ልጅ፥ የስሙን ፍችና ስርዎ ቃል ስንመረምር፥
ኤፍሬም ~ Ephraim: የፍሬያም ፍሬያም፣ ፍርያማ፣ ዘረ ብዙ... ማለት ነው። ፍሬያም ከሚለው ቃል የመጣ ስም ነው። የስሙ ምንጭ ፍሬ የሚለው ቃል ነው። የእንግሊዝኛውም የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት እንዲህ ይፈታዋል፥
Ephraim: The name “Ephraim” means fruitful; increasing, HBN,
የሁለተኛውንም ስም ኤፍሬም ብሎ ጠራው፥ እንዲህ ሲል፦ እግዚአብሔር በመከራዬ አገር አፈራኝ (ዘፍ 4152)
ዮሴፍ፥ በመቶ አሥር ዓመት ዕድሜው፥ የሞተው፥ ተሽጦ በሄደበትና በኖረበት ግብፅ ነው። ከሞተ ከአራት መቶ ዓመት በኋላ፥ አጽሙ ፈልሶ፥ ለዘለዓለሙ ያረፈው በዛሬዋ ኢትዮጵያ፥ ምሥራቅ አፍሪካ ውስጥ ነው። ዮሴፍም የእስራኤልን ልጆች፦ እግዚአብሔር ሲያስባችሁ አጥንቴ ከዚህ አንሥታችሁ እናንተ ጋር ውሰዱ ብሎ አማላቸው።” (ዘፍ 50: 25)
 ኬጡራ ኢትዮጵያዊቱ የአብርሃም ሚስት፥ የምድያም እናት፥
አብርሃምም ደግሞ ስምዋ ኬጡራ የተባለች ሚስት አገባ።” (ዘፍ 25: 1)
ኢትዮጵያዊት ሴት ናት። ጉሳዋም፥ በኢትዮጵያ ከነበሩ ጎሳዎች አንዱ፥ ከነበረው፥ ኬጢ የተባለው ነው። ሳራ ስትሞት፥ አብርሃም ኬጡራን አገባ።
            ከአብርሃም ስድስት ልጆችን ወለደች፥ እርስዋም ዘምራንን፥ ዮቅሳንን፥ ሜዳንን፥ ምድያምን፥ የስቦቅን፥ ስዌሕን ወለደችለት። (ዘፍ 25: 2)
እንግዲህ፥ ምድያም የተባለው ከልጆቿ አንዱ ሲሆን፥ በሱም፥ ኢትዮጵያ፥ የምድያም አገር በመባል ተጠርታለች። (ዕን 37)
ሙሴ ከግብፅ ሸሽቶ በኢትዮጵያ ሲኖር፥ ለወገኖቹ በምድያም አገር ኖርሁ ያላቸው ለዚህ ነው። [የንገሥ ዳዊት ኦሪዮን ወታደር ሚስቱ፥ ቤር ሳባ፤ የንጉሥ ስሎሞን እናት፥ የትውልድ ሐረጋቸው ኬቲያውያን (ኢትዮጵያውያን) መሆናቸውን ልንገነዘብ ይገባል።]
አብርሃም ኢትዮጵያ ውስጥ፥ ስማቸው ያልተጠቀሰ፥ ኢትዮጵያውያን ቁባቶች እና ልጆች ነበሩት።
 ምድያም ከኢትዮጵያዊት ሚስቱ፥ ከኬጡራ፥የተወለደ፥ የአብርሃም ልጅ፥
አብርሃም ከኢትዮጵያዊቱ ሚስቱ፥ ከኬጡራ፥ በኢትዮጵያ የወለደው። ሙሴ፥ እስራኤላውያንን ከግብፅ ለማውጣት ከኢትዮጵያ ወደ ግብፅ ሲመለስ በምድያም አገር ኖርሁ አላቸው።
የምድያም ሰዎች ዮሴፍን ወደ ግብፅ ሸጡት፥ምድያም ነጋዶችም አለፉ፤ እነርሱም ዮሴፍን አንሥተው ከጕድጓድ አወጡት፤ ለእስማኤላውያንም ዮሴፍን በሀያ ብር ሸጡት፤ እነርሱም ዮሴፍን ወደ ግብፅ ወሰዱት።” (ዘፍ 3728)እነዚያ ምድያም ሰዎች ግን ዮሴፍን በግብፅ ለፈርዖን ጃንደረባ ለዘበኞቹ አለቃ ለጲጥፋራ ሸጡት።” (ዘጸ 3628)
ኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ አየሁ፤ ምድያም አገር መጋረጃዎች ተንቀጠቀጡ።” (ዕን 37)
 
 
ምዕራፍ ሁለት
 ሙሴ በኢትዮጵያ፥
 እግዚአብሔርም ሙሴን ምድያም ነፍስህን የሚሹአት ሰዎች ሁሉ ሞተዋልና ተመልሰህ ወደ ግብፅ ሂድ አለው።” (ዘጸ 4: 19)
በዚህ ምዕራፍ የምናነሳቸው ነጥቦች፥ ከግብፅ ንጉሥ፥ ከፈርዖን ሸሽቶ 40 ዓመት የኖረው የት ነው? ምድያም የተባለው አገር የት ነው? እግዚአብ የተገለጠለት ኮሬብ (ሲና) የት ነው? ሙሴ፥ ለምን ሚስቱን እና ልጆቹን መለሳቸው? ሙሴና እስራኤላውያን ያቋረጡት የውኃ አካል የቱ ነው? አሮን እና ማርያም በሙሴ ላይ ለምን ተናገሩ? ጽላቱን የተቀበለው ሲና የት ነው? ከግብፅ ከወጡ በኋላ 40 ዓመት የኖሩ የት ነው? ኦባብ ማን ነው? ለእስራኤላውያን ነጻነት አስተዋጾውስ ምንድን ነበረ? ሙሴ የሞተው እና የተቀበረው የት አገር ነው? እነዚህን እና ሌሎች ጥያቄዎችን እያነሳን፥ አጥጋቢ መልስና ማብራሪያ ለማቅረብ ይሞከራል።
ሙሴ የተወለደው በግብፅ፣ ያደገው በፈርዖን ቤት፣ የኖረውና ሙቶ የተቀበረው ከአፍሪካ ሳይወጣ ነው። የተወለደውና እስከ አርባ ዓመቱ የኖረው በግብፅ ሲሆን፤ ቀሪውን ሰማኒያ ዓመት፤ የኖረውና የተቀበረው በዛሬዋ ኢትዮጵያ ነው።
የተወለደበት ዘመንም፤ እስራኤላውያን በግብፅ አገር፥ በባርነት በኖሩበት ዘመን፥ የዛሬ ሦስት ሺሕ አራት መቶ ሃምሳ ዓመት ገደማ ነው።
ሙሴ በአርባ ዓመቱ፥ አንድ ግብጻዊ ገድሎ፤ ከግብፅ ንጉሥ፤ ከፈርዖን ሸሽቶ የሄደው ወደ ምድያም አገር፤ ወደ ኢትዮጵያ ነው። ፈርዖንም ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ሙሴን ሊገድለው ፈለገ። ሙሴ ግን ከፈርዖን ፊት ኰበለለ፥ በምድያምም ምድር ተቀመጠ፤ በውኃም ጕድጓድ አጠገብ ዐረፈ።” (ዘጸ 2: 15)
ኢትዮጵያዊቱን ሲፓራን አግብቶ፥ ሁለት ልጆችን ወለደ። ሲፓራ፥ የምድያም ካህን የዮቶር ልጅ ናት። ዮቶር ከመጀመሪያው የእስራኤላውያን ካህን፥ ከአሮን በፊት የነበረ ኢትዮጵያዊ ካህን ነው።
በኢትዮጵያ እያለ በኮሬብ ተራራ እግዚአብሔር ተገለጠለት። ወደ ግብፅ ተመልሶ፥ በብዙ ታምራት ዕብራውያንን፥ ከግብፅ ባርነት ነጻ አወጣ።
እስራኤላውያንን ከግብፅ ባርነት አላቆ፤ ያባይን ወንዝ ከፍሎ፤ ያመጣቸው እና አርባ ዓመት ያኖራቸው በዛሬዋ ኢትዮጵያ ነው።
የቃል ኪዳን ታቦቱን የተቀበለበት፥ ሲና ወይም ኮሬብ ተራራ በዛሬዋ ኢትዮጵያ ነው።
 የኤርትራ ባሕር ሙሴና እስራኤላውያን ያቋረጡት የውኃ አካል፥ 40 ዓመታት በምድረ በዳ/ በአዳ (ባእዳ) ከግብፅ ከወጡ በኋላ የኖሩበት አገር፥ ሙሴ፥ ጽላቱን የተቀበለበት ቦታ፥
   የፈርዖንን ሰረገሎች ሠራዊቱንም በባሕር ጣላቸው፤ የተመረጡት ሦስተኞች በኤርትራ ባሕር ሰጠሙ።” (ዘጸ 154) 
አባቶቻችሁም በወንዝ ማዶ በግብፅም ውስጥ ያመለኩአቸውን አማልክት ከእናንተ አርቁ፥ እግዚአብሔርንም አምልኩ።” (ኢያ 24: 14)
ይህ የኤርትራ ባሕር የተባለውና፥ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ከግብፅ ባርነት ባሕርን አቋርጦ ያሻገራቸው፥ የውኃ አካል የአባይ ወንዝን ነው።
በኢሳያስ ትንቢት፤ ስለ ግብፅ ሸክም የተነገረው፥ ስለ አባይ ወንዝ መሆኑ የታወቀ  ነው። ውኆችም ባሕር ይደርቃሉ፥ ወንዙ ያንሳል ደረቅም ይሆናል። ወንዞቹም ይገማሉ፥ የግብፅም መስኖች ያንሳሉ ይደርቃሉም፤ ደንገል ቄጤማ ይጠወልጋሉ። በዓባይ ወንዝ ዳር ያለው መስክ በዓባይም ወንዝ አጠገብ የተዘራ እርሻ ሁሉ ይደርቃል፥ ይበተንማል፥ አይገኝምም።” (ኢሳ 19: 5-7)And they shall turn the rivers far away; and the brooks of defence shall be emptied and dried up: the reeds and flags shall wither.” (ኢሳ 19:6)
ባሕርም፥ ወንዝም ተብሎ የተጠራው አንድ የውኃ አካል እንደሆነ፥ ወንዞች ባሕር እየሰሩ ጉዟቸውን እንደሚቀጥሉ ያሳያል። ይህም የአባይ (የናይል) ወንዝ፥  በግብፅ ባሕር እንደሚሠራ ያሳያል። የአባይ ወንዝ፥ ግብፅንና ኢትዮጵያን የሚለያይ ድንበር ሲሆን፥ በኢትዮጵያ  በኩል ባሕረ ኤርትራ ሲባል፥ በግብፅ በኩል ደግሞ የግብፅ ወንዝ (ባሕር) ተብሎ ይጠራል። ይህም የአባይ (የናይል) ወንዝ፥  በግብፅ ባሕር እንደሚሠራ ያሳያል።
ሙሴ፥ የኢትዮጵያዊ አማቱን በጎች እየጠበቀ፥ በኮሬብ ተራራ ከተገለጠለት፤ የተገለጠለት በኢትዮጵያ እንጅ በሌላ አገር ሊሆን አይችልም። እግዚአብሔር በኮሬብ ተራራ የተገለጠለት ገና ወደ ግብፅ ሳይመለስ፥ ህዝቡንም ሳያወጣ ነው፥ኮሬብየእግዚአብሔር ተራራ መባሉ፥ በኢትዮጵያ  ውስጥ በመሆኑና፥ በዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን የሚያመልኩ ኢትዮጵያውያን ብቻ በመሆናቸው፥ሙሴም የዮቶርን የአማቱን የምድያምን ካህን በጎች ይጠብቅ ነበር፤ ወደ ምድረ በዳ ዳርቻም በጎቹን ነዳ፥ ወደ እግዚአብሔርም ተራራ ወደ ኮሬብ መጣ።” (ዘጸ 31)አርባ ዓመትም ሲሞላ የጌታ መልአክ ሲና ተራራ ምድረ በዳ በቍጥቋጦ መካከል በእሳት ነበልባል ታየው።” (ሐዋ 7: 30)
ሙሴ የተሰጠውን፥ እስራኤልን ከግብፅ ባርነት ነጻ የማውጣት ተልኮ ማረጋገጫው፥ እስራኤልን ከግብፅ አውጥቶ፥ በኮሬብ እግዚአብሔርን ማምለክ ነው።እርሱም፦ በእውነት እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ እኔም እንደ ላክሁህ ምልክትህ ይህ ነው ሕዝቡን ከግብፅ ባወጣህ ጊዜ በዚህ ተራራ ላይ ለእግዚአብሔር ትገዛላችሁ አለ።(ዘጸ 312)
እስራኤላውያን ከግብፅ እንደወጡ የመጡት፤ ወደ ደቡብ እና ወደ ኢትዮጵያ መሆኑ ሌላው ማረጋገጫ ይህ ነው። እንዲህም ሆነ ፈርዖን ሕዝቡን በለቀቀ ጊዜ፥ ምንም ቅርብ ቢሆን እግዚአብሔር በፍልስጥኤማውያን ምድር መንገድ አልመራቸውም፤ እግዚአብሔር፦ ሕዝቡ ሰልፉን ባየ ጊዜ እንዳይጸጽተው ወደ ግብፅም እንዳይመለስ ብሎአልና።” (ዘጸ 13: 17)
ወደ ኢትዮጵያ ይዟቸው መጣ፤ በሚለው ከተስማማን፥ ጽላቱንም የተቀበለው፤ በዚያው ተራራ፤ መጀመሪያ በጎቹን ሲጠብቅ በተገለጠለት፤ በኮሬብ ተራራ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ መሆኑን እንገነዘባለን።እግዚአብሔርም ከሙሴ ጋር ሲና ተራራ የተናገረውን በፈጸመ ጊዜ በእግዚአብሔር ጣት የተጻፈባቸውን ከድንጋይ የሆኑ ሁለቱን የምስክር ጽላቶች ሰጠው።(ዘጸ 3118) በታቦቱም ውስጥ የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ምድር በወጡ ጊዜ እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን ባደረገ ጊዜ፥ ሙሴ ኮሬብ ካስቀመጣቸው ከሁለቱ የድንጋይ ጽላቶች በቀር ምንም አልነበረበትም።
ኮሬብ ተራራ እና ሲና ተራራ፤ የአንድ ቦታ ሁለት ስሞች መሆናቸውን ልብ ልንል ይገባል። ቀጥሎ የምናያቸው ጥቅሶች፥ የኮሬብን እና የሲና ተራራን አንድ መሆን አጉልቶ ያሚያሳዩ ናቸው። ኮሬብ ጥጃን ሠሩ፥ ቀልጦ ለተሠራ ምስልም ሰገዱ።” (መዝ 106: 19) በኮሬብ ተራራ ጥጃ ሠርተው ያመለኩት ከግብፅ ከወጡ በኋላ መሆኑ ይታወቃል፥አምላካችን እግዚአብሔር ኮሬብ ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ።” (ዘዳ 52)
ሙሴ ትዕዛዛትን በኢትዮጵያ ለመሆኑ ሌላው ማስረጃ፤ በሞአብ ምድር፥ ማለቱ ነው። ሞባውያን የሎጥ ልጆች፥ ሁነው፥ በኢትዮጵያ የነበሩ መሆኑ በቂ ማስረጃ አለ።ኮሬብእናሞዓብ ምድርየአንድ አገር ግዛቶች ሲሆኑ እስራኤላውያን ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን ያደረጉበት መሆኑን ነው። እግዚአብሔር ኮሬብ ካደረገው ቃል ኪዳን ሌላ በሞዓብ ምድር ከእስራኤል ልጆች ጋር ያደርገው ዘንድ ሙሴን ያዘዘው የቃል ኪዳኑ ቃሎች እነዚህ ናቸው።” (ዘዳ 29: 1)
ከግብፅ ወጥተው፥ ወደ ደቡብ ለመምጣታቸውና፤ በምሥራቅ አፍሪካ ለመቆየታቸው ሌላው ማስያ፥ይህን ተራራ መዞር ይበቃችኋል ተመልሳችሁ ወደ ሰሜን ሂዱ።(ዘዳ 23)
ከላይ ያሉትን ጥቅሶች ስንመረምር፥
በዚህ ተራራ ላይ ለእግዚአብሔር ትገዛላችሁ...” የሚለው፥ እስራኤላውያን ከግብፅ ሲወጡ የሄዱት መጀመሪያ ሙሴ የአማቱን  በግ ሲጠብቅ ወደተገለጠለት ተራራ ወደ ኮሬብ መሆኑ ነው።
“...ሰሜን ሂዱየሚለው፥ የሚጠቁመው ከግብፅ ሲወጡ የሄዱት ወደ ደቡብ መሆኑን ነው፥በፍልስጥኤማውያን ምድር መንገድ አልመራቸውም...” ይህ ጥቅስ የሚያሳውቀን፥ እስራኤላውያን ከግብፅ እንደወጡ ወደ አረብ አገር ወይም ወደ ከነዓን ሳይሆን በተቃራኒው፥ ወደ ደቡብ ወደ ኢትዮጵያ መሆኑን ነው።
ሙሴም እግዚአብሔርን፦ እነሆ፥ እኔ ወደ እስራኤል ልጆች በመጣሁ ጊዜ፦ የአባቶቻችሁ አምላክ ወደ እናንተ ላከኝ ባልሁም ጊዜ፦ ስሙስ ማን ነው? ባሉኝ ጊዜ፥ ምን እላቸዋለሁ? አለው።” (ዘጸ 3: 13) በግብፅ በባርነት ሲኖሩ፥ አምላክ እግዚአብሔርን እንደማያውቁ፥ ከዚህ እንገነዘባለን።
እግዚአብሔርም ሙሴን፦ «ያለና የሚኖር» እኔ ነኝ አለው፤ እንዲህ ለእስራኤል ልጆች፦ «ያለና የሚኖር» ወደ እናንተ ላከኝ ትላለህ አለው።(ዘጸ 3: 14) ያለ እና የሚኖር ማለት፥  ዘለለማዊ፣ የማያልፍ ... የሚለው የአምላክ ስም ሲሆን፤ ይህም ያ፣ ያህዌ፣ ህያው... የሚል ስያሜን ያስገኘ ነው።
አባቶቻችሁም ወንዝ ማዶ ግብፅ ውስጥ ያመለኩአቸውን አማልክት ከእናንተ አርቁ፥ እግዚአብሔርንም አምልኩ።” (ኢያ 24: 14) ይህ ጥቅስ የሚነግረን፤ እስራኤላውያን ከግብፅ ሲወጡ ያቋረጡት የወኃ አካል፥ ባሕር ተብሎ ከመጠራቱ በተጨማሪ፥ ወንዝ ተብሎም እንደተጠራ ነው። ሙሴ ከፍሎ ያሻገራቸውን ባሕር፥ መጀመሪያ በስም አልጠቀሰውም።
ይህ ባሕር የእንግሊዝኛው መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው፥ ቀይ ባሕር፥ ሳይሆን ሌላ ነው።ከግብፅ ምድር በወጣችሁ ጊዜ እግዚአብሔር ኤርትራን ባሕር በፊታችሁ እንዳደረቀ፥ በዮርዳኖስም ማዶ በነበሩት እናንተም ፈጽማችሁ ባጠፋችኋቸው በሁለቱ በአሞራውያን ነገሥታት፥ በሴዎንና በዐግ ያደረጋችሁትን ሰምተናል።” (ኢያ 210 እና 423)ኤርትራን ባሕር ገሠጸ እርሱም ደረቀ፤ እንደ ምድረ በዳ በጥልቅ መራቸው።” (መዝ 106 9 እና 13613) ይህም ግብጾች በሚጠሩበት ስም የናይል ባሕር ወይም የአባይ ባሕር ነው። የአማርኛው መጽሐፍ ቅዱስየኤርትራ ባሕርብሎ መዝግቦት እናገኛለን። የዛሬው ቀይ ባሕር ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ የሚታወቀው፥ ጨው ባሕር እና ዓረባ ባሕር፥ በመባል ነው።በምሥራቅም በኩል ያለውን ዓረባ እስከ ኪኔሬት ባሕር ድረስ፥ በቤትየሺሞት መንገድ አጠገብ እስካለው እስከ አረባ ባሕር እስከ ጨው ባሕር ድረስ፥ በደቡብም በኩል ከፈስጋ ተራራ አፋፍ በታች ያለውን ምድር የገዛው የአሞራውያን ንጉሥ ሴዎን፤” (ኢያ 123)
ባሕር፥ ለትንሹም ለትልቁም የውኃ አካል መጠሪያ ይሆናል፥ ለኩሬ፣ ለሐይቅ፣ ለወንዝ፣ ለውቃያኖስ... ይሰጣል። (ኪወክ) ውኆችም ባሕር ይደርቃሉ፥ ወንዙ ያንሳል ደረቅም ይሆናል።” (ኢሳ 19: 5) ግብጾች የአባይ ወንዝን አገራቸው ውስጥባሕር አል ኒል ወይም የናይል ባሕርብለው ይጠሩታል።
ንጉሥ ዳዊት ስለ እስራኤል አወጣጥ በጻፈው ማስረጃ፥ ወንዙን በእግራቸው ተሻገሩ ብሏል፥ ባሕር የብስ አደረጋት፥ ወንዙን በእግር ተሻገሩ፤ በዚያ በእርሱ ደስ ይለናል። (መዝ 66: 6) እዚህ ላይ፥ አጽንዖት ልንሰጠው የሚገባ፥ የአባይ ወንዝ ወንዝነቱን እንደጠበቀ በግብፅ ምድር፥ ባሕር ስለሚሠራ፥ ባሕር እየተባለ መጠራቱን ነው። ይህም የሚያስረዳን እስራኤላውያን ከግብፅ ሲወጡ ያቋረጡት ባሕር፥ የአባይ ወንዝ መሆኑን ነው። ቀይ ባሕር፥ ባሕር ሲሆን ባሕር እንጅ፥ መቸም ወንዝ ተብሎ አልተጠራም። እንዲያውም ዛሬ ቀይ ባሕር እየተባለ የሚጠራው የባሕር አካል፥ በዚያን ዘመን፥ ጨው ባሕር እና የአረብ ባሕር በመባል እንጅ፥ ቀይ ባሕር በመባል በአማርኛው መጽሐፍ ቅዱስ አልተጠራም። [ማይጨው፥ የተባለው በሰሜን ኢትዮጵያ የሚገኘው የቦታ ስያሜም ከዚሁ ጋር የተያያዘ ነው።]
ቀይ ባሕርን ወንዝ ብሎ መጥራት አይችልም፤ የአባይ ወንዝ ግን  በግብፅውያን ባሕር ተብሎ እንደሚጠራ አውቀናል። ስለዚህ፥ እስራኤላውያን ከግብፅ ወጥተው፥ የአባይን ወንዝ (ባሕር) አቋረጠው አፍሪካ ውስጥ ቀሩ እንጅ የትም አልሄዱም።
እስራኤላውያን፥ በግብፅ ምድር ለአራት መቶ ዓመት በባርነት ሲኖሩ፤ ያመልኩ የነበረው እግዚአብሔርን ሳይሆን ሌሎችን የግብፅን አማልክትን መሆኑን፥ ይልቁንም እግዚአብሔርን ያወቁትና ያመለኩት በሲና ምድረ ባዕዳ፥ በኢትዮጵያ መሆኑን ነው።
ኢያሱም፥እግዚአብሔርንም ማምለክ ክፉ መስሎ ቢታያችሁ፥ አባቶቻችሁ በወንዝ ማዶ ሳሉ ያመለኩአቸውን አማልክት ወይም በምድራቸው ያላችሁባቸውን የአሞራውያን አማልክት ታመልኩ እንደ ሆነ፥ የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ። እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን(ኢያ 2415) አሞራውያን በኢትዮጵያ የነበሩ፤ አምልኮተ እግዚአብሔርን ያላወቁ ጎሣዎች ናቸው።  አባቶቻችሁም ወንዝ ማዶ ግብፅ ውስጥ ያመለኩአቸውን አማልክት ከእናንተ አርቁ፥ እግዚአብሔርንም አምልኩ።” (ኢያ 24: 14) ከግብፅ ከወጡ በኋላ ሌሎችን የአሞራውያንንም አማልክት እንዳመለኩ እና እግዚአብሔርን ማምለክ በፈቃድ እንጅ በተጽእኖ አለመሆኑንም እንማርበታለን።
በጠቅሉ፥ ኢያሱአባቶቻችሁ በወንዝ ማዶ፥ በግብፅ ሳሉያለው የአባይን ወንዝ እንጂ፥ ቀይ ባሕርን አይደለም። ቀይ ባሕርን ተሻግረው ቢሆን፥አባቶቻችሁ በባሕር ማዶ ሳሉይል ነበር።
 የምድያም አገር፥ ከግብፅ ንጉሥ፥ ሸሽቶ የኖረበት፥
ኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ አየሁ፤ ምድያም አገር መጋረጃዎች ተንቀጠቀጡ።” (ዕን 37) ድንኳን እና መገጋረጃ፥ በአንድ ቦታ ሳይለያዩ  መገኘታቸውን ልናስተውል ይገባል።
ዚህ ጥቅስ የምንረዳው ኢትዮጵያ እና የምድያም አገር፥ የአንድ ቦታ ወይም አገር ሁለት ስሞች መሆናቸውን ነው። ይህም፤ አቢሲኒያ ብሎ፥ የምኒልክ አገር፥ እንደማለት ነው። ሙሴ ወደ ግብፅ ተመልሶ አርባ ዓመት የኖርሁበት አገር፥የምድያም አገርነው፥ ያላቸው ኢትዮጵያ መሆኑን ያሳያል።
ምድያም የአብርሃም ልጅ፥ ከኬጡራ የወለደው መሆኑ በኢትዮጵያና ከኢትዮጵያዊት መሆኑን ያሳያል። ይህም ምድር የሲና ወይም የኮሬብ ምድር በኢትዮጵያ መሆኑን ያረጋግጥልናል።
ከሙሴ ታሪክ ጋር በተያያዘ፥ የሚጠቀሱ የቦታ እና የሰው ስሞች፥
ኮሬብ፣ ሲና... ሲፓራ፣ ዮቶር፣ ኦባብ...
እራኤላውያን፥ በግብፅ አገር በባርነት አራት መቶ ዓመት ኖሩ። ቁጥራቸው እየበዛ ስለሄደ፥ ከጠላቶቻችን ጋር ወግነው ያጠቁናል፥ ብለው ግብጾች እስራኤላውያንን ፈሩ።የእስራኤልም ልጆች አፈሩ፥ እጅግም በዙ፥ ተባዙም፥ አጅግም ጸኑ፤ ምድሪቱም በእነርሱ ሞላች በግብፅም ዮሴፍን ያላወቀ አዲስ ንጉሥ ተነሣ።የእስራኤላውያንን የህዝብ ቁጥር ለመቀነስና ለመቆጣጠር፤ የሚወለዱ ወንድ እስራኤላውያን፥ ወደ አባይ ባሕር እንዲጣሉ፥ ትእዛዝ ወጣ።
ሙሴ ሲወለድ፥ እናቱ፥ በሚንሳፈፍ ቅርጫት አድርጋ በአባይ ወንዝ ላይ ጣለችው። የፈርዖን ልጅ፥ ገላዋን ለመታጠብ ስትወርድ፥ አየችውና ከባሕር አስወጥታ፥ በቤተ መንግሥት አሳደገችው። ሕፃኑም አደገ፥ ወደ ፈርዖንም ልጅ ዘንድ አመጣችው፥ ለእርስዋም ልጅ ሆነላት። እኔ ከውኃ አውጥቼዋለሁና ስትልም ስሙን ሙሴ ብላ ጠራችው።” (ዘጸ 2: 10)
እናቱ ሞግዚት መስላ ስላሳደገችው፥ ግብጻዊ ሳይሆን፥ እስራኤላዊ መሆኑን እያወቀ አደገ።
በአርባ ዓመቱ፥ እስራኤላዊ ወገኖቹ በሚኖሩበት አካባቢ ለመጎብኘት በሄደበ በተፈጠረ ጠብ፥ አንድ ግብጻዊ ሰው ገደለ። ይህን ነገርም ፈርዖን እንደሰማ ሲያውቅ፥ ከግብፅ ኮብልሎ፥ ወደ ምድያም አገር፥ ወደ ኢትዮጵያ መጣ።
በምድያም አገርም፥ በውኃ ጉድጓድ አጠገብ፥ የኢትዮጵያዊውን ካህን፥ የዮቶርን ሴት ልጆች ተዋወቀ። እነሱም ወደ ቤታቸው ወስደው፥ ከአባታቸው ጋር አስተዋወቁት ሙሴም ከዚያ ሰው ጋር ሊቀመጥ ወደደ፤ ልጁንም ሲፓራን ለሙሴ ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠው።” (ዘጸ 221) ኢትዮጵያዊቱን ሲፖራን አገባ፥ ከአማቱ ከካህኑ ከዮቶር ሥርዓተ አምልኮን ተማረ። የሙሴ ሚስት፥ ሲፓራ፥ ምድያምዊት ከሆነች እና ኢትዮጵያዊት ከተባለች፤ የምድያም አገርም፥ ኢትዮጵያ ነው፥ ማለት ነው።
 ኮሬብ / ሲና እግዚአብ ለሙሴ የተገለጠለት ተራራ፥
ሙሴም ዮቶር የአማቱን ምድያምን ካህን በጎች ይጠብቅ ነበር፤ ወደ ምድረ በዳ ዳርቻም በጎቹን ነዳ፥ ወደ እግዚአብሔርም ተራራ ወደ ኮሬብ መጣ።” (ዘጸ 31) እግዚአብሔርም ሙሴን በምድያም፦ ነፍስህን የሚሹአት ሰዎች ሁሉ ሞተዋልና ተመልሰህ ወደ ግብፅ ሂድ አለው።” (ዘጸ 4: 19)
በኢትዮጵያ እየኖረ፥ አርባ ዓመት ሲሆነው፥ የአማቱን በጎች ሲጠብቅ እግዚአብሔር በኮሬብ ተገለጠለት፥እግዚአብሔርም ተራራየሚባል እሳቤ በዚያን ዘመን የነበረው፥ በኢትዮጵያ ብቻ ነው።
የምድያም ከህን...’ ኢትዮጵያዊ፥ የምድያም አገርም ኢትዮጵያ ናት።
ወደ ምድረ በዳም...’ ‘ወደ ምድረ ባዕዳነው። እሱም ወደ ግብፅ አዋሳኝ አገር ማለት ነው። ከግብፅ ሲወጡም ወደ ምድረ በዳ የተባለውም፥ ምድረባዕዳነው። ግብፅ ለኢትዮጵያውያን ባዕድ አገር፤ ኢትዮጵያውያንም ለግብጻውያን ባዕድ ስለሆኑ ነው።
ኮሬብ እና ሲና በመባል የሚታወቀው፥ የተራራና የቦታ ስም፥ የአንድ ስፍራ ሁለት መጠሪያ ነው። እግዚአብሔር ለሙሴ የተገለጠለት፥ ሙሴ የኢትዮጵያዊውን ካህን፥ የአማቱን የዮቶርን በጎች ሲጠብቅ ነው፥ እግዚአብሔርም ሙሴን በምድያም፦ ነፍስህን የሚሹአት ሰዎች ሁሉ ሞተዋልና ተመልሰህ ወደ ግብፅ ሂድ አለው።” (ዘጸ 4: 19)
በዚህ ስፍራ እግዚአብሔር ለሙሴ ተገለጠለት። በዚህም ስፍራ ሙሴ እስራኤላውያንን ከግብፅ ከአወጣ ብኋላ፥ ለእግዚአብሔር አምላክ የአምልኮ ሥርዓት እንደሚፈጽም፥ ምልክት ሰጠው፥ እርሱም፦ በእውነት እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ እኔም እንደ ላክሁህ ምልክትህ ይህ ነው ሕዝቡን ከግብፅ ባወጣህ ጊዜ በዚህ ተራራ ላይ ለእግዚአብሔር ትገዛላችሁ አለ።(ዘጸ 312)
በዚህም ስፍራ እስራኤላውያን ከግብፅ ከወጡ በኋላ፥ ለሙሴ አሥርቱን ትእዛዛት ሰጠው።
ከዚህ የምንረዳው፥ ሙሴ እስራኤላውያንን ከግብፅ ካወጣ በኋላ፥ የተመለሰው ወደ ኢትዮጵያ መሆኑን ነው።
ሙሴ እስራኤላውያንን ከግብፅ ባርነት አውጥቶ ወደ ቃል ኪዳን አግራቸው እንደሚያስገባቸው ቃል ሲገባ፥ ለምልክት እና ለማስራጃ ከግብፅ ከወጡ በኋላ የሚመጡት ወደ ኮሬብ ምድር መሆኑን ይጠቁማል።
እስራኤላውያን ከግብፅ ሲወጡ ያቋረጡት የአባይን ወንዝ መሆኑን፥አባቶቻችሁም ወንዝ ማዶ ግብፅ ውስጥ ያመለኩአቸውን አማልክት ከእናንተ አርቁ፥ እግዚአብሔርንም አምልኩ።” (ኢያ 24: 14)
እስራኤላውያን በግብፅ ምድር ለአራት  መቶ  ዓመታት በባርነት ሲኖሩ ያመልኩ የነበረው እግዚአብሔርን ሳይሆን ሌሎችን የግብፅን አማልክት መሆኑን፥ ይልቁንም እግዚአብሔርን ያወቁትና  ያመለኩት በሲና  ምድረ ባዕዳ መሆኑን ነው። ከአርባ ዓመት በኋላ ከነዓን ገብተው፥ አንዳንዶች አሁንም የግብፅን አማልክት መከተል አለመተውን ነው፥እግዚአብሔርንም ማምለክ ክፉ መስሎ ቢታያችሁ፥ አባቶቻችሁ ወንዝ ማዶ ሳሉ ያመለኩአቸውን አማልክት ወይም በምድራቸው ያላችሁባቸውን አሞራውያን አማልክት ታመልኩ እንደ ሆነ፥ የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ። እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን።” (ኢያ 2415) ከግብፅ ከወጡ በኋላ ሌሎችን የአሞራውያንንም አማልክት እንዳመለኩ፤ እግዚአብሔርን ማምለክ በፈቃድ እንጅ በተጽእኖ አለመሆኑንም እንማርበታለን።
የአባይ ወንዝ፥ በግብፅ ምድር ባሕር በመሆኑ፥ ጠባብ የሚባለው ሰርጥ ሁለት ኪሎ ሜትር ነው። ከግብፅ አባይን ለመሻገር የሚያበረታታቸው፥ ወንዙን ተሻግረው የብስ፣ ሌላ አገር፥ ደረቅ መሬት ማየታቸው፥ ተስፋ ይሰጣቸዋል። በአንጻሩ ቀይ ባሕር ሰፊ በመሆኑ፥ ተሻግረው መሬት ለማግኘታቸው፥ ምንም ማረጋገጫ ስለሌላቸው፥ ተስፋ ያስቆርጣል።
 ሲፓራ፥ የሙሴ ሚስት፥ ለእስራኤላውያን ነፃነት አስተዋጽዖ፥
·      ሙሴ፥ ለምን ሚስቱን እና ልጆቹን እንደመለሳቸው?
·       አሮን እና ማርያም ለምን በሙሴ ላይ ተናገሩ?
ሙሴም ከዚያ ሰው ጋር ሊቀመጥ ወደደ፤ ልጁንም ሲፓራ ለሙሴ ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠው።” (ዘጸ 221) ሙሴ፥ ከፈርዖን ሸሽቶ፥ ወደ ኢትዮጵያ እንደመጣ የተዋወቀው ሲፓራን እና ስድስት እህቶቿን ነው። በጎቻቸውን ውኃ ሊያጠጡ በነበሩበት ጉድጓድ አጠገብ ሙሴን አገኙት። ወደቤታቸውም ወሰዱት። ከአባታቸው፥ ከዮቶር ጋር ሙሴን አስተዋወቁት ሙሴም ሲፓራን አገባ፥ ሙሴም ኢትዮጵያዊቱን አግብቶአልና ባገባት በኢትዮጵያይቱ ምክንያት ማርያምና አሮን በእርሱ ላይ ተናገሩ።” (ዘኁ 121)
ሁለት ወንድ ልጆችን ወለደችለት። የመጀመሪያው ልጅ ስም፥ ጌርሰም ነው። ፍችውም፥ መጻተኛ ማለት ነው። የሁለተኛው ልጅ ስም ደግሞ፥ አላዛር ነው። ፍችውም፥ ኤል ዘር፣ ያምላክ ወገን፣ የእግዚአብሔር ዘር፣ እግዚአብሔር በመከራዬ ጊዜ እርዳኝ፥ ማለት ነው።
ሙሴ፥ እስራኤላውያንን ከግብፅ ባርነት፥ ነፃ ለማውጣት ሴሄድ፤ ሚስቱን እና ልጆቹን ይዞ ነበር።ሙሴም ሚስቱንና ልጆቹን ወሰደ፥ በአህያ ላይም አስቀመጣቸው፥ ወደ ግብፅም አገር ተመለሰ ሙሴም የእግዚአብሔርን በትር ይዞ ሄደ።” (ዘጸ 420)
በመንገድ ላይ እግዚአብሔር አገኛቸው። ሙሴንም ሊገድለው ሲል ሲፓራ ልጅዋን በመገረዝ ኢትዮጵያይነታቸውን ስላረጋገጠችለት፤ የሙሴን ነፍስ አተረፈች።እንዲህም ሆነ፤ በመንገድ ላይ ባደረበት ስፍራ እግዚአብሔር ተገናኘው፥ ሊገድለውም ፈለገ። ሲፓራም ሚስቱ ባልጩት ወሰደች፥ የልጅዋንም ሸለፈት ገረዘች ወደ እግሩም ጣለችው፤ አንተ ለእኔ የደም ሙሽራ ነህ አለች።ከእርሱም ፈቀቅ አለ። የዚያን ጊዜ፦ ስለ ግርዛቱ አንተ የደም ሙሽራ ነህ አለች።” (ዘጸ 424 - 26) ዚህ ጥቅስ የምንማረው፥ የሙሴ ሚስት ለአብርሃም የተሰጠውን የግርዛት የቃል ኪዳን ምልክት ጠንቅቃ  እንደምታውቅ ነው። በዚህ ድሪጊቷ የሙሴን ህይወት እንዲተርፍና ተልኮውን እንዲያሳካ ከፍተኛ አስተዋጽዖ አድርጋለች። 
ምናልባትም ከሙሴ ይልቅ ሲፓራ የልጇ አለመገረዝ ምን ዓይነት መዘዝ ሊያስከትል እንደሚችል የበለጠ እንደተረዳች እናያለን። በዚህ አጋጣሚ፥ ሲፓራ ልጇን ገርዛ የነሱን ኢትዮጵያዊነት ባታስመሰክር ኑሮ፤ ሙሴም በእግዚአብሔር መልአክ ይቀዘፍና የእስራኤላውያን ከግብፅ ነጻ መውጣትም ይዘገይ ወይም ይቀር ነበር።
 ግርዛት፥ አብርሃም ከእግዚአብሔር ጋር ያደረገው የቃል ኪዳን ምልክት መሆኑ የታወቀ ነው። እዚህ ላይ፥ የሙሴ ሚስትም፥ ለአብርሃም የተሰጠውን የግርዛት የቃል ኪዳን ምልክት ጠንቅቃ እንደምታውቅ እንረዳለን። በግልጽ እንደሚታየው፥ ሙሴ በኮሬብ ትእዛዛትን ከመቀበሉ በፊት፤ ግርዛት፥ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያውያን ዘንድ የነበረ መሆኑን ነው። ብዙ ግልጽ ያልሆነውና ብዙ ያልተነገረለት ታሪክ ግን፥ አብርሃም ቃልኪዳኑን ያደረገው ኢትዮጵያ ውስጥ መሆኑን እና ግርዛት በኢትዮጵያ ብቻ የነበረ ሥርዓት መሆኑን ነው። [ይህም ከላይአብርሃም በኢትዮጵያበሚለው ርዕስ ሥር ተብራርቷል።]
ሙሴ ወደ ግብፅ ከተመለሰ በኋላ፥ የኖረውበምድያም አገርያላቸው፤ ኢትዮጵያ የኖረ መሆኑን ለመሸፈንና አድበስብሶ ለማለፍ ነበር። በግብፅ፥ አራት መቶ ዓመት፥ በክፋ የባርነት፥ አገዛዝ የኖሩ ሰዎች፤ እንኳን የምድያም አገር ኢትዮጵያ መሆኑዋን ሊያውቁ፤ የራሳቸውንም ታሪክ አጥርተው የማወቅ እድሉ አይኖራቸውም።
መጀመሪያ፥ ሙሴ ልጆቹን ሳይገረዙ፥ ወደ ግብፅ ይዟቸው ለመሄድ የፈለገው፤ ኢትዮጵያዊነታቸው እንዳይታወቅና እሱም ኢትዮጵያ መኖሩን ላለማሳዎቅ ነበር። ይህም እስራኤላውያንን ከግብፅ ወደቃል ኪዳን አገራችን ልወስዳችሁ መጣሁ ሲላቸው፥የለም ለኢትዮጵያውያን ልትሸጠን ነው፥ብለው እንዳያስቸግሩት ነበር። ከተገረዙ በኋላ ምክንያት ይሆኑብኛል ብሎ ስለፈራ፥ ወደ አማቱ ቤት ሚስቱን እና ልጆቹን መለሳቸው።
ይህንም ያደረገበት ምክንያት፥ የተገረዙ ልጆችን ይዞ ወደ ግብፅ ቢገባ ሚስቱ ኢትዮጵያዊ መሆኗን በቀላሉ ይረዳሉ፥ ምክንያቱም ግርዛት በዚያን ጊዜ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ብቻ የሚፈጸም የቃል ኪዳን ምልክት ነበር። እንደዛሬው የዜግነት መለያ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት እንደማለት ነው። በዚህም እስራኤላውያንን ከግብፅ ምድር አውጥቶ የሚወሰዳቸው ለኢትዮጵያውያን ሊሸጠን ነው፥ ብለው አንወጣም እንዳይሉት ነው። ይህንም የምናየው እስራኤላውያን ከግብፅ ከወጡ በኋላ፥ በሲና ምድረ በዓዳ፥ አማቱ ሙሴ  መልሷት የነበረውን ሚስቱን ሲወስድለት፥ እህቱ ማሪያምና ወንድሙ አሮን በሙሴ ላይ ሲናገሩ፥ ይህም የሙሴ ሚስት ኢትዮጵያዊ መሆኗን ሲያውቁ፥ ለኢትዮጵያውያን ሊሸጠን ነው ብለው ስለጠረጠሩ ነው።
ይህ ነገር ግልጽ የሚሆነው፤ ሙሴ እስራኤላውያንን ከግብፅ ካወጣቸው በኋላ የተፈጠረውን ክስተት ስንመለከት ነው። የሙሴ አማት፥ ዮቶር፥ ሙሴ እስራኤላውያንን ከግብፅ ባርነት ነፃ አውጥቶ፥ ወደ ኢትዮጵያ እንዳመጣቸው ሲሰማ፤ ሙሴን ለመቀበል ሄደ። በዚያን ጊዜ የሙሴ አማት ዮቶር መልሶአት የነበረውን የሙሴን ሚስት ሲፓራን ሁለቱንም ልጆቿን ወሰደ። የሙሴ አማት ዮቶርም ከልጆቹና ከሚስቱ ጋር በእግዚአብሔር ተራራ አጠገብ በምድረ በዳ ወደ ሰፈረ ወደ ሙሴ መጣ።” (ዘጸ182 እና 5)በእግዚአብሔር ተራራ አጠገብ የሚለው ገለጻ፤ ወደ ኢትዮጵያ ምድር መምጣታቸውን አጉልቶ ያሳያል። ምክንያቱም፥የእግዚአብሔር አገርእናየእግዚአብሔር ተራራየሚባሉ መጠሪያዎች ወይም እሳቤዎች የነበሩት በኢትዮጵያ ብቻ ነበር። በዚህ ጊዜ፥ ማሪያምና አሮን፤ የሙሴ ሚስት ኢትዮጵያዊት መሆኗን ሲያውቁ፤ ሙሴ ከግብፅ ያወጣን በነጻነት ሊያኖረን ሳይሆን፥ ለኢትዮጵያውያን ሊሸጠን ነው፣ ብለው አጉረመረሙ።ሙሴም ኢትዮጵያይትን አግብቶአልና ባገባት ኢትዮጵያይቱ ምክንያት ማርያምና አሮን በእርሱ ላይ ተናገሩ።” (ዘኁ 121)
ሙሴንም፦ በግብፅ መቃብር ስላልኖረ በምድረ በዳ እንሞት ዘንድ አወጣኸንን? ከግብፅ ታወጣን ዘንድ ይህ ያደረግህብን ምንድር ነው?” (ዘጸ 1413) ከዚህ አባባል የምንረዳው፥ እስራኤላውያን በሙሴ ላይ እምነት እንዳልነበራቸው፤ ድብቅ አጀንዳ እንዳለው ያስቡ እንደነበር ነው።
 ዮቶር (ራጉኤል) ኢትዮጵያዊው ካህን እና የሙሴ መምህር፥
የምድያም አገር፥ የኢትዮጵያ፥ ኢትዮጵያዊ ካህን ነው። ልጁን ሲፓራን ለሙሴ ሚስት እንድትሆን ሰጠው።
ሙሴም ከሲፓራ ሁለት ወንድ ልጆችን (ጌርሳም እና አልዓዛር) ወለደ።
ሙሴ ለተልኮው በአምልኮና በአገልግሎት ለአርባ ዓመት የተዘጋጀው፥ በአማቱ በዮቶር አሰልጣኝነትና አስተማሪነት ነው። ይህን የምንገነዘበው፥ ሙሴ እስራኤላውያንን ከግብፅ ባርነት ካላቀቀ እና ወደ ኢትዮጵያ ካመጣቸው ብኋላም፤ አስተዳደርን አማቱ ሲያስተምረው የሚያሳይን ታሪክ በኦሪት ዘጸአት ተመዝግቦ እናገኛለን። ዮቶር፥ ሙሴን አስተማረው ማለት እግዚአብሔር፥ ሙሴን አስተመረው ማለት ነው። ምክንያቱም እግዚአብሔር የማዳን ሥራውን የሠራው በኢትዮጵያውያን በኩል ነው። ኢትዮጵያውያን፥የእግዚአብሔር ምድራዊ ተወካዮች ናቸው ማለት ይቻላል።
የምድያምም ካህን የሙሴ አማት ዮቶር እግዚአብሔር ለሙሴና ለሕዝቡ ለእስራኤል ያደረገውን ሁሉ፥ እግዚአብሔርም እስራኤልን ከግብፅ እንዳወጣ ሰማ።
በዚያን ጊዜ የሙሴ አማት ዮቶር መልሶአት የነበረውን የሙሴን ሚስት ሲፓራን ሁለቱንም ልጆቿን ወሰደ።
ከእነርሱ የአንደኛው ስም ጌርሳም ነበረ፤ አባቱ፦ በሌላ አገር ስደተኛ ነበርሁ ብሎአልና፤
የሁለተኛውም ስም አልዓዛር ነበረ፦ የአባቴ አምላክ ረዳኝ፥ ከፈርዖንም ሰይፍ አዳነኝ ብሎአልና።
የሙሴ አማት ዮቶርም ከልጆቹና ከሚስቱ ጋር በእግዚአብሔር ተራራ አጠገብ በምድረ በዳ ወደ ሰፈረ ወደ ሙሴ መጣ።
ሙሴንም፦ እኔ አማትህ ዮቶር፥ ሚስትህም፥ ከእርስዋም ጋር ሁለቱ ልጆችዋ መጥተንልሃል አለው።
ሙሴም አማቱን ሊገናኝ ወጣ፥ ሰገደም፥ ሳመውም፤ እርስ በርሳቸውም ደኅንነታቸውን ተጠያየቁ፥ ወደ ድንኳኑም ገቡ።
ሙሴም እግዚአብሔር በፈርዖንና በግብፃውያን ላይ ስለ እስራኤል ያደረገውን ሁሉ፥ በመንገድም ያገኛቸውን ድካም ሁሉ፥ እግዚአብሔርም እንዳዳናቸው ለአማቱ ነገረው።
ዮቶርም እግዚአብሔር ለእስራኤል ስላደረገው ቸርነት ሁሉ፥ ከግብፃውያንም እጅ ስላዳናቸው ደስ አለው።
ዮቶርም፦ ከግብፃውያንና ከፈርዖን እጅ ያዳናችሁ፥ ከግብፃውያንም እጅ ሕዝቡን ያዳነ እግዚአብሔር ይባረክ።
ትዕቢት ባደረጉባቸው ነገር እግዚአብሔር ከአማልክት ሁሉ እንዲበልጥ አሁን አወቅሁ አለ።
የሙሴ አማት ዮቶርም የሚቃጠል መሥዋዕትንና ሌላ መሥዋዕትን ለእግዚአብሔር ወሰደ በእግዚአብሔርም ፊት ከሙሴ አማት ጋር እንጀራ ሊበሉ አሮን የእስራኤልም ሽማግሌዎች ሁሉ መጡ።
እንዲህም ሆነ፤ በነጋው ሙሴ በሕዝቡ ሊፈርድ ተቀመጠ፤ ሕዝቡም በሙሴ ፊት ከጥዋት እስከ ማታ ድረስ ቆመው ነበር።
የሙሴም አማት በሕዝቡ ያደረገውን ሁሉ ባየ ጊዜ፦ ይህ በሕዝቡ የምታደርገው ምንድር ነው? ሕዝቡ ሁሉ ከጥዋት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ በዙሪያህ ቆመው ሳሉ አንተ ብቻህን ስለ ምን ተቀምጠሃል? አለው።
ሙሴም አማቱን፦ ሕዝቡ እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ወደ እኔ ይመጣሉ፤ ገርም ቢኖራቸው ወደ እኔ ይመጣሉ፥ በዚህና በዚያ ሰውም መካከል እፈርዳለሁ፥ የእግዚአብሔርንም ሥርዓትና ሕግ አስታውቃቸዋለሁ አለው።
የሙሴም አማት አለው፦ አንተ የምታደርገው ይህ ነገር መልካም አይደለም።
ይህ ነገር ይከብድብሃልና አንተ ከአንተም ጋር ያለው ሕዝብ ትደክማላችሁ፤ አንተ ብቻህን ልታደርገው አትችልም
አሁንም እመክርሃለሁና ቃሌን ስማ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር ይሆናል፤ አንተ በእግዚአብሔር ፊት ለሕዝቡ ሁን፥ ነገራቸውንም ወደ እግዚአብሔር አድርስ፤ ሥርዓቱንም ሕጉንም አስተምራቸው፥ የሚሄዱበትን መንገድ የሚያደርጉትንም ሥራ ሁሉ አሳያቸው።
አንተም ከሕዝቡ ሁሉ አዋቂዎችን፥ እግዚአብሔርን የሚፈሩትን፥ የታመኑ፥ የግፍንም ረብ የሚጠሉትን ሰዎች ምረጥ፤ ከእነርሱም የሺህ አለቆችን፥ የመቶ አለቆችን፥ የአምሳ አለቆችን፥ የአሥርም አለቆችን ሹምላቸው።
በሕዝቡ ላይ ሁልጊዜ ይፍረዱ፤ አውራውን ነገር ሁሉ ወደ አንተ ያምጡት፥ ታናሹንም ነገር ሁሉ እነርሱ ይፍረዱ፤ እነርሱም ከአንተ ጋር ሸክሙን ይሸከማሉ፥ ለአንተም ይቀልልሃል።
ይህንም ብታደርግ፥ እግዚአብሔር እንዲሁ ቢያዝዝህ፥ መቆም ይቻልሃል፥ ደግሞም ይህ ሕዝብ ሁሉ በሰላም ወደ ስፍራው ይደርሳል።
ሙሴም የአማቱን ቃል ሰማ፥ ያለውንም ሁሉ አደረገ።
ሙሴም ከእስራኤል ሁሉ አዋቂዎችን መረጠ፥ በሕዝቡም ላይ የሺህ አለቆች፥ የመቶም አለቆች፥ የአምሳም አለቆች፥ የአሥርም አለቆች አድርጎ ሾማቸው።
በሕዝቡም ላይ ሁልጊዜ ፈረዱ፤ የከበደባቸውንም ነገር ወደ ሙሴ አመጡ፥ ታናሹን ነገር ሁሉ ግን እነርሱ ፈረዱ።
ሙሴም አማቱን ሰደደው፤ እርሱም ወደ አገሩ ተመለሰ። (ዘጸ 18
ከላ የቀረበውን ታሪክ ስናጤነው፥ ሙሴ በታምራት እስራኤላውያንን ከግብፅ ካወጣ በኋላ፥ አማቱ ዮቶር የሚመክረውና  ምክሩንም ተግባራዊ የሚያደርግ ከሆነ፥ሙሴ አርባ ዓመት ሙሉ ከአማቱ ጋር የኖረው፥ ስለ እግዚአብሔር ሲያጠና እና ሥርዓተ አምልኮን ሲለማመድ ነበርለማለት ያስችላል።
ይህም እራኤላውያንን ከግብፅ ምድር ካወጣ በኋላ፥ ምክርና ትእዛዝ ሲያስተላልፍ፥ ሙሴም የአማቱን ትእዛዝ መቀበሉንና መፈጸሙን ያሳየናል።
 ኦባብ (የሙሴ አማች) ለእስራኤላውያን ነጻነት ያደረገው አስተዋጽዖ፥
ኦባብ፥ የሙሴ አማት፥ የዮተር ልጅ ነው። በሌላ አባባል፥ ኦባብ የሙሴ ሚስት፥ የሲፓራ፥ ወንድም ነው።ሙሴም የሚስቱን አባት የምድያማዊውን የራጉኤልን ልጅ ኦባብን። እግዚአብሔር ለእናንተ እሰጠዋለሁ ወዳለው ስፍራ እንሄዳለን፤ እግዚአብሔር ስለ እስራኤል መልካምን ነገር ተናግሮአልና አንተ ከእኛ ጋር ና፥ መልካምን እናደርግልሃለን አለው።” (ዘኁ 10 29)
እስራኤላውያን ከግብፅ ወጥተው፥ በኢትዮጵያ በሚዞሩበት ወቅት፤ በተለይም የቃል ኪዳኑን ታቦት ከተቀበሉ በኋላ፤ አብሯቸው ይጓዝ ነበር። መንገዱንም አጣርቶ ያውቅ ስለነበር፥ እየቀደመ የታቦቱን ማረፊያ ያመቻችላቸው ነበር። ሙሴም ኦባብ ወደ ከነዓን አብሯቸው እንዲሄድ ደጋግሞ ለምኖታል። ከእኛም ጋር ብትሄድ እግዚአብሔር ከሚያደርግልን መልካም ነገር ሁሉ እኛ ለአንተ እናደርጋለን አለ።” (ዘኍ 10: 32)
ጥሩ ኑሮ ስለነበረው ይሆናል፥ አብሮአቸው ወደ ከነዓን ለመሔድ ፈቃደኛ አልሆነም።እርሱም፦ አልሄድም፥ ነገር ግን ወደ አገሬና ወደ ዘመዶቼ እሄዳለሁ አለው።” (ዘኍ 1030) እርሱም፦ እባክህ፥ በምድረ በዳ የምንሰፍርበትን አንተ ታውቃለህና፥ እንደ ዓይኖቻችንም ትሆንልናለህና አትተወን፤(ዘኍ 1031) ከእግዚአብሔርም ተራራ የሦስት ቀን መንገድ ያህል ተጓዙ፤ የእግዚአብሔርም የኪዳኑ ታቦት የሚያድርበትን ስፍራ ይፈልግላቸው ዘንድ የሦስት ቀን መንገድ ቀደማቸው።” (ዘኍ 10: 33)
የእግዚአብሔር ተራራ የሚባለው  በዚያን ዘመን የነበረው፥ በኢትዮጵያ ብቻ ነው። ጉዟቸው በኢትዮጵያ ምድር በመሆኑና መንገዱን በማወቁ ይመራቸው ነበር።
ሚስት ኢትዮጵያዊት መሆኗ ከታወቀ፥ ወንድሟም ኢትዮጵያዊ መሆኑ አያከራክርም። ኦባብ በእስራኤል የምድረ ባዕዳ ጉዞ አብሯቸው ነበር። መንገድም ይመራቸው ነበር። የእግዚአብሔር የኪዳኑ ታቦት የሚያርፍበት ስፍራ ይፈልግላቸው ነበር። ይህም የሚያሳየው፥  ኦባብ የነበሩበትን አገር መግቢያና መውጫ ጠንቅቆ ማወቁን፥ ለቃል ኪዳን ታቦት ተገቢውን ክብርና የሚመጥን ስፍራ ማወቁ ምን ያህል ሥርዓተ አምልኮን ከእስራኤላውያን የላቀ እውቀት እንደነበረው መገንዘብ ይቻላል።
ሙሴም ኦባብን፥ አብሮአቻው ወደ ከነዓን እንዲገባ ይጠይቀው ነበር። ኦባብ ግን አብሮ ለመሄድ ፈቃደኛ አልነበረም። ሙሴም የሚስቱን አባት የምድያማዊውን ራጉኤልን ልጅ ኦባብን፦ እግዚአብሔር፦ ለእናንተ እሰጠዋለሁ ወዳለው ስፍራ እንሄዳለን፤ እግዚአብሔር ስለ እስራኤል መልካምን ነገር ተናግሮአልና አንተ ከእኛ ጋር ና፥ መልካምን እናደርግልሃለን አለው።
በመጨረሻ ግን የኦባብ ልጆች ከነዓን እንደገቡ እንረዳለን። ይህም እስራኤላውያን ለአርባ ዓመት በኢትዮጵያ ከተዘዋወሩ በኋላ ከነዓን ሲገቡ፥ ብዙ ኢትዮጵያውያን አብረዋቸው እንደገቡ ያመለክተናል።ቄናዊውም ሔቤር ከሙሴ አማት ከኦባብ ልጆች ከቄናውያን ተለይቶ ድንኳኑን በቃዴስ አጠገብ በጻዕናይም እስከ ነበረው እስከ ትልቁ ዛፍ ድረስ ተከለ።” (መሣ 411)
በሌላ በኩልም፥ ብዙ እስራኤላውያን በዛሬዋ በኢትዮጵያ ኑሮ መስርተው እንደቀሩ እንረዳለን። ከግብፅ የወጡት በሙሉ በኢትዮጵያ አርጅተው፣ ሙተው ኢትዮጵያ ውስጥ ተቀብረው ሲቀሩ፤ ከነዓን የገቡት ደግሞ ሁሉም በኢትዮጵያ የተወለዱት ናቸው።
ከእግዚአብሔርም ተራራ የሦስት ቀን መንገድ ያህል ተጓዙ፤ የእግዚአብሔርም የኪዳኑ ታቦት የሚያድርበትን ስፍራ ይፈልግላቸው ዘንድ የሦስት ቀን መንገድ ቀደማቸው።(ዘኍ 10: 29-33) የእግዚአብሔር ተራራ የተባለው ኮሬብ በኢትዮጵያ  መሆኑን፥ በዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን የሚያውቅ ህዝብ የኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ነበር። ኦባብ የእግዚአብሔርን ታቦት እና  ቃልኪዳን የሚያውቅና የሚያከብር ስለነበር፥ ለታቦቱ ክብር የሚገባውን እና  የሚመጥነውን የሦስት ቀን መንገድ እየቀደመ ስፍራ ያመቻች ነበር።
 የሙሴ ፍጻሜ የሞተበት እና የተቀበረበት አገር፥
ሙሴ የሞተውና የተቀበረው፤ ወደ ቃል ኪዳኑ አገር ሳይገባ አፍሪካ ውስጥ፣ በምሥራቅ አፍሪካ፣ በኢትዮጵያ ነው።
ሙሴም ሞዓብ ሜዳ በኢያሪኮ ፊት ለፊት ወዳለው ወደ ናባው ተራራ ወደ ፈስጋ ራስ ወጣ፤ እግዚአብሔርም እስከዳን ድረስ ያለውን የገለዓድን ምድር...” (ዘዳ 34: 1)
ከጥቅሱ እንደምንረዳው፥ ሞዓብ እና ኢያሪኮ፥ በከነዓን አገር የቦታ መጠሪያዎች ከመሆናቸው በፊት፥ በምሥራቅ አፍሪካ  የነበሩ ቦታዎች ስያሜዎች፥ የነበሩ መሆናቸውን ነው። ለዚህም ማስረጃ  የሚሆነን፥ ናባው ሙሴ  የሞተበት ቦታ ሲሆን፥ ሙሴ ወደ ቃል ኪዳኑ አገር እንዳልገባ፥ በግልጽ ተመዝግቦ  ይገኛል።
ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ዕብራውያን በላከው ደብዳቤ፥እነዚህ ሁሉ አምነው ሞቱ፥ የተሰጣቸውን የተስፋ ቃል አላገኙምና ዳሩ ግን ከሩቅ ሆነው አዩትና ተሳለሙት፥ በምድሪቱም እንግዶችና መጻተኞች እንዲሆኑ ታመኑ።” (ዕብ 1113)
ይህ የሚያስገነዝበን፥ የቀደሙ አባቶች፥ አብርሃም፣ ይስሐቅ፣ ያቆብ፣ ዮሴፍ እና ሙሴ ወደ ቃል ኪዳን አገራቸው ወደ ከነዓን እንንዳልገቡ ነው። ይህ ከሆነ፥ ከግብፅ ከወጡና ከነዓን ካልገቡ፥ የት ኖሩ፣ የት ሞቱ፣ የትስ ተቀበሩ
ዮሴፍም፦ እግዚአብሔር ሳይጎበኛችሁ አይቀርም፥ አጥንቶቼንም ከዚህ ከእናንተ ጋር ታወጣላችሁ ብሎ የእስራኤልን ልጆች አምሎአቸው ነበርና ሙሴ የእርሱን አጥንቶች ከእርሱ ጋር ወሰደ።” (ዘጸ 13: 19) ከአራት መቶ ዓመት በፊት የሞተውን የዮሴፍን አጽም ከግብፅ ይዘውት ወጥተው፥ የት ቀበሩት? መልሱ አሁንም ኢትዮጵያ ነው።
ይህን ተራራ መዞር ይበቃችኋል ተመልሳችሁ ወደ ሰሜን ሂዱ።(ዘዳ 23) ከግብፅ ወጥተው የሄዱት ወደ ደቡብ መሆኑን ነው።
ይህ ተራራ የተባለው፥ የቱ ነው? መልሱ የሲናን ተራራ ነው።
ሴይርን ተራራ ዔሳው ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ እኔ ከምድራቸው የጫማ መርገጫ ታህል እንኳ አልሰጣችሁምና አትጣሉአቸው።” (ዘዳ 2: 5)
ርስት የተባለው የሴይር ተራራ የሚገኘው በኢትዮጵያ ነው። ዔሳው፥ በኢትዮጵያ ተውልዶ፣ በኢትዮጵያ አድጎ፣ በኢትዮጵያ አግብቶና ወልዶ፥ የኤዶማውያንን ነገድ መስርቶ ያለፈው፥ በኢትዮጵያ መሆኑ የታወቀ ነው።
ሴፍ የተቀበረው፥ እስራኤላውያን ከግብፅ ወጥተው ከነዓን ሳይገቡ መሆኑ የሚጠቁመን በኢትዮጵያ መሆኑን ነው።
 
 
ምዕራፍ ሦስት
 ጌታ ኢየሱስ በኢትዮጵያ፥
 በዚህ ምድር ከኖረበት ሠላሳ ሦስት ዓመት ውስጥ፥ ከሃያ ዓመት በላይ የሚሆነውን እድሜ የኖረው፥ በዛሬዋ የኢትዮጵያ ምድር ነው።
የተወለደው፥ በቤተልሔም ይሁዳ፥ በእስራኤል አገር ነው።
ሁለት ዓመት ሳይሞላው፥ ከእናቱ ጋር በሽሽት ወደ ኢትዮጵያ መጣ። የተወሰኑ ዓመታት በኢትዮጵያ ከቆየ ብኋላ፥ ከእናቱ ጋር ወደ እስራኤል ተመለሰ።
የአሥራ ሁለት ዓመት እድሜ ሲሆነው ብቻውን፥ ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ ሠላሳ ዓመት እስኪሆነው፥ ለአሥራ ስምንት አመት በኢትዮጵያ ኖረ።
ወንጌላውያን ጌታ ከአሥራ ሁለት ዓመት እድሜው እስከ ሠላሳ የኖረውን ያልመዘገቡት፥ እነርሱ በእስራኤል እንጅ ከጌታ ጋር በኢትዮጵያ ስላልነበሩ ነው።
ከእናቱ ጋር በሽሽት፥ ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸውም፥ ወደ አገሯ እና ወደ ዘመዶቿ  መሸሽ ስለነበረባት፤ የመቤታችን የትውልድ ሐረግም ኢትዮጵያዊ እንጅ እስራኤላዊት ስላልሆነ ነው።
ኢትዮጵያ አገረ እግዚአብሔር በመሆኗ፥ የሚሸሸው ወደ እግዚአብሔር እንጅ፥ ወደሌላ ወደየትም ስላልሆነም ነው።
አባቴ ቤት ብዙ ስፍራ አለእያለ የገለጸው፥ ቤተ አብ፣ ቤተ እግዚአብሔር... የሚገኘው በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያውያን ዘንድ ብቻ ነው። በሌላ አገር ያለው፥ ቤተ ጸሎት፣ ቤተ አምልኮ፣ ቤተ መቅደስ... ነው።
ዛሬም፥ ቤተ ክርስቲያን የሚባል ህንጻ ያለው፥ በኢትዮጵያ እንጅ በሌላ አገር አይደለም።
በመዋእለ ትምህርቱ የኢትዮጵያውያንን ቃላት መጠቀሙ ይህነኑ በኢትዮጵያ መኖሩን ያስረዳል።
እራሱንየሰው ልጅእያለ የሚጠራበት ዋናው ምክንያት እስራኤላዊ አለመሆኑን፥ እንዲያውም ኢትዮጵያዊ መሆኑን ለመጠቆም ነው።
የስሙ ምንጭ እና ፍች ኢትዮጵያዊ እንጅ እስራኤላዊ አያደርገውም።
አፉን የፈታበት ቋንቋ፥ የኢትዮጵያውያን ሲሆን፤ ያስተምር የነበረውም በዚሁ ቋንቋ ነበር። (ማር 541 እና 734)
·       እየሱስ ማን ነው
·       የተሰደደውስ ወዴት ነው
·       የተማረው እና የኖረውስ የት ነው
 ኢየሱስ ማን ነው? የሰውን ልጅ
ትውልዱስ ከየት ነው?
ኢየሱስም ወደ ፊልጶስ ቂሣርያ አገር በደረሰ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን፦ ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደ ሆነ ይሉታል? ብሎ ጠየቀ።” (ማቴ 1613) ይህን ጥያቄ ያቀረበው፤ ጌታ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ነው። የጠየቃቸውም፥ እስራኤላውያን ስለራሱ፥ ስለኢየሱስ ማንነት ያለቸውን ግንዛቤ ለማጤን ነው። ከዚህ ጥቅስ የምንማረው፥ እኛም ዛሬ፥ ደጋግመን እንድንጠይቅና የኢየሱስን ማንነት በትክክል እንድንረዳ ያደርገናል።
ይህን ጥያቄ ሲያቀርብለቸው ለመጀመሪያ ጊዜም አልነበረም።ፈሪሳውያንም ተሰብስበው ሳሉ፥ ኢየሱስ፦ ስለ ክርስቶስ ምን ይመስላችኋል? የማንስ ልጅ ነው? ብሎ ጠየቃቸው። የዳዊት ልጅ ነው አሉት። እርሱም፦ እንኪያስ ዳዊት፦ ጌታ ጌታዬን፦ ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው ሲል እንዴት በመንፈስ ጌታ ብሎ ይጠራዋል? ዳዊትስ ጌታ ብሎ ከጠራው፥ እንዴት ልጁ ይሆናል? አላቸው።” (ሉቃ 2041- 45) ፈሪሳውያን ይህን የመለሱ፥ አንድም አባቱ ዮሴፍ መስሏቸው ነው። አንድም ደግሞ ማንም ሰው የዳዊት ልጅ ተብሎ መጠራትን እንደሚፈልግ ስለሚያውቁና ከዚያ የበለጠ ክብር መኖሩን ስላልተረዱ ነው። እውነታው ደግሞ፤ የንጉሥ ዳዊት ልጅ ከመሆን፤ የእግዚአብሔር ልጅ መሆን በእጅጉ የላቀ በመሆኑ ነው። ከሰጣቸው መልስ የምንረዳው፥ የንጉሥ ዳዊት ልጅ አለመሆኑን ወይም የዳዊት ልጅ ተብሎ መጠራትን እንደማይቀበል ነው።
በሌላም ቦታ፥አንተ ማነህ? ብለው በጠየቁት ጊዜ ሲመልስላቸው፥ኢየሱስም መለሰ አለም፦ እኔ ራሴን ባከብር ክብሬ ከንቱ ነው፤ የሚያከብረኝ እናንተ አምላካች የምትሉት አባቴ ነው” (ዮሐ 854) እዚህ ላይ፥ እኛ የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ለምንል ኢትዮጵያውያ እና ለሌሎችም ክርስቲያኖች ጭምር፥ የእስራኤላውያን አምላክ፥ ለኛ ደግሞ አባታችን፥ በመሆኑ፥ ምን ያህል ለእግዚአብሔር የቀርብን መሆናችንን ማሳያ ነው።
            ለምንስ የትውልድ ሐረጉ፥ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልቀረበም? ተብሎ ለቀረበ ጥያቄ ምላሹ፥አባትና እናት ትውልድም ቍጥር የሉትም ለዘመኑም ጥንት ለህይወቱም ፍጻሜ የለውም፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ልጅ ተመስሎ ለዘላለም ካህን ሆኖ ይኖራል።” (ዕብ 7: 3) ቅዱስ ጳውሎስ እንዳስቀመጠው፤ ጌታ ኢየሱስን እና መልከ ጼዴቅን፥ የሚያመሳስላቸው ብዙ ነገሮች መኖራቸውን ነው። ከነዚህም ውስጥ አንዱ፥ ዘላለማዊ ክህነታቸው ነው። የሁለቱም ክህነት፥ ከአሮን እና ከሌዊ ያይደለ፥ ቀዳሚነት ያለውና ፍጻሜ የሌለው መሆኑ እንጅ። ሌላ ሁለቱን የሚያመሳስላቸው፥ የትውልድ ሐረጋቸው፥ በእስራኤላውያን የትውልድ ቁጥር መጽሐፍ ተመዝግቦ አለመገኘቱ ነው። የመልከ ጼዴቅን የትውልድ ሐረግን ፈልጎ ማግኘት፥ የጌታ ኢየሱስንም የትውልድ ሐረግ ለማግኘት ይረዳል። በቅዱስ ማቴዎስና በቅዱስ ሉቃስ መጽሐፍት ተዘርዝረው የቀረቡት የትውልድ ሐረጋት፥ የዮሴፍን የትውልድ ሐረግ የሚያሳይ እንጅ፥ የመቤታችንን ወይም የጌታን የትውልድ ሐረግ የሚያሳይ አይደለም። ቅዱስ ማቴዎስ፥ የዮሴፍን የትውልድ ሐረግ ባቀረበበት በምዕራፍ አንድ መጨረሻ ‘... ሳይገናኙ ከመንፈስ ቅዱስ ጸንሳ ተገኘች  በማለት፥ የጌታ የትውልድ ሐረግ አለመሆኑን በግልጽ አስቀምጦታል። ቅዱስ ሉቃስም ዝርዝሩን ሲጀምር፥ አይሁድን፥እንደመሰላቸው፥ የዮሴፍ ልጅ ሁኖ፥ የኤሊ ልጅ ሁኖ...” ይላል። ይህም ማለት፥አይሁድ የመሰላቸው እንጅ፥ እርግጠኛ የጌታ የትውልድ ሐርግ አይደለም እያለን ነው።
            የማቴዎስን ምእራፍ አንድን እና የሉቃስን ወንጌላት ምእራፍ ሃያ ሦስትን፥ በግልቡ እያየን፥ የጌታ የትውልድ ሐረግ ነው፥ ብለን የምንወስድ ከሆነ ብዙ የማያስሄዱ ጉዳዮች አሉ።
ለምሳሌ ያህል፥ በማቴዎስ ወንጌል ያለው የዮሴፍ፥ አባትያዕቆብይላል፥ያዕቆብ ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን የወለደች የማርያምን እጮኛ ዮሴፍን ወለደ (ማቴ 1 16) በሉቃስ ወንጌል ያለው የትውልድ ሐረግ ዝርዝር ላይ ያለው ደግሞ የዮሴፍን አባትኤሊይለዋል፥ኢየሱስም ሊያስተምር ሲጀምር ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ያህል ሆኖት ነበር እንደመሰላቸው ዮሴፍ ልጅ ሆኖ፥ ኤሊ ልጅ...” (ሉቃ 321) ዮሴፍ እንዴት ሁለት አባቶች ይኖሩታል። ታዲያ የትኛው ትክክል ነው? ሁለቱስ እንዴት ትክክል ይሆናሉ። ሌላው ደግሞ፥ በማቴዎስ ወንጌል የቀረበው የትውልድ ሐረግ ዝርዝር በዳዊት ልጅ፥ በሰሎሞን ይቀጥላል፥እሴይም ንጉሥ ዳዊትን ወለደ። ንጉሥ ዳዊት ከኦርዮ ሚስት ሰሎሞንን ወለደ፤ ሰሎሞንም ሮብዓምን ወለደ፤ ሮብዓምም አቢያን ወለደ...” (ማቴ16 እና 7)  በሉቃስ ወንጌል የቀረበው የትውልድ ሐረግ፥ በንጉስ ዳዊት ልጅ፥ በናታን ይቀጥላል፥ “...የማጣት ልጅ፥ ናታን ልጅ ዳዊት ልጅ የእሴይ ልጅ፥ (ሉቃ 331 እና 32) ታዲያ የትኛው የትውልድ ሐረግ ዝርዝር ትክክል ነው? ሁለቱስ እንዴት ትክክል ሊሆኑ ይችላሉ? መልሱ፥ የትውልድ ሐረጉ ከቀረቡት ዝርዝሮች ውጭ የሆነ፥ እንደ መልከጼዴቅ፥ የትውልድ ሐረጉ (የእናቱ፥ አባቱ ሰማያዊ ስለሆነ) በመጽሐፍ ያልተጻፈ መሆኑ ነው።
            በመጽሐፍ ቅዱስ፥ እስራኤላዊ ባለመሆናቸው፥ የትውልድ ሐረጋቸው ካልተጠቀሱ ሰዎች ውስጥ፡ በአዜብ (ኢትዮጵያ) የጌራራ ንጉሥ አቤሜሌክ፤ ኤርሚያስን ከጉድጓድ ያወጣው፥ ኢትዮጵያዊው አቤሜሌክ፤ የናዖሚን ባል አቢሜሌክ፤ ካህኑ ዮቶር፤ የአብርሃም ሚስት ኬጡራና ስድስቱ ልጆቻቸው፤ ሞባዊቷ ሩት፣ ንግሥተ ሳባ/ ንግሥተ አዜብ፣ ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ... እመቤታችን ድንግል ማርያም...
ኢየሱስ፥ የመቤታችን የቅድስት ድንግል ማሪያም የበኩር ልጅ ነው። የመጀመሪያ ልጇ ብቻ ሳይሆን የመጨረሻ ልጅም ስለሆነ፤ ይህም፥ የመጀመሪይና የመጨረሻ፤  አልፋና ዖሜጋ የሚለውን መጠሪያውን አስገኝቶለታል። የእናቱ የበኩር ልጅ በመሆኑ፤ ለአባቱም የበኩር ልጅ ተባለ። ይህም፥ አብርሃም ከይስሐቅ በፊት ልጅ ቢኖረውም፤ ይስሐቅ የአብርሃም የበኩር ልጅ ተብሏል። እንዲያውም፥አንድ ልጅህን...’ ተብሏል። አንድ ልጅነቱም፥ በእናቱ በሳራ በኩል እንጅ፤ ለአባቱ ለአብርሃምም ሌሎችም ልጆች አሉት።
ምንም እንኳን፥ ከክርስቶስ መወለድ በፊትም፥ የእግዚአብሔር ልጆች ተብለው፥ በቅዱስ መጽሐፍ የተጠሩ፥ ቢኖሩም፤ ጌታ ኢየሱስ ለእናቱ የበኩር ልጅ በመሆኑ፥ ለአባቱ ለአብርም የበኩር ልጅ ይባላል።
·       እኔ ከአብርሃም በፊት ነበርሁ....”
·       ጌታ ጌታዬን ጠላቶችህን የእግርህ መርገጫ እስካደርግ ድረስ በቀኘ ተቀመጥ አለው። ዳዊት ጌታዬ ካለኝ እንዴት ልጁ እሆናለሁ?”
እነዚህን ጥቅሶች ስንመረምር... የኢየሱስ የትውልድ ሐረግ ጥያቄ ያስነሳ እንደነበር እንገነዘባለን...
የጌታ ኢየሱስን መልሶች ስናጤን ደግሞ... እስራኤላዊ አለመሆኑን ሊያሳያቸው የሚያደርገውን አካሄድ እንገነዘባለን...
የሰው ልጅ ማለት ምን ማለት ነው? የማርያም፣ የኤልሳቤጥ... የትውልድ ሐረግ፤ ሰብዓ ሰገል... አገራቸው...?
ሱስ የስሙ ትርጉም፥ ምንድነው?
ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።” (ማቴ 121)
ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና...’ የሚለውን ገለጻ ስናይ፤ ኢየሱስ ማለት፥ከኃጢያት የሚያድን የሚል አውዳዊ ፍችን እናገኛለን።ሕዝብንማለት ደግሞ የአዳምን ዘር በሙሉ ማለት ነው። ሕዝብ ለማዳን፥ አዳምን ማዳን፥ ደግሞ በአዳም የሚተካና የአዳምን ኃጢያት የሚሸከም ሰው ያስፈልጋል። ስለዚህ፥ ኢየሱስ የአዳምን ኃጢያት ሲወስድ፥ ለአዳም ቤዛ፣ ምትክ፣ ዋስ... ሁኖ አዳነ እንላለን። አዳምን ማዳን ደግሞ ሕዝበ አዳምን ማዳን ነው።
ኢየሱስ ብሎ ስም ያወጣለት፤ ዮሴፍ ነው። እናቱ ደግሞ አማኑኤል አለችው። ስሙ የጎላው የእናቱ ቢሆን ኑሮ፥ ኢየሱስ፥ የሚለው ሳይሆን፥ አማኑኤል በሚለው ይጠራ ነበር። ማለትም፥ኢየሱስ ክርስቶስበሚለው ፋንታ፤አማኑኤል ክርስቶስይሆን ነበር ማለት ነው።
ኢየሱስማለት አዳኝ ማለት ነው። የስሙ ምንጭ ወይም ስርዎ ቃል፥የሺሕ...’ እናዋስ የሚሉት ሁለት ቃላት ናቸው። አዳኝ የሚለውን ፍች የመጣው፥ዋስከሚለው ስም፥ ስለተወሰደ ነው። አዳም በሐጢያቱ ምክንያት፥ በዘላለማዊ ባርነት፣ በማይቀር የሞት ፍርድ፣ በዳቢሎስ ግዛት በግዞትና በእስራት ሲኖር፥ ጌታ ኢየሱስ በዋስነት ነጻ አወጣው። ሰው ስለሆነ ስለ ሰው፥ ስለ አዳም ሞተ፥ አምላክ ስለሆነ ተነሳ...
            የሰው ልጅማለት ሰው ከሚለው ፍች በተጨማሪ፤ የሌላ ሰው ልጅ የሚል ትርጓሜ  አለው። ይህም፥ የሰው ገንዘብ፣ የሰው አገር፣ የሰው ቤት፣ የሰው፣ አጥር፣ የሰው መኪና... የራስ ያልሆነን ነገር ሁሉ መግለጫ ቋንቋ ነው። ጌታ ኢየሱስ፥ በእየሩሳሌምየሰው ልጅእያለ ራሱን መጥራቱ፥ እስራኤላዊ አለመሆኑን እና የሌላ አገር ሰው መሆኑን ለመግለጥ ነው።
            የሰው ልጅበሌላው ፍች፥ ወልደ ዕጓለ መሕያው ማለት ሁኖ፥ የእግዚአብሔር ልጅ ማለት ይሆናል።
የሰው ልጅማለት ቤርሳባ ወይም ቤተሳባ ማለት ሁኖ፥የሳባ ልጅየሚል ትርጓሜን ይይዛል።ሳባማለት ሰው ማለት ነውና። ይህም ሳባዊ፣ የሳባ ልጅ፣ የሳባ ነገድ፣ ቤተ ሳባ፣ ቤተ ሰብ፣ ሳባ ቤት፣ ኢትዮጵያዊ ... የሚሉ አንድምታዎችን የያዘ  ነው።
ኤልሳቤትየሚለው ስም ፍች፥ የአምላክ ቤተሰብ የሚል ነው። ቤተሰብ ማለት እናት፣ አባት እና ልጅ ሲሆን፥ ቤርሳባ እና ኤልሳቤት() የሚሉ ስሞች፥ የእግዚአብሔር ቤተሰብ፥ የሚል ፍችን የያዙ ናቸው። ስለዚህ ኤልሳቤጥ እና ቤርሳባ የሚባሉ ስሞች፥ የእግዚአብሔር ልጅ፣ ማለትና፥ ኢትዮጵያአገረ እግዚአብሔርስለሆነች፥ ኢትዮጵያውያን ማለትም ነው።
የመጥምቁ ዮሐንስ እናት፥ ኤልሳቤት፥ ኢትዮጵያዊ ከሆነችና፥ የመቤታችን አክስት ከሆነች፥ እመቤታችንም ኢትዮጵያዊት ልትሆን ትችላለች ብሎ ማሰብ አይከብድም።
ከዚህ በታች የቀረቡ ጥቅሶች፥ የጌታ ኢየሱስን ኢትዮጵያዊነት የሚጠቁሙ ናቸው፥
1.       በይሁዳ ንጉሥ በሄሮድስ ዘመን ከአብያ ክፍል የሆነ ዘካርያስ የሚባል አንድ ካህን ነበረ፤ ሚስቱም ከአሮን ልጆች ነበረች፥ ስምዋም ኤልሳቤጥ ነበረ።(ሉቃ 15) ከአሮን ወገን የተባለችው፥ የሙሴ ወንድም፥ የካህኑ የአሮን፤ ሚስት ስም ኤልሳቤጥ በመሆኑ ነው። አሮንም የአሚናዳብን የነአሶንን እኅት ኤልሳቤጥ አገባ፥ እርስዋም ናዳብንና አብዮድን አልዓዛርንና ኢታምርን ወለደችለት።(ዘጸ 623) ኤልሳቤጥ የሚለው ስም ፍች፥ የኢትዮጵያዊነት እና ኢትዮጵያዊ መሆኗን ነው፥ ሲብራራም ኤል ሰባት፥ ሰባት የኢትዮጵያ ልዩ ስም መሆኑን የምንገነዘበው ስርዎ ቃሉ፥ ሳባ ቤት በመሆኑ ነው። ኤልሳቤጥ የማርያም አክስትና ኢትዮጵያዊት ወገን ካላት፥ ማርያምም የኢትዮጵያ የትውልድ ሐርግ አላት ማለት አያስቸግርም። ከአሮን ልጆች የሚለው የመጣው የሙሴ  ወንድም፥ አሮን ያገባው ኤልሳቤጥ የምትባል ኢትየጵያዊት ስለነበረ ነው።
2.      አባትና እናት የትውልድም ቍጥር የሉትም፥ ለዘመኑም ጥንት ለህይወቱም ፍጻሜ የለውም፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ልጅ ተመስሎ ለዘላለም ካህን ሆኖ ይኖራል።” (ዕብ 7: 3) አባትና እናት የትውልድም ቁጥር የሉትም፥ ማለት የትውልድ ሐረጉ፥ ከእስራኤል  አይደለም፥ ማለት ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ፥ እንደ አቤሜሌክና ሌሎች ታዋቂ ሰዎች፥ የትውልድ ሐረጋቸው ያልተጠቀሰው ኢትዮጵያውያን ስለሆኑ ነው።
3.      ኢየሱስም በይሁዳ ቤተ ልሔም በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰብአ ሰገል፦ የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና እያሉ ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።” (ማቴ 2: 1-2) ዚህ ጥቅስ የምንገነዘበው፥ ብአ የሚለው ቃል ሳባውያን መሆናቸውን ይጠቁማል።
በዚያን ዘመን፥ ስለ እስራኤል አምላክ እውቀት የነበራቸው ነገሥታትም ሆነ ህዝብ፥ የኢትዮጵያ ብቻ ነበር፥ ስለዚህ ሰብአ ሰገል የሄዱት ሁሉም ከኢትዮጵያ መሆናቸውን እንገነዘባለን።
የመቤታችንን ከልጇ ጋር ከግብፅ ወደ ኢትዮጵያ መሰደድን ከሰብአ ሰገል ጋር ማያያዝ ይቻላል፥ ከአገረ እግዚአብሔር፥ ከአባቱ የተላኩ ስለሆኑ...
4.     ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፥ ወድቀውም ሰገዱለት፥ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት።” (ማቴ 2: 11) “... ዓረብና የሳባ ነገሥታት እጅ መንሻን ያቀርባሉ። (መዝ 72 : 9-11) የተባለውም ያንጊዜ ተፈጸመ። ጌታ በተወለደበት ዘመን፥ በወርቅ፣ በዕጣንና በከርቤ የምትታወቀው አገር፥ ኢትዮጵያ፥ እንደነበረች ይታወቃል።
5.     የአሥራ ሁለት ዓመት ልጅ በሆነ ጊዜ፥ እንደ በዓሉ ሥርዓት ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ፤” (ሉቃ 2: 42)
6.     ኢየሱስም ሊያስተምር ሲጀምር ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ያህል ሆኖት ነበር እንደመሰላቸው የዮሴፍ ልጅ ሆኖ፥ የኤሊ ልጅ፥” (ሉቃ 3: 23) ቅዱስ ሉቃስ፥ የጌታን የትውልድ ሐረግ መቁጠር ሲጀምር፥እንደመሰላቸው ብሎ  ነው። ከዚህ አባባሉ የምንረዳው፥ መሰላቸው እንጅ፥ አይደለም ማለት ነው። ጌታ ኢየሱስ አይሁድ፥ ሳምራውያን ነው ሲሉ፤ ሳምራውያን ደግሞ፥ አይሁድ ይመስላቸው ነበር።ስለዚህ ሳምራዊቲቱ፦ አንተ የይሁዳ ሰው ስትሆን ሳምራዊት ሴት ከምሆን ከእኔ መጠጥ እንዴት ትለምናለህ? አለችው፤ አይሁድ ከሳምራውያን ጋር አይተባበሩም ነበርና።” (ዮሐ49) በሌላ በኩል ደግሞ፥ አይሁድ ሳምራዊ ይመስላቸው ነበር፥አይሁድ መልሰው፦ ሳምራዊ እንደ ሆንህ ጋኔንም እንዳለብህ በማለታችን እኛ መልካም እንል የለምን? አሉት።” (ዮሐ 848)
7.      ኢየሱስም ወደ ፊልጶስ ቂሣርያ አገር በደረሰ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን፦ ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደ ሆነ ይሉታል? ብሎ ጠየቀ።” (ማቴ 16: 13) ጌታ እራሱን የሰው ልጅ እያለ ይጠራ እንደ ነበር፥ የሰው ልጅ ማለትና ሰው ማለት አንድ እንዳልሆነ፥ ሁለቱ መጠሪያዎች በአንድ ዓርፍተ ነገር በመቅረቡ፥ በፍች የተለያዩ እንደሆኑ እንድንገነዘብ ያደርገናል።ሰውማለት የታወቀ ትርጉም አለው።የሰው ልጅማለትስ ምን ማለት ነው? የሰው ልጅ ማለት ዋናው ፍች፥ የራስ ያልሆነ፥ የሌላ  ሰው ልጅ፥ ማለት ነው። ይህም በአገራችን ቋንቋ አጠቃቀም፥ የሰው አገር፣ የሰው ገንዘብ፣ የሰው ቤት...እንደማለት ነው። በዚህም የእስራኤላውያን ወገን እንዳልሆነ መረዳት እንችላለን።
 የጌታን የትውልድ ሐርግ፥ ከእስራኤላዊነት ይልቅ ኢትዮጵያዊ የሚያሰኘው፤ የመሰረተው እና የፈጸመው ሥርዓተ አምልኮ ነው። ይህም ግርዘት እና ጥምቀት ነው። የጌታን መጠመቅ ለየት የሚያደርገው፥ የተገረዘም የተጠመቀም መሆኑ ነው። ይህ ዓይነት ስርዓት ያለው ደግሞ በኢትዮጵያውያን ብቻ ነው። ምን አልባትም፥ እንደጌታ የተገረዘም የተጠመቀም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሰው ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ ይሆናል። ሌሎች የተገረዙት፥ ጌታን ስላልተቀበሉ አልተጠመቁም፤ የተጠመቁት ደግሞ፥ አሕዛብ ስለነበሩ ግርዘትን አላገኙም።
 ሰብዓ ሰገል፥ የምሥራቅ አገር (የኢትዮጵያ) የጥበብ ሰዎች፥
ኢየሱስም በይሁዳ ቤተ ልሔም በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰብዓ ሰገል የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና እያሉ ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ” (ማቴ21 እና 2)
            በዚህ ምዕራፍና ቁጥር፥ምሥራቅተብሎ የተጠቀሰው አገር ኢትዮጵያን ነው። ኢትዮጵያን ምሥራቅ አድርገን፥ ከቀይ ባሕር ማዶ ያሉትን አገራት መካከለኛው ምሥራቅ ብለን፤ ከዚያ የሚርቁ አገራትን ደግሞ እሩቅ ምሥራቅ እንላለን። ብዙውን ጊዜ፥ ስለ መካከለኛው ምሥራቅ እና ስለ እሩቅ ምሥራቅ እንሰማለን፤ ስለምሥራቅግን አይወራም። ይህም የሆነበት ምክንያት፥ የኢትዮጵያን ታሪክ የማግለልና የመሰወር ድርጊት ነው።
በዚያን ዘመን የእግዚአብሔርን መንግሥት የሚያውቁና የመሲሁን መምጣት የሚጠብቁ አገራት ኢትዮጵያና እስራኤል ብቻ ነበሩ። ከመጡት ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም ከሆነ፥ ሊመጡ የሚችሉት ከኢትዮጵያ እንጅ ከሌላ ከየትም ሊሆን አይችልም።
ሰብዓ ሰገልማለት የጥበብ ሰዎች ማለት ነው።ሰብዓሰው ማለት ነው። ሌላው ሰብዓ የሚለው ስም ፍችሳባማለትም ነው። ስለዚህሰብዓየሚለው ስም ሳባዊነታቸውን፥ ማለትም ኢትዮጵያዊነታቸውን ይጠቁማል።
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች ያለው ቅዱስ ዳዊት፥ አንድም ይህን ሰብዓ ሰገል፥ ለእግዚአብሔር ወልድ፥ ስጦታን ለመስጠት መዘርጋታቸውን ነው።እጅ መዘርጋትአንድም ለመስጠት፥ አንድም ደግሞ ለመቀበል ነውና።
ስለዚህ፥ የጌታን መወለድ ጠብቀው ለህጻኑ ስጦታን ለመስጠት የሚመጡ ኢትዮጵያውያን እንጅ የሌላ አገር ህዝብና መንግሥት ሊሆን አይችልም።
ከዚህ በመነሳትሰብዓ ሰገል የመጡት ከኢትዮጵያ ነው!’ ከማለት ውጭ፥ ሌላ ታሪክ እና ማስርጃ አይኖርም።
 ሽሽት በግብፅ (ወደ ኢትዮጵያ) የተሰደደው ወዴት ነው?
ጌታ ኢየሱስ፥ በህፃንነቱ፥ ከእናቱ ከድንግል ማርያም እና ከዮሴፍ ጋር፥ ከቤተልሔም ተሰዶ የሄደው ወደ ኢትዮጵያ ነው።
እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ፥እነርሱም ከሄዱ በኋላ እነሆ፥ የጌታ መልአክ በሕልም ለዮሴፍ ታይቶ፦ ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይፈልገዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑንና እናቱንም ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ፥ እስክነግርህም ድረስ በዚያ ተቀመጥ አለው።” (ማቴ 213)
ከላይ፥ ከጥቅሱ የምንገነዘበው፥እነሱ ከሄዱ ብኋላየተባሉት፥ ሰብዓ ሰገልን ነው። ስለሆነም፥ የእመቤታችን ከልጇ ጋር ያደረጉት ሽሽት፥ ከሰብዓ ሰገል ጋር የሚያይዘው ነገር እንዳለ እንገምታለን። ምን አልባትም ሽሽታቸው፥ ሰብዓ ሰገል ወደ መጡበት፥ ወደ ምሥራቅ አገር ይሆናል። ምሥራቅ አገር ደግሞ ግብፅ እንዳልሆነች አያከራክርም። ግብጻውያን እንዲያውም በዚያን ዘመን የጥጃን ጣዖት የሚያመልኩ፤ እግዚያብሔርን የማያውቁ ሰዎች ነበሩ። እንኳንስ ቅዱሳን በሽሽት የሚሄዱባት፥ ከዚያ እንዲወጣ ማሳሰቢያና ማስጠንቀቂያ የሚሰጥባት አገር ነበረች። ታዲያ ለምን ወደ ግብፅ ሸሹ ካልን፥ በግብፅ አድርገው የሚሄዱበትና፥ የሚሸሸጉበት ሌላ እግዚአብሔር ያዘጋጀላቸው ቦታ ስለነበረ ነው።
የጌታ መልአክ የተላከው፥ ከእግዚአብሔር መሆኑ የታወቀ ነው። እግዚአብሔር መልአክ ልኮ እግዚአብሔር በቤተልሔም አልነበረም ማለት ነው። በዚያ ቢኖርማ፥ ከእግዚአብሔር ወዴት ይሸሻል። ‘... ወደ ግብፅ ሽሽ...’ እግዚአብሔር በግብፅ አልነበረም ማለት ነው። በግብፅ ቢሆር ኖሮወደ ግብፅ ይል ነበር።እስክነግርህም በዚያ ተቀመጥማለት፥ ከግብፅ ወጥቶ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጣ፥  የሚሰጠውን ትእዛዝ፥ በግብፅ ሆኖ መጠበቅ፥ ማለት ነው።
ምናልባት፤ ትቂት ፍንጭ ይሰጡን እንደሆን፥ ቀጥለው የቀረቡትን ጥቅሶች እንመርምር።
እርሱም ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን በሌሊት ያዘና ከጌታ ዘንድ በነቢይ፦ ልጄን ከግብፅ ጠራሁት የተባለው እንዲፈጸም ወደ ግብፅ ሄደ፥ ሄሮድስም እስኪሞት ድረስ በዚያ ኖረ” (ማቴ 2: 14-15) መጥራት፥ የተጠራውን ወደ ጤሪ መሔድን ያሳያል። በዚህ ጥቅስ የምናየው፤ እግዚአብሔር አብ ልጁን እግዚአብሔር ወልድን፥ ውደሱ እንዲሄድ ሲጥራው ነው። ይህም የሚጥቁመን እግዚአብሔር አብ ኢትዮጵያ ሁኖ ከግብጽ ወደ ኢትዮጵያ እንደጠራው ነው።  ሽሽት ወደ እግዚአብሔር ነውና፥ ኢትዮጵያምአገረ እግዚአብሔርስለሆነች ሽሽቱ የሚያበቃው ኢትዮጵያ ሲደርሱ ነው።
እስራኤል ሕፃን በነበረ ጊዜ ወደድሁት፥ ልጄንም ከግብፅ ጠራሁት” (ሆሴ 11: 1) ይህ ትንቢት የተነገረው፥ እስራኤላውያን ከግብፅ ባርነት ወጥተው፥ ከነዓን ከገቡ ከስምንት መቶ ዓመት በኋላ ነው። ትንቢቱም ፍጻሜን ያገኘው፥ ጌታ ከግብፅ ወደ ኢትዮጵያ ባረገው ሽሽት ነው። ይህን ሽሽት ቅዱስ ዳዊት፥ ከድርጊቱ አንድ ሺህ ዓመት አስቀድሞ ተናግሮታል፥ እንዲህ በማለት፥መኳንንት ከግብፅ ይመጣሉ ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።” (መዝ 68: 31)ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።የሚለውም ትንቢት ፍጻሜን ያገኘው፥ እግዚአብሔር ወልድ፥ ከግብፅ ወጥቶ፥ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣና፥ ኢትዮጵያምእጆቿን ዘርግታእግዚአብሔር ወልድን፣ ስትቀበለው ነው።
ሽሽት የሚደረገው፤ ፍጹም ደህንነት ወደሚገኝበት ወደ ጽዮን ነው። ጽዮን ማለት አምባ፣ መሸሻ፣ መሸሸጊያ፣ መጠጊያ፣ መመኪያ... ማለት ነው።
እስራኤል፣ ግብፅ እና ሌሎች የመካከለኛው ምሥራቅ አገራት በሮማን ቅኝ ግዛት በወደቁበት ዘመን፤ ወደ ነፃይቱ አገር ወደ ኢትዮጵያ ይሸሻል፤ እንጅ ወደ ሌላ የሮማ ቅኝ ግዛት አገር አይሸሽም።
በሮማውያን ቅኝ ግዛት ስር በነበረችው እስራኤል ውስጥ የነበሩ ወንጌላውያን፤ ከጽንሰቱ ጀምራው እስከ ግብፅ ስደት የነበረውን ታሪክ ሲመዘግቡ፤ ከግብፅ ቀጥለው ያደረጉትን ጉዞ፤ የኢትዮጵያ የነጻነት ግዛት ስለማይፈቅድላቸው፥ ሳይገቡና ሳይመዘግቡት አልፈውታል።
በእርግጥ ጌታ ኢየሱስ እና እናቱ፥ በግብፅ አድርገው የሸሹት ወደ ኢትዮጵያ ነው። ከእስራኤል ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት፤ በግብፅ ውስጥ ማለፍ የግድ ስለሆነ እንጅ። እስራኤልን ከግብጽ ያወጣ አምላክ፥ ልጁን በግብጽ እንዲያድግ ፈለገ፥ ብሎ ማሰብ አስተዋይነት የጎደለው ይሆናል።
ከዚያም በኢትዮጵያውያን ቋንቋአፋን ፈታ ይህንም፥ ከዚህ ቀጥሎ፥ኢየሱስ የተማረው የት ነው?’ በሚለው ርዕስ ሥር፥ በቂ ማብራሪያ ቀርቦበታል።
የሕፃኑን ነፍስ የፈለጉት ሞተዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑን እናቱንም ይዘህ ወደ እስራኤል አገር ሂድ፡አለ። (ማቴ 2 20)
ከትቂት ዓመታት በኋላ፥ ወደ ተወለደበት አገር ተመለሰ፥ ከዚያም አሥራ ሁለት ዓመት ገደማ ሲሆነው፥ ከቤተሰቦቹ ተለይቶ ወደ አደገበት አገር፥ ወደ ኢትዮጵያ መጣ። በኢትዮጵያ፥ ሰላሳ ዓመት እስኪሆነው ድረስ ኖረ። ይህንም፥ መጽሐፍ ቅዱስ የልተመዘገበው፤ ነብያቱ፣ ሐዋርያቱ፣ ወንጌላውያኑ.... በነበሩበት በእስራኤል እና በአካባቢው ግዛቶች የሆነውን እንጅ፥ ከቅኝ ግዛት ነፃ በነበረው በኢትዮጵያ ግዛት የተፈጸመውን፥ የመጻፍ አጋጣሚው ስላልፈቀደላቸው ነው።
 የጌታ ኢየሱስ ትምህርት፥ እድገቱ እና ትምህርቱ በኢትዮጵያ
ምንም ልጅ ቢሆን፥ ከተቀበለው መከራ መታዘዝን ተማረ...” (ዕብ 58) የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ በመከራ መማር የሚጀምረው፥ ከተወለደ ሁለት ዐመት ሳይሞላው ወደ ግብጽ በመሰደድ ነው።
ወደ ገዛ አገሩም መጥቶ እስኪገረሙ ድረስ በምኩራባቸው ያስተምራቸው ነበር እንዲህም አሉ፦ ይህን ጥበብና ተአምራት ይህ ከወዴት አገኘው?” (ማቴ 13: 54)
አንድ ሰው፥ ማስተማር ከመጀመሩ፥ በፊት ሊማር ይገባል። የጌታ ኢየሱስ፥ የትምህርቱ ከፍታ ወይም ጥልቀት፥ ለአይሁድ መምህራን አግራሞትን ፈጥሮባቸዋል። የት እንደተማረ የሚያውቁት ነገር አልነበረም።
በቅድሚያ፥ተምሯል፥ ወይንስ አልተማረም?’ የሚለው ጥያቄ መልስ ሊገኝለት ይገባላ። በእርግጥ፥ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደማንኛውም ህፃን መጻፍ እና ማንበብ ተምሯል።
ኢየሱስም ደግሞ ጥበብ በቁመት በሞገስም በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ያድግ ነበርበጥበብ አደገማለት እውቀቱ ጨመረ ማለት ነው። ቀጥሎም፥ተምሯልሲባል፤ ደሞስ፥ ተፀነሰ፣ ተወለደ፣ ተራበ፣ ተጠማ፣ በላ፣ ጠጣ፣ አንቀላፋ አዘነ፣ ተከዘ፣ አስተማረ፣ ታመመ፣ ሞተ፣ ... ካልን፥ተማረማለት አይከብድም ኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ፥ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንም።” (ዕብ 415) ከተባለ፥ተምሯልየሚለውንም ያስማማል፥ መማር ኃጢያት ስላልሆነ።
የት ተማረ? እንዴት ተማረ? እስራኤል ውስጥ ወይንስ ከእስራኤል ውጭ? የሚሉ ጥያቄዎች፥ ምክንያታዊ በሆነ መልኩ፥ መልስ ሊያገኙ ይገባል፥
ከእስራኤል ውጭ ከሆነ፥ የት? ማስራጃዎችስ?
እስራኤል ውስጥ ቢማር፥ የት እንደተማረ ታሪኩን መዝግበው ያቆዩን ነበር... ሲፀነስ፣ ሲወለድ፣ ሲገረዝ፣ ሲሰደድ... የመዘገቡ ወንጌላውያን፥ ከስደት እስኪመለስ ምንም አላሉም፥ ይህ የሚያሳየው፥ በተሰደደበት አገር ታሪኩን የጻፋ ሰዎች፥ አብረው፥ አለመሄዳቸውን ነው።
ከአሥራ ሁለት ዓመቱ እስከ ሰላሳ ዓመቱም፥ በህጻንነት ዘመኑ ወደሸሸበት አገሩ ተመልሶ ሲሄድ፥ ሲኖር፣ ሲማር... ወንጌላውያኑ በዚያ አብረውት ስላልነበሩ፥ አልመዘገቡትም፥ አልተረኩትም...
በኢትዮጵያ ከሆነስ የተማረው?
የአገሪቱ የትምህርት ልማድ እንደሚያሳየው፥ ልጆች ድቁና ከተቀበሉ በኋላ፥ በአማካኝ፥ ከአሥር ዓመት እድሜያቸው ጀምረው፥ ለብዙ ዓመታት፥ በተለያዩ ትምህርት ቤቶችና ተቋማት በመሄድ መንፈሳዊ ጥበብን፥ ይቀስማሉ። በዚህ ወቅት ወላጆቻቸው እንዳያገኝዋቸው በተለያየ ምክንያት፥ ትምርታቸውን አቋርጠው እንዳይዎስዷቸው፥ በማሰብ ማንነታቸውን ይደብቃሉ፣ ስማቸውንም ይቀይራሉ፥ የሚሄዱበትን ቦታም ለሚያውቋቸው ሰዎች አይናገሩም። ጌታ በጎልማሳነት ዘመኑም የፈጸመው ይህንኑ ነው።
ሌላው ትኩረት የተነፈገው ማስረጃ ጌታ በሚያስተምርበት ወቅት፥ ብዙ ምሳሌያዎችን መጠቀሙ ነው። ይህም የሚያስረዳን፥ የቋንቋ ልዩነት መኖሩንና አሳቡን እንዲረዱለት፥ ምሳሌዎችን ደጋግሞ መጠቀሙ ነው። ከዚህ በተጨማሪም ጌታ በሚያስተምርበት ወቅት፥ ቅዱስ ማርቆስ ይተረጉምላቸው ነበር። እንደ ጣሊታ ቁሚ (ማር 541) ኢፍታህ (ይፍታህ ማር 734) ... የመሳሰሉ ቃላት የኢትዮጵያውያን እንጅ፥ የዕብራውያን ባለመሆናቸውና እስራዊላውያን ባለመረዳታቸው፥ ቅዱስ ማርቆስ ሲተረጉምላቸው አይተናል።
ከላይ ከቀረቡት ማስረጃዎች በተጨማሪ፥አባ አባ ብላችሁ የምትጠሩበትን የልጅነት መንፈስን ሰጣችሁ፥በሚለው ውስጥአባ አባ፥ አባባየሚለው የጥሪ ቃል፥ ከኢትዮጵያውያን የተገኘ ለመሆኑ አያጠያይቅም። በዚያን ዘመንና ከዚያም በፊት፥ አምላክ እግዚአብሔርን፥አባ አባብለው ይጠሩ የነበር፥ ኢትዮጵያውያን ብቻ ናቸው።
ሕፃኑም አደገ፥ ጥበብም ሞልቶበት በመንፈስ ጠነከረ፤ የእግዚአብሔርም ጸጋ በእርሱ ላይ ነበረ።” (ሉቃ 2: 40)ጥበብ ሞላበት ማለት ሲወለድ ጥበብ አልሞላበትም ነበር፥ ማለት ነው።በመንፈስ ጠነከረ ማለት ሲወለድ ከነበረው የመንፈስ ጥንካሬ ጨመረ ማለት ነው። በሦስት ዓመቱ እና በሰላሳ ዓመቱ የነበረው የእውቀት ደረጃ እኩል አልነበረም ማለት፥ እስከ ሰላሳ ዓመት ዕድሜው በመማር ዕውቀት ጨምሯል፥ ማለት ነው።  ኢየሱስም ደግሞ ጥበብ በቁመት በሞገስም በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ያድግ ነበር” (ሉቃ 2: 52)በጥበብ ማለት፥ ጥበብ (ባት) በቁሙ፥ ዕውቀት፣ ብልኀት፣ ፈሊጥ፣ ፍልስፍና፣ ሕክምና፣ ጥንቆላ፣ ምክር፣ ተንኮል። (ኪወክ)
ወዳደገበቱም ወደ ናዝሬት መጣ እንደ ልማዱም በሰንበት ቀን ወደ ምኵራብ ገባ፥ ሊያነብም ተነሣ።” (ሉቃ 4: 16)ወደ ናዝሬት መጣ...’ ከተባልን፤ ከየት? ብለን እንድንጠይቅ ያደርገናል። ምክንያቱም፥ ከአሥራ ሁለት ዓመት እድሜው ጀምሮ፥ በሰላሳ ዓመቱ እስኪመለስ በዚያ አለመኖሩን ነው።እንደልማዱም በሰንበት ቀን ወደ ምኩራብ ገባሲል፥ ምኩራብ በኦሪት፥ ወደ አንድ እግዚአብሔር በማህበር ጸሎት የሚጸለይበት፥ የአምልኮ ቦታ ነው። ይህም የአምልኮ ቦታ የነበረው፥ በኢትዮጵያና በእስራኤል አገር ብቻ ነበር።እንደልማዱሲል፥ ይህን ልማድ ያደረገው፥ ወደ እስራኤል ከመምጣቱ በፊት፥ በኢትዮጵያ ሳለ ነው።
ወደ ገዛ አገሩም መጥቶ...” (ማቴ 13: 54) እኅቶቹስ ሁሉ በእኛ ዘንድ ያሉ አይደሉምን? እንኪያስ ይህን ሁሉ ከወዴት አገኘው? ተሰናከሉበትም።” (ማቴ 13: 56) አይሁድም፦ ይህ ሰው ሳይማር መጻሕፍትን እንዴት ያውቃል? ብለው ይደነቁ ነበር።” (ዮሐ 715) ‘... ሳይማር እንዴት ያውቃል ማለታቸው፥ እነርሱ አላስተማሩትም፥ ማለት እንጅ፥ አልተማረም ማለት አይደለም። ሰንበትም በሆነ ጊዜ በምኵራብ ያስተምር ጀመር፤ ብዙዎችም ሰምተው ተገረሙና፦ እነዚህን ነገሮች ይህ ከወዴት አገኛቸው? ለዚህ የተሰጠችው ጥበብ ምንድር ናት? በእጁም የሚደረጉ እንደነዚህ ያሉ ተአምራት ምንድር ናቸው?” (ማር 6: 2)እንደነዚህ ያሉ ተአምራት ምንድር ናቸው?ብለው መጠየቃቸው፥ ጌታ የፈጸማቸውን ጥበባት እና ታምራት እነሱ አያውቋቸውም። እነሱ የማያቁት እውቀት ከሆነ ደግሞ፥ የተማረው ሌላ ቦታ ነው። ጥበብ፥ በመማር የሚገኝ እውቀት ነው፥ እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ፥ ሙሴም የግብፆችን ጥበብ ሁሉ ተማረ፥ በቃሉና በሥራውም የበረታ ሆነ።” (ሐዋ 7: 22) ጥበብ በመማር ብቻ ሳይሆን፥ መጻሕፍትን በማንበብም የሚገኝ እንደሆነ፥ ቅዱስ ጳውሎስ፥ እንዲህ በማለት አሳስቦናል፥ ከሕፃንነትህም ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን፥ መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳን መጻሕፍትን አውቀሃል።” (2ጢሞ 315)
ጌታ ከፈጸማቸው ታምራት ውስጥ አንዱ፥ የሞተችውን ብላቴና ያስነሳበት ጥበብ ነው፥ የብላቴናይቱንም እጅ ይዞ፦ ጣሊታ ቁሚ አላት፤ ፍችውም አንቺ ብላቴና ተነሽ እልሻለሁ ነው።” (ማር 5: 41) ‘...እጅ ይዞ... ቁሚ አላትበሚለው ጥቅስ ውስጥ፥ ከጌታ አንደበት የወጣውቁሚየሚለውን ትእዛዝ፥ የኢትዮጵያውያን ቃል ነው። ይህቁሚየሚለው ቃል፥ እንግሊዝኛን (Cumi or Kumi) የሚለውን ጨምሮ፥ በተለያዩ ቋንቋዎች በተጻፉ መጽሐፍ ቅዱስ፥ ድምጹቁሚየሚል ሁኖ፥ ተመዝግቦ ይገኛል።
በተመሳሳይ፥ ዲዳ እና ደንቆሮ የነበረውን ሰው ሲፈውስ፥ የተጠቀመው፥ የኢትዮጵያውያን ካህናት፥ የሚሉትን ቃል፥ይፍታህየሚለውን ነው። ወደ ሰማይም አሻቅቦ አይቶ ቃተተና፦ ኤፍታህ አለው፥ እርሱም ተከፈት ማለት ነው።” (ማር 7: 34) ይህም ቃል የእንግሊዝኛውን (Ephphatha) ጨምሮ፤ በተለያዩ የዓለም ቋንቋዎች፥ በተመሳሳይ ድምጽ ተመዝግቦ ይገኛል። እነዚህ፥ ከላይ የጠቃቀስናቸው ቃላት የሚያረጋግጡልን፥ ይናገር የነበረው፥ የኢትዮጵያውያንን ቋንቋ እንደነበረ ነው። ይህም፥ በሌላ አገላለጽ፥ ጌታ ኢየሱስ፥ አብዛኛውን ምድራዊ ህይወት የኖረው፥ በኢትዮጵያ ውስጥ እንደሆነ ነው።


No comments:

Post a Comment

ማውጫ

መግቢያ                                                                                                     ክፍል አንድ፡ ኢትዮጵያ እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ታ...